ትንቢተ ሚክያስ 2

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:30 አዳምጥ
አዳምጥ 2:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።

2በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፤ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።

3ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፤ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።

4በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፤ እነርሱም፦ ‘ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፤ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል፡’ ይላሉ።

5ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።

6ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፤ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።

7“የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?

8ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፤ ሳይፈሩም፤ የሚያልፉትን ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።

9የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፤ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።

10በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፤ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።

11ነፋስንም ተከትሎ፦ ‘ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ፡’ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።

12ያዕቆብ ሆይ፥ ሁለንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፤ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።

13ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፤ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።”

ማብራሪያ

ምዕራፍ 2:1-5 በሌሊት ክፋትን ለሚያስቡና በማለዳም ወደ ተግባር ለማዋል ለሚነሡ ሰዎች ወዮላቸው! ክፋትን በድንገተኛ ሐሳብ መፈጸም መጥፎ ነው፤ ነገር ግን በዕቅድና በቅድሚያ በማሰብ ማድረግ ደግሞ እጅግ የከፋ ነው። የብቸኝነትና የእረፍት ጊዜያትን በአግባቡ መጠቀም ትልቅ ፋይዳ አለው። በልብ ውስጥ ስግብግብነት የሚነግሥ ከሆነ ምሕረት ይባረራል፤ ልብ በዚህ ሲጠመድም ዓመፅና ማታለል በተለምዶ እጅን ይቆጣጠራሉ። በብልጽግና ውስጥ እጅግ ትዕቢተኞችና ደኅና ነን ብለው የሚታበዩት ሰዎች፣ በችግር ጊዜ ደግሞ ተስፋ ለመቁረጥ እጅግ ፈጣኖች ናቸው። እግዚአብሔር ፊቱን ከሚያዞርባቸው ሰዎች ወዮላቸው! ከጌታ ጉባኤ የሚያርቁን ወይም ከጥቅሞቹ/ከበረከቶቹ ሙሉ በሙሉ እንዳንጠቀም የሚያደርጉን እነዚህ እጅግ ከባድ መከራዎች ናቸው።

2:6-11 ‹ትንቢት አትናገሩ› ስለሚሉ፣ እግዚአብሔርም ቃላቸውን ተቀብሎ ኃጢአታቸው ቅጣታቸው ይሆናል። የማይድን በሽተኛን ሐኪም ከእንግዲህ አይጎብኘው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Woe to those who plan iniquity, to those who plot evil on their beds! At morning's light they carry it out because it i… English BCV እቶም በደል ዝምህዙ፥ ኣብ መደቀሲኦም ከዓ ኽፉእ ዝፍሕሱ ወይለኦም! ስልጣን ኣብ ኢዶም ስለ ዝኾነ፥ ብብርሃን ወጋሕታ ኽፍፅምዎ እዮም። ትግርኛ GAZBIB Warra siree isaanii irra ciisanii akeeka jal'inaa baasanii hamaa qopheessaniif wayyoo! Kana gochuudhaaf humni harka isa… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ እስመ መከሩ ኀጢአተ ወገብሩ እኩየ በውስተ ምስካቦሙ፤ ወበአሒቲ ዕለት ፈጸምዋ ወኢያንሥኡ እደዊሆሙ ኀበ እግዚአብሔር። giz GAZGAZ Warra siree isaanii irra ciisanii akeeka jal'inaa baasanii hamaa qopheessaniif wayyoo! Kana gochuudhaaf humni harka isa… Afaan Oromoo BCV aksum እቶም በደል ዝምህዙ፥ ኣብ መደቀሲኦም ከዓ ኽፉእ ዝፍሕሱ ወይለኦም! ስልጣን ኣብ ኢዶም ስለ ዝኾነ፥ ብብርሃን ወጋሕታ ኽፍፅምዎ እዮም። ትግርኛ AMHNIV ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና። አማርኛ SWAHSUV Ole wao wakusudiao mambo maovu, na kutenda mabaya vitandani mwao! Kunapopambazuka asubuhi huyafanya, kwa sababu ya kati… Kiswahili