ኦሪት ዘኍልቍ 29

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች8:22 አዳምጥ
አዳምጥ 8:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው።

2እንከን የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

3ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቊርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራውም በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ፣ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት አቅርቡ፤

4ከእያንዳንዱም ሰባት የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።

5ማስተስረያ እንዲሆናችሁም አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ በተጨማሪ አቅርቡ።

6እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋር በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።

7“ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ሥራም አትሥሩ።

8ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

9ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ዱቄት አቅርቡ፤

10ከሰባቱ የበግ ጠቦቶችም ከእያንዳንዳቸው ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።

11ማስተስረያ እንዲሆንም ለኀጢአት መሥዋዕት ከሚቀርበው እንዲሁም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ቀርቦ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

12“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም (ያህዌ) የሰባት ቀን በዓል አክብሩ።

13ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ እንዲያሰኝ በእሳት አቅርቡ

14ከዐሥራ ሦስቱ ወይፈኖች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከሁለቱ አውራ በጎችም ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርቡ፤

15እንዲሁም ከዐሥራ አራቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርቡ።

16ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

17“ ‘በሁለተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

18ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር በተወሰነው ቊጥር መሠረት የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን አብራችሁ አቅርቡ።

19ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ አውራ ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

20“ ‘በሦስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ አንድ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

21ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አብራችሁ አቅርቡ።

22ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

23“ ‘በአራተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

24ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተደነገገው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

25ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

26“ ‘በአምስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

27ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

28ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

29“ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

30ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

31ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

32“ ‘በሰባተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

33ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

34ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

35“ ‘በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩ።

36ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ቍርባን በእሳት አቅርቡ።

37ከወይፈኑ፣ ከአውራ በጉና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።

38ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

39በስእለትና በበጎ ፈቃድ ከምታቀርቧቸው ቍርባኖች በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቊርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቊርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በተወሰኑት በዓሎቻችሁ ላይ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) አቅርቡ።’ ”

40ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው።

ማብራሪያ

29:1-11 በሰባተኛው ወር ከሌሎች ወራት ይልቅ ብዙ ቅዱሳን ክብረ በዓላት ነበሩ። ይህ የመኸርና ዘር የሚዘራበት ጊዜ መካከል ያለው ክፍተት ነበር። ከዚህ ሕይወት አጣዳፊ ሥራዎች የምናገኘው ትርፍ ጊዜ በበዛ መጠን፣ ለእግዚአብሔር ቀጥተኛ አገልግሎት የምናሳልፈው ጊዜም እንዲሁ በበለጠ መብዛት ይገባዋል። የመለከት መንፋት ታዝዞ ነበር፣ ዘሌ 22:24። በዚያ ቀን የሚያቀርቡት መሥዋዕት ምን እንደሆነ እዚህ ጋር ተነግሯቸዋል። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ከቅዱሳት መጻሕፍት ሊያውቁ የሚሹ፣ አንድን ክፍል ከሌላው ጋር ማስተያየት አለባቸው። የኋለኛው የመለኮታዊ ብርሃን ግልጽ መገለጫዎች በቀደመው ክፍል የጨለመውን ያብራራሉ፣ የጎደለውንም ይሞላሉ፤ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም እንዲሆን።

ምዕራፍ 29 ይህ ምዕራፍ በሰባተኛው ወር በሦስቱ ታላላቅ በዓላት ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይሾማል። I. በዚያ ወር በመጀመሪያው ቀን በመለከት በዓል (ቁጥር 1-6)። II. በአሥረኛው ቀን በስርየት ቀን (ቁጥር 7-11)። III. በአሥራ አምስተኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ሰባት ቀናት በዳስ በዓል (ቁጥር 12-38)። ከዚያም የእነዚህ ሥርዓቶች ማጠቃለያ (ቁጥር 39, 40)።

ቁጥር 1-11 በሰባተኛው ወር ከሌሎች ወራት ይልቅ ብዙ የተቀደሱ በዓላት ነበሩ። ይህ የሆነው እስራኤል ከግብፅ እስከምትወጣበት ጊዜ ድረስ የመጀመሪያው ወር ስለነበረ ብቻ ሳይሆን (ይህም በአቢብ ወር ላይ በመውደቁ ከዚህ በኋላ በሁሉም የቤተ ክርስቲያን ስሌቶች የወራት መጀመሪያ እንዲሆን አድርጎታል)፣ ነገር ግን አሁንም በኢዮቤልዩ እና በዕረፍት ዓመታት ሲቪል ስሌቶች የመጀመሪያው ወር ሆኖ ስለቀጠለ ነው። እንዲሁም በመከር እና በመዝራት ጊዜ መካከል ያለው የእረፍት ጊዜ ስለነበር፣ መቅደሱን ለማገልገል ብዙ ጊዜ ስለነበራቸው ነው። ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር አስፈላጊ እና ምሕረት የሚጠይቁ ሥራዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመሥዋዕት ነፃ ቢያደርግም፣ ከዚህ ሕይወት አስቸኳይ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ ባገኘን ቁጥር፣ በእግዚአብሔር ቀጥተኛ አገልግሎት ብዙ ጊዜ ማሳለፍ እንዳለብን ነው።

1. እዚህ ላይ በወሩ የመጀመሪያ ቀን፣ በመለከት ነፊያ ቀን የሚቀርቡት መሥዋዕቶች ተሹመዋል። ይህ ቀን በስርየት ቀን ለሚደረገው ታላቅ የተቀደሰ ሐዘን እና በዳስ በዓል ለሚደረገው የተቀደሰ ደስታ ዝግጅት ነበር። አንድ ሃይማኖታዊ አገልግሎት ለሌላው እንድንዘጋጅ እና ሁሉም ለሰማይ እንድንዘጋጅ ሲረዳን፣ የመለኮታዊ ሥርዓቶች ዓላማ በሚገባ ይፈጸማል። የመለከት ነፊያ በዘሌዋውያን 23:24 ላይ ተሹሞ ነበር። እዚህ ላይ ሕዝቡ በዚያ ቀን ምን ዓይነት መሥዋዕቶችን ማቅረብ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፣ በዚያን ጊዜ ግን ምንም አልተጠቀሰም። ማስታወሻ፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን አንድ ክፍል ከሌላው ጋር ማነጻጸር አለባቸው፣ እናም ተመሳሳይ ነገርን የሚያመለክቱ ክፍሎችን አንድ ላይ ማሰባሰብ አለባቸው። ምክንያቱም የመለኮታዊ ብርሃን የኋለኛ ግኝቶች የጨለመውን ያብራራሉ እና በቀድሞው የጎደለውን ይሞላሉ፣ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም እንዲሆን። በዚያን ጊዜ የሚቀርቡት መሥዋዕቶች እዚህ ላይ በዝርዝር ታዘዋል (ቁጥር 2-6)፣ እናም እነዚህ የዕለት ተዕለት መባውን እና የአዲስ ወር መባውን እንዳይሽሩ ጥንቃቄ ተደርጓል። በዚህም በእግዚአብሔር አገልግሎት ያለንን ቅንዓት ለመቀነስ ሰበብ መፈለግ እንደሌለብን፣ ወይም መልካም ግዴታን ለመተው ሰበብ በማግኘታችን ደስ መሰኘት እንደሌለብን፣ ይልቁንም በሃይማኖት ውስጥ ከመደበኛው በላይ ለመሰብሰብ እና ለመስራት እድል በማግኘታችን ደስ መሰኘት እንዳለብን ይጠቁማል። የቤተሰብ አምልኮን የምንፈጽም ከሆነ፣ ይህ ከግል ጸሎቶቻችን ነፃ ያደርገናል ብለን ማሰብ የለብንም፤ ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያን በምንሄድባቸው ቀናት ብቻችንን እና ከቤተሰቦቻችን ጋር እግዚአብሔርን ማምለክ አያስፈልገንም ብለን ማሰብ የለብንም፤ ይልቁንም ሁልጊዜ በጌታ ሥራ መትጋት አለብን።

2. በስርየት ቀን። በዘሌዋውያን 16 ላይ ሥርዓቱን ያገኘንባቸው የዚያ ቀን አገልግሎቶች በሙሉ፣ እናም አንድ ሰው በቂ ችግርና ወጪ የሚጠይቁ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ቢሆንም፣ እዚህ ላይ የሚቃጠሉ መባዎች እንዲቀርቡ ታዝዘዋል (ቁጥር 8-10)። ምክንያቱም በእምነታችንና በንስሐችን፣ በዚያ ቀን በሚደረጉት ነገሮች የተገለጹት እነዚያ ሁለቱ ታላላቅ የወንጌል ጸጋዎች፣ በሚቃጠሉ መባዎች ውስጥ በንጹህነት የታሰበውን የእግዚአብሔርን ክብር እና ሞገስ ማየት አለብን፤ ከታላቁ የስርየት ኃጢአት መባ በተጨማሪ (ቁጥር 11) ለኃጢአት መባ የሚሆን የአውራ ፍየል ግልገልም ሊኖር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመጀመሪያ ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፤ መለከቶች የሚነፉበት ቀን ነው። አማርኛ ENGNIV “ ‘On the first day of the seventh month hold a sacred assembly and do no regular work. It is a day for you to sound th… English BCV በታ ቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻውዐይቲ ወርሒ፥ ቅዱስ ጉባኤ ግበሩ። ዝኾነ ስራሕ ኣይትስርሑ። ንሳ መለኸት እትነፍሑላ መዓልቲ ትኹነልኩም። ትግርኛ GAZBIB “Ji'a torbaffaatti, ji'ichattiis guyyaa duraatti wal ga'ii qulqullaa'aa godhadhaa! Gaafas hojii nama dadhabsiisu hin ho… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበሳብዕ ወርኅ አመ ሠርቀ ወርኅ ቅድስተ ትሰመይ ለክሙ ይእቲ ዕለት ኵሎ ግብረ ማሕረስ ኢትግበሩ ባቲ ወዕለተ ትእምርት ትኩንክሙ። giz GAZGAZ “Ji'a torbaffaatti, ji'ichattiis guyyaa duraatti wal ga'ii qulqullaa'aa godhadhaa! Gaafas hojii nama dadhabsiisu hin ho… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻውዐይቲ ወርሒ፥ ቅዱስ ጉባኤ ግበሩ። ዝኾነ ስራሕ ኣይትስርሑ። ንሳ መለኸት እትነፍሑላ መዓልቲ ትኹነልኩም። ትግርኛ SWAHSUV Tena mwezi wa saba, siku ya kwanza ya mwezi, mtakuwa na kusanyiko takatifu; hamtafanya kazi yo yote ya utumishi; ni sik… Kiswahili