ትንቢተ ሶፎንያስ 2

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች3:04 አዳምጥ
አዳምጥ 3:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እናንተ እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፥ ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ትኵሳት ሳይመጣባችሁ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፥ ተከማቹም።

3እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፤ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።

4ጋዛ ትበረበራለች፥ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፤ አዞጦንንም በቀትር ወደ ውጭ ያሳድዱአታል፥ አቃሮንም ትነቀላለች።

5በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።

6ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል።

7የባሕሩም ዳር ለይሁዳ ቤት ቅሬታ ይሆናል፥ በዚያም ይሰማራሉ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ይጐበኛቸዋልና፥ ምርኮአቸውንም ይመልሳልና በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ ማታ ይተኛሉ።

8በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።

9ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፤ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።

10በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል።

11እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፤ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።

12“እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።”

13እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል፥ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌንም ባድማ፥ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል።

14መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፤ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፤ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፤ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።

15ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፡” ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፤ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።

ማብራሪያ

2:1-3 ነቢዩ፣ ሀገራዊ ጥፋትን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ እንደመሆኑ መጠን፣ ለሀገራዊ ንስሐ ጥሪ ያደርጋል። እግዚአብሔርን የማትሻ፣ ወደ እግዚአብሔርም ምኞት የሌላት ሀገር፣ የእርሱን ሞገስና ጸጋ አትፈልግም፤ ንስሐ ለመግባትና ለመታደስም ፍላጎት የላትም። ወይም ደግሞ፣ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባት የሚችል ምንም ነገር የሌላትና እግዚአብሔር ዘንድ የማትወደድ ሀገር ናት፤ እግዚአብሔርም በትክክል “ከእኔ ራቁ” ሊላት ይችል የነበረ ቢሆንም፣ እርሱ ግን “ፊቴን ትሹ ዘንድ ወደ እኔ ተሰብሰቡ” ይላል። የእግዚአብሔር ድንጋጌ በማይጸጸቱ ኃጢአተኞች ላይ ምን እንደሚያመጣ እናውቃለን፤ ስለዚህም ሁሉም ሰው በጸጋው ዘመን ንስሐ እንዲገባ በጥልቀት ሊያሳስበው ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6