ትንቢተ ሚክያስ 1

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:58 አዳምጥ
አዳምጥ 2:58 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።

2እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፤ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፤ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።

3እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይረግጣል።

4ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ።

5ይህ ሁሉ ስለ ያዕቆብ በደልና ስለ እስራኤል ቤት ኃጢአት ነው። የያዕቆብም በደል ምንድር ነው? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ የኮረብታው መስገጃ ምንድር ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?

6ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።

7የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰበቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።

8ስለዚህ ነገር ዋይ ብላ ታለቅሳለች፥ ባዶ እግርዋንና ዕራቁትዋን ሆና ትሄዳለች፤ እንደ ቀበሮ ታለቅሳለች፥ እንደ ሰጐንም ዋይ ትላለች፤

9ቍስልዋ የማይፈወስ ነውና፤ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።

10በጌት ላይ አታውሩ፤ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፤ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

11በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በዕራቁትነትሽና በእፍረት እለፊ፤ በጸዓናን የምትቀመጠው አልወጣችም፤ የቤትኤጼል ልቅሶ ከእናንተ ዘንድ መኖሪያውን ይወስዳል።

12ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።

13በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፤ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፤ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።

14ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፤ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ።

15በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፤ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል።

16ተማርከው ከአንቺ ዘንድ ወጥተዋልና ስለ ተድላሽ ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ጠጕርሽንም ተቈረጪ፤ ቡሃነትሽንም እንደ ንስር አስፊ።

ማብራሪያ

1:1-7 ምድር በውስጧ ካሉት ሁሉ ጋር ነቢዩን እንድትሰማ ተጠርታለች። የእግዚአብሔር ቅዱስ ቤተ መቅደስ ሐሰተኛ ምእመናንን አያድንም። እንደ ተራሮች ከፍ ያሉ ሰዎችም ሆኑ እንደ ሸለቆዎች ዝቅ ያሉ ሰዎች ራሳቸውን ወይም ምድሪቱን ከእግዚአብሔር ፍርድ ማስጠበቅ አይችሉም። በእግዚአብሔር ሕዝብ ዘንድ ኃጢአት ከተገኘ፣ እርሱ አይራራላቸውም፤ ኃጢአታቸውም እርሱን እጅግ ያስቆጣል፣ ምክንያቱም ስሙን እጅግ ያሳንሳሉ። የኃጢአትን መቅሰፍት ስንሰማ፣ ስለ የትኛው ኃጢአት እንደተቀጣን መመርመር ይገባናል። እጅግ ከፍ ከፍ ያሉ ሰዎችና ቦታዎች ለመንፈሳዊ በሽታዎች ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው። የመሪዎችና የአስተዳዳሪዎች ክፋት በእርግጥና በጽኑ ይቀጣል። ቅጣቱ ለኃጢአቱ ተመጣጣኝ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The word of the Lord that came to Micah of Moresheth during the reigns of Jotham, Ahaz and Hezekiah, kings of Judah–the… English BCV ብዘመን ኢዮኣታምን ኣካዝን ሕዝቅያስን ነገስታት ይሁዳ፥ ብዛዕባ ሰማርያን ኢየሩሳሌምን ሞሬታዊ ሚክያስ ዝረኣዮ ናብኡ ኸዓ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ። ትግርኛ GAZBIB Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yotaam, Ahaaz, Hisqiyaasis tarreetti Yihudaa irratti mo'anitti gara Miikiyaas nama mandar… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ ሚክያስ ወልደ ሞራት በመዋዕለ ኢዮአታም ወአካዝ ወሕዝቅያስ ነገሥተ ይሁዳ ዘርእየ በእንተ ሰማርያ ወበእንተ ኢየሩሳሌም። giz GAZGAZ Kun dubbii Waaqayyoo isa bara Yotaam, Ahaaz, Hisqiyaasis tarreetti Yihudaa irratti mo'anitti gara Miikiyaas nama mandar… Afaan Oromoo BCV aksum ብዘመን ኢዮኣታምን ኣካዝን ሕዝቅያስን ነገስታት ይሁዳ፥ ብዛዕባ ሰማርያን ኢየሩሳሌምን ሞሬታዊ ሚክያስ ዝረኣዮ ናብኡ ኸዓ ዝመፀ ቓል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ። ትግርኛ AMHNIV በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤ አማርኛ SWAHSUV Hili ndilo neno la Bwana lililomjia Mika, Mmorashti, katika siku za Yothamu, na Ahazi, na Hezekia, wafalme wa Yuda; mao… Kiswahili