ትንቢተ ሚክያስ 7

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች3:22 አዳምጥ
አዳምጥ 3:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።

2ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፤ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።

3እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፤ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።

4ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፤ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፤ አሁን ይሸበራሉ።

5ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፤ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።

6ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ፥ ምራቲቱም በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፥ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸውና።

7እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል።

8ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ።

9በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።

10ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” ያለች በእፍረት ትከደናለች።

11ዓይኖቼ ይመለከቱአታል፤ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች። ቅጥርሽ በሚሠራበት በዚያ ቀን ድንበርሽ ትስፋፋለች።

12በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፥ ከግብፅ እስከ ወንዙ፥ ከባሕርም እስከ ባሕር፥ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ወደ አንቺ ይመጣሉ።

13ምድሪቱ ግን በሚኖሩባት በሥራቸው ፍሬ ምክንያት ባድማ ትሆናለች።

14በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፤ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።

15“ከግብፅ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳያቸዋለሁ።”

16አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፤

17እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥ እንደ ምድርም ተንቀሳቃሾች እየተንቀጠቀጡ ከግንባቸው ይመጣሉ፤ ፈርተውም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፥ ስለ አንተም ይፈራሉ።

18በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።

19ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።

20ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ።

ማብራሪያ

፯፡፩-፯ ነቢዩ ራሱ፣ በፍጥነት ለጥፋት እየበሰለ ባለውና ብዙ መልካም ሰዎች መከራ በሚቀበሉበት ሕዝብ መካከል በመኖሩ ይተክዛል። ሰዎች በየራሳቸው ቤተሰብ ውስጥም ሆነ በቅርብ ዘመዶቻቸው ዘንድ መጽናናትንም ሆነ እርካታን አያገኙም ነበር። የቤተሰብ ግዴታዎችን መናቅና መተላለፍ የአጠቃላይ ብልሹነት አሳዛኝ ምልክት ነው። ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ ሰዎች መልካም ነገር ሊያገኙ አይችሉም። ነቢዩ ደህንነትንና መጽናናትን ያየው ወደ እግዚአብሔር በመመልከትና ድነቱም በሆነው በእግዚአብሔር ላይ በመጠበቅ ብቻ ነበር። በፈተናዎች ውስጥ ሳለን፣ በእርሱ ለመታመን የሚያስችል ጥንካሬና ጸጋ እንድናገኝ፣ በዙሪያችን ላሉትም ምሳሌ እንድንሆን፣ ያለማቋረጥ ወደ መለኮታዊ ቤዛችን መመልከት አለብን።

7:8-13

ኃጢአታቸውን ከልብ ንስሐ የገቡ ሁሉ በመከራ ውስጥ ታጋሾች ለመሆን ታላቅ ምክንያት ያገኛሉ። የዘመኑን ክፋት ለጌታ ስናማርር፣ የልባችንን ክፋት በተመለከተ ራሳችንን መውቀስ ይገባናል። በተገቢው ጊዜ እኛን ነጻ እንዲያወጣን በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ አለብን። እሱን ብቻ መመልከት የለብንም፣ እርሱንም መጠበቅ አለብን። በከባድ ጭንቀቶቻችን ውስጥ፣ ጌታን እንደ ድነታችን አምላክ አድርገን በእምነት ብንመለከት፣ ስለ ድነት ተስፋ ለመቁረጥ ምንም ምክንያት አናገኝም።

ጠላቶች ቢመጻደቁም ቢያንቋሽሹም፣ ዝም ይባላሉ ያፍሩማል። የጽዮን ቅጥሮች ለረጅም ጊዜ ፈራርሰው ቢቆዩም፣ የሚታደሱበት ቀን ይመጣል። እስራኤል ከሩቅ ቦታዎች ሁሉ ይመጣል፣ ተስፋ መቁረጥም ሳይመልሰው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV What misery is mine! I am like one who gathers summer fruit at the gleaning of the vineyard; there is no cluster of gra… English BCV ፍረ ኦምን ፍረ ወይንን ምስተኣረዩ፥ ከም ዝተረፈ ቐሪም ኮይነ ኣለኹሞ ወይለይ! ንምግቢ ዝኸውን፥ ነፍሰይውን ዝተመነየቶ፥ ኣቐዲሙ ዝበሰለ በለስውን የለን። ትግርኛ GAZBIB Ani akka nama erga iji mukaa ciramee iji wayniis muramee booddee, haftee barbaaddatee dhabee waanan ta'eef, anaaf wayyo… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሊተ እስመ ኮንኩ ከመ ዘያስተጋብእ ሰዊተ ድኅረ ማእረር ወከመ ትቅራም ድኅረ ቀሥም ዘአልቦ አስካል ዘይበልዑ ደቂቅ። giz GAZGAZ Ani akka nama erga iji mukaa ciramee iji wayniis muramee booddee, haftee barbaaddatee dhabee waanan ta'eef, anaaf wayyo… Afaan Oromoo BCV aksum ፍረ ኦምን ፍረ ወይንን ምስተኣረዩ፥ ከም ዝተረፈ ቐሪም ኮይነ ኣለኹሞ ወይለይ! ንምግቢ ዝኸውን፥ ነፍሰይውን ዝተመነየቶ፥ ኣቐዲሙ ዝበሰለ በለስውን የለን። ትግርኛ AMHNIV ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም። አማርኛ SWAHSUV Ole wangu! Maana mimi ni kama hapo walipokwisha kuyachuma matunda ya wakati wa hari, kama zabibu zichumwazo baada ya ma… Kiswahili