ትንቢተ ሚክያስ 7

AMHNIVአማርኛ20 ጥቅሶች3:57 አዳምጥ
አዳምጥ 3:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።

2ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ሰው ከምድር ጠፍቶአል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፣ ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።

3እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዡ እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጒቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።

4ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤ የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን መጥቶአል፤ የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሶአል።

5ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።

6ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ ሴት ልጅ በእናቷ ላይ፤ ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፤ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰዎቹ ናቸውና።

7እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤ አዳኜ የሆነውን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።

8ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ! ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል።

9እርሱን ስለ በደልሁ፣ እስኪቆምልኝ እስኪፈርድልኝም ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ቊጣ እቀበላለሁ፤ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ እኔም ጽድቁን አያለሁ።

10ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።

11ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት፣ ድንበራችሁንም የምታሰፉበት ቀን ይመጣል።

12በዚያ ቀን ሰዎች፣ ከአሦር እስከ ግብፅ ከተሞች፣ ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።

13ከሥራቸው የተነሣ፣ በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።

14ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

15“ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”

16አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።

17በደረታቸው እንደሚሳቡ ፍጥረታት፣ እንደ እባብም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዋሻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤ በፍርሀትም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ እናንተንም ይፈራሉ።

18የርስቱን ትሩፍ፣ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።

19ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤ በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ።

20ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል እንደ ገባህላቸው፣ ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም ምሕረትን ታደርጋለህ።

ማብራሪያ

፯፡፩-፯ ነቢዩ ራሱ፣ በፍጥነት ለጥፋት እየበሰለ ባለውና ብዙ መልካም ሰዎች መከራ በሚቀበሉበት ሕዝብ መካከል በመኖሩ ይተክዛል። ሰዎች በየራሳቸው ቤተሰብ ውስጥም ሆነ በቅርብ ዘመዶቻቸው ዘንድ መጽናናትንም ሆነ እርካታን አያገኙም ነበር። የቤተሰብ ግዴታዎችን መናቅና መተላለፍ የአጠቃላይ ብልሹነት አሳዛኝ ምልክት ነው። ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ ሰዎች መልካም ነገር ሊያገኙ አይችሉም። ነቢዩ ደህንነትንና መጽናናትን ያየው ወደ እግዚአብሔር በመመልከትና ድነቱም በሆነው በእግዚአብሔር ላይ በመጠበቅ ብቻ ነበር። በፈተናዎች ውስጥ ሳለን፣ በእርሱ ለመታመን የሚያስችል ጥንካሬና ጸጋ እንድናገኝ፣ በዙሪያችን ላሉትም ምሳሌ እንድንሆን፣ ያለማቋረጥ ወደ መለኮታዊ ቤዛችን መመልከት አለብን።

7:8-13

ኃጢአታቸውን ከልብ ንስሐ የገቡ ሁሉ በመከራ ውስጥ ታጋሾች ለመሆን ታላቅ ምክንያት ያገኛሉ። የዘመኑን ክፋት ለጌታ ስናማርር፣ የልባችንን ክፋት በተመለከተ ራሳችንን መውቀስ ይገባናል። በተገቢው ጊዜ እኛን ነጻ እንዲያወጣን በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ አለብን። እሱን ብቻ መመልከት የለብንም፣ እርሱንም መጠበቅ አለብን። በከባድ ጭንቀቶቻችን ውስጥ፣ ጌታን እንደ ድነታችን አምላክ አድርገን በእምነት ብንመለከት፣ ስለ ድነት ተስፋ ለመቁረጥ ምንም ምክንያት አናገኝም።

ጠላቶች ቢመጻደቁም ቢያንቋሽሹም፣ ዝም ይባላሉ ያፍሩማል። የጽዮን ቅጥሮች ለረጅም ጊዜ ፈራርሰው ቢቆዩም፣ የሚታደሱበት ቀን ይመጣል። እስራኤል ከሩቅ ቦታዎች ሁሉ ይመጣል፣ ተስፋ መቁረጥም ሳይመልሰው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም። አማርኛ ENGNIV What misery is mine! I am like one who gathers summer fruit at the gleaning of the vineyard; there is no cluster of gra… English BCV ፍረ ኦምን ፍረ ወይንን ምስተኣረዩ፥ ከም ዝተረፈ ቐሪም ኮይነ ኣለኹሞ ወይለይ! ንምግቢ ዝኸውን፥ ነፍሰይውን ዝተመነየቶ፥ ኣቐዲሙ ዝበሰለ በለስውን የለን። ትግርኛ GAZBIB Ani akka nama erga iji mukaa ciramee iji wayniis muramee booddee, haftee barbaaddatee dhabee waanan ta'eef, anaaf wayyo… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሊተ እስመ ኮንኩ ከመ ዘያስተጋብእ ሰዊተ ድኅረ ማእረር ወከመ ትቅራም ድኅረ ቀሥም ዘአልቦ አስካል ዘይበልዑ ደቂቅ። giz GAZGAZ Ani akka nama erga iji mukaa ciramee iji wayniis muramee booddee, haftee barbaaddatee dhabee waanan ta'eef, anaaf wayyo… Afaan Oromoo BCV aksum ፍረ ኦምን ፍረ ወይንን ምስተኣረዩ፥ ከም ዝተረፈ ቐሪም ኮይነ ኣለኹሞ ወይለይ! ንምግቢ ዝኸውን፥ ነፍሰይውን ዝተመነየቶ፥ ኣቐዲሙ ዝበሰለ በለስውን የለን። ትግርኛ SWAHSUV Ole wangu! Maana mimi ni kama hapo walipokwisha kuyachuma matunda ya wakati wa hari, kama zabibu zichumwazo baada ya ma… Kiswahili