ጠብ
19 ቁጥሮች14አማርኛምሳ 3:30
30ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ፥ እርሱ ክፉ ካልሠራብህ።
ምሳ 6:12-14
ምሳ 6:16-19
ምሳ 10:12
12ጥል ክርክርን ታስነሣለች፤ ፍቅር ግን ኃጢአትን ሁሉ ትከድናለች።
ምሳ 13:10
10በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።
ምሳ 17:1
1ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት፡ በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።
ምሳ 21:19
19ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ፡ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
ምሳ 22:10
10ፌዘኛን ብታወጣ ክርክር ይወጣል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል።
ምሳ 25:8
8ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት፡ ለክርክር ፈጥነህ አትውጣ፤
ምሳ 25:24
24ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ፡ በሰገነት ማዕዘን መቀመጥ ይሻላል።
ምሳ 26:17
17አልፎ በሌላው ጥል የሚደባለቅ፡ ውሻን በጅራቱ እንደሚይዝ ነው።
ምሳ 30:33
33ወተት መግፋት ቅቤን ያወጣል፥ አፍንጫንም መጭመቅ ደምን ያወጣ፤ እንዲሁም ቍጣን መጐተት ጠብን ያወጣል።
ማቴ 5:25
25“አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤
2ኛ ጢሞ 2:14
14ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።