የማቴዎስ ወንጌል 27

AMHNIVአማርኛ66 ጥቅሶች9:38 አዳምጥ
አዳምጥ 9:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጠዋት በማለዳ ላይ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስ ስለሚገደልበት ሁኔታ ተመካከሩ፤

2ካሰሩትም በኋላ ወስደው ለገዥው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

3አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፤ የወሰደውን ሠላሳ ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ ሽማግሌዎች መልሶ በመስጠት፣

4“ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” አለ። እነርሱም፣ “ታዲያ እኛ ምን አገባን፤ የራስህ ጕዳይ ነው!” አሉት።

5ስለዚህ ይሁዳ ብሩን በቤተ መቅደስ ውስጥ ወርውሮ ወጣ፤ ሄዶም ራሱን ሰቅሎ ሞተ።

6የካህናት አለቆች ብሩን አንሥተው፣ “የደም ዋጋ ስለ ሆነ ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ፤

7ተመካክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን ቦታ ገዙበት።

8ስለዚህም ያ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል።

9በዚህም በነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤ “ለእርሱ ዋጋ ይሆን ዘንድ የእስራኤል ልጆች የገመቱትን ሠላሳ ጥሬ ብር ተቀበሉ፤

10እግዚአብሔርም ባዘዘኝ መሠረት ለሸክላ ሠሪው ቦታ ከፈሉ።”

11በዚህ ጊዜ ኢየሱስ አገረ ገዥው ፊት ቀረበ፤ አገረ ገዥውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተው እንዳልኸው ነው” ሲል መለሰለት።

12የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ሲከሱት ግን ምንም መልስ አልሰጠም።

13በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “ስንት ነገር አቅርበው እንደሚከሱህ አትሰማምን?” አለው።

14እርሱ ግን አገረ ገዥው እስኪገረም ድረስ ለቀረበበት ክስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰም።

15አገረ ገዥው ሕዝቡ በበዓሉ እንዲፈታላቸው የሚጠይቁትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።

16በዚያን ጊዜ በዐመፅ የታወቀ በርባን የሚባል እስረኛ ነበር።

17ሕዝቡ እንደተሰበሰቡ ጲላጦስ፣ “ከበርባንና ክርስቶስ ከሚባለው ከኢየሱስ፣ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው፤

18ጲላጦስም በቅናት አሳልፈው እንደሰጡት ያውቅ ነበርና።

19በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፣ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለተሠቃየሁ፣ በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት።

20ነገር ግን የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች በርባን እንዲፈታላቸው ኢየሱስ ግን እንዲገደል ይለምኑ ዘንድ ሕዝቡን ያግባቡ ነበር።

21አገረ ገዥውም፣ “ከሁለቱ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቀ። እነርሱም፤ “በርባንን!” በማለት መለሱ።

22ጲላጦስም፣ “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ይሰቀል!” አሉ።

23ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን ክፉ ነገር አድርጎአል?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱ ግን አብዝተው እየጮኹ፣ “ይሰቀል!” አሉ።

24ጲላጦስ ሁኔታው ሽብር ከማስነሣት በስተቀር ምንም ፋይዳ የሌለው መሆኑን ተመልክቶ፣ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የራሳችሁ ነው” በማለት ውሃ አስመጥቶ በሕዝቡ ፊት እጆቹን ታጠበ።

25ሕዝቡም በሙሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን!” ብለው መለሱ።

26በዚህ ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።

27ከዚያም የአገረ ገዥው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዥው ግቢ ወሰዱት፤ ሰራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ።

28ልብሱን ገፈው ቀይ ልብስ አጠለቁለት፤

29እሾኽ ጐንጕነው አክሊል በመሥራት ራሱ ላይ ደፉበት፤ የሸምበቆ በትር በቀኝ እጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት አሾፉበት፤

30ተፉበትም፤ የሸምበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱ ላይ በሸምበቆው ደግመው ደጋግመው መቱት፤

31ካሾፉበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፈው የራሱን መጐናጸፊያ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ይዘውት ሄዱ።

32ይዘውትም ሲሄዱ ስምዖን ተብሎ የሚጠራ የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉንም እንዲሸከም አስገደዱት።

33ትርጕሙ፣ “የራስ ቅል ስፍራ” ከሆነው ጎልጎታ ከተባለው ቦታ ሲደርሱ፣

34ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈቀደም።

35ከሰቀሉትም በኋላ ዕጣ ጥለው ልብሱን ተካፈሉ፤

36በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። ከራስጌውም፣

37“ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሑፍ አኖሩ።

38ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ፣ አንዱ በግራው አብረውት ተሰቅለው ነበር።

39መንገድ ዐላፊዎችም በኀይል እየተሳደቡና ራሳቸውን እየነቀነቁ፣

40“ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን ውስጥ የምትሠራው፤ እስቲ ራስህን አድን! የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ በል ከመስቀል ውረድ!” ይሉት ነበር።

41የካህናት አለቆችም ከኦሪት ሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎች ጋር ሆነው እያሾፉበት እንዲህ ይሉ ነበር፤

42“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን።

43በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ይል ስለ ነበር እስቲ ከወደደው አሁን ያድነው!”

44ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።

45ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።

46በዘጠኝ ሰዓት ገደማ፣ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ትርጕሙም “አምላኬ፤ አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።

47በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ጩኸቱን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው!” አሉ።

48ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሰፍነግ በመውሰድ የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነከረው፤ ሰፍነጉንም በሸምበቆ ዘንግ ጫፍ ላይ በማድረግ እንዲጠጣው ለኢየሱስ አቀረበለት።

49የቀሩት ግን፣ “ተዉት፤ እስቲ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን!” አሉ።

50ኢየሱስ እንደ ገና ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ፤ መንፈሱንም አሳልፎ ሰጠ።

51በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ ምድር ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጣጠቁ፤

52መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሡ፤

53ከመቃብርም በመውጣት ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።

54የመቶ አለቃውና አብረውት ኢየሱስን ይጠብቁት የነበሩት የመሬት መናወጡንና የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው፤ ይህስ፣ “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!” አሉ።

55ከገሊላ የመጡና ኢየሱስን በሚያስፈልገው ነገር ለማገልገል የተከተሉት ብዙ ሴቶች ሁኔታውን ከርቀት እየተመለከቱ በአካባቢው ነበሩ።

56ከእነርሱም መካከል ማርያም መግደላዊት፣ ማርያም የያዕቆብና የዮሴፍ እናት እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ነበሩ።

57ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚባል ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ።

58ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስን በድን ለመነው፤ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።

59ዮሴፍም በድኑን ወስዶ በንጹሕ የበፍታ ጨርቅ ከፈነው፤

60ለራሱ ከዐለት አስፈልፍሎ ባዘጋጀው መቃብር ውስጥ አኖረው፤ ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን በር ዘግቶ ሄደ።

61በዚህ ጊዜ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ከመቃብሩ ትይዩ ተቀምጠው ነበር።

62በማግሥቱ፣ ከሰንበት ዝግጅት በኋላ ባለው ቀን፣ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ጲላጦስ ፊት ቀርበው እንዲህ አሉት፤

63“ክቡር ሆይ፤ ያ አሳች በሕይወት ሳለ፣ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ’ ያለው ትዝ ብሎናል፤

64ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ አስከሬኑን ሰርቀው ለሕዝቡ፣ ‘ከሙታን ተነሥቶአል’ ብለው እንዳያስወሩ መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ ትእዛዝ ስጥልን፤ አለዚያ የኋለኛው ስሕተት ከፊተኛው የባሰ ይሆናል!”

65ጲላጦስም፣ “ጠባቂዎች አሏችሁ፤ ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው።

66እነርሱም ሄደው መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት።

ማብራሪያ

27:1-10 ክፉ ሰዎች ወንጀላቸውን ሲፈጽሙ የሚያስከትለውን ውጤት ብዙም አይመለከቱም፤ ነገር ግን ለሁሉም ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ይሁዳ ሙሉ በሙሉ ለካህናት አለቆች ኃጢአት እንደሠራና ንጹሕን ሰው አሳልፎ እንደሰጠ አምኗል። ይህ ስለ ክርስቶስ ባሕርይ የተሟላ ምስክርነት ነበር፤ ገዥዎቹ ግን ልባቸው ደንድኖ ነበር። ይሁዳ ገንዘቡን ወርውሮ ወጣ፤ ከዚያም የመለኮታዊ ቁጣን ፍርሃትና የተስፋ መቁረጥን ሰቆቃ መሸከም ስላልቻለ ሄዶ ራሱን ሰቀለ። የይሁዳ ሞት የተባረከው ጌታችን ከመሞቱ በፊት እንደነበረ ጥርጣሬ የለውም። ታዲያ ይህን ደም ከምኞት ተነስተው ፈልገው፣ ይሁዳን አሳልፎ እንዲሰጥ አከራይተውት፣ በግፍ እንዲፈስ ፈርደውበት ሳለ፣ ለእነርሱ ምንም አልነበረምን? ሞኞች ኃጢአትን በዚህ መንገድ ይሳለቁበታል። ብዙዎች የተሰቀለውን ክርስቶስን በዚህ መልኩ ንቀውታል። የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት በማንሳት የራሳችንን ኃጢአት ማቃለል ደግሞ የልባችን ተንኮል የተለመደ ምሳሌ ነው። የእግዚአብሔር ፍርድ ግን እንደ እውነት ነው። ብዙዎች ይሁዳ የመለሰውን ገንዘብ ይዞ መሬት ስለመግዛቱ የሚናገረውን ይህን ክፍል፣ በክርስቶስ ደም ለባዕዳንና ከአሕዛብ ለሆኑ ኃጢአተኞች የታሰበውን ሞገስ ለማመልከት ይጠቀሙበታል። ይህ ትንቢትን ፈጽሟል፣ ዘካርያስ 11:12። ይሁዳ ወደ ንስሐ በጣም ቀረበ፣ ነገር ግን ለድነት አልነበረም። ተናዘዘ፣ ግን ለእግዚአብሔር አልነበረም፤ ወደ እርሱም ሄዶ፣ "አባት ሆይ፣ በሰማይ ላይ በደልኩ" አላለም። አንድ ሰው ሊኖረው በሚችለው እንደዚህ ባሉ ከፊል ንስሐዎች ማንም አይርካ፤ እንዲህ እያለ እኮ በትዕቢት፣ በጥላቻና በዓመፅ የተሞላ ሆኖ ሊቆይ ይችላልና።

27:11-25 በኢየሱስ ላይ ክፉ ሐሳብ ስላልነበረው፣ ጲላጦስ ራሱን እንዲያጸዳ አጥብቆ አበረታታው፤ እርሱንም ለማስለቀቅ ደከመ። ከሚስቱ የመጣው መልእክት ማስጠንቀቂያ ነበር። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በኃጢአት ፍላጎቶቻቸው ላይ እንቅፋት ለማድረግ ብዙ መንገዶች አሉት፤ እንዲህ ያሉ እንቅፋቶችን ከመለኮታዊ አቅርቦት (Providence)፣ ከታማኝ ወዳጆች እንዲሁም ከራሳችን ሕሊና ማግኘት ታላቅ ምሕረት ነው። ጌታ የሚጠላውን ይህን አስጸያፊ ነገር አታድርግ! የሚለው ቃል ወደ ፈተና ስንገባ የምንሰማው ሲሆን፣ እኛ ግን ብናዳምጠው መልካም ነው። በካህናቱ ግፊት ሕዝቡ በርባንን መረጠ። እግዚአብሔርን ሳይሆን ዓለምን ገዥያቸውና ክፍላቸው አድርገው የሚመርጡ ብዙዎች፣ በዚህ መንገድ የራሳቸውን ማታለያ ይመርጣሉ።

አይሁድ የክርስቶስን ሞት በብርቱ ስለፈለጉ፣ ጲላጦስ እምቢ ማለት አደገኛ እንደሆነ አሰበ። ይህ ትግል ደግሞ በከፋ ሰዎች ላይም ቢሆን የሕሊናን ኃይል ያሳያል። ሆኖም ሁሉም ነገር የተደራጀው ክርስቶስ የራሱ ጥፋት ሳይኖረው እንደተሰቃየ ሳይሆን፣ ለሕዝቡ ኃጢአት እንደሆነ ግልጽ ለማድረግ ነበር። ጲላጦስ በሥልጣኑ ሊጠብቀው የተገባውን ጻድቅና ንጹሕ ሰው ደም ከኃጢአቱ ራሱን ነጻ ለማድረግ መጠበቁ እንዴት ከንቱ ነው! አይሁዶች በራሳቸው ላይ የጫኑት እርግማን በሕዝባቸው ስቃይ ውስጥ በግልጽ ተመልሷል። የራሱ ኃጢአት የሌለበት እርሱን ካልሆነ በቀር ማንም የሌሎችን ኃጢአት ሊሸከም አይችልም።

ሁላችንንም አያሳስበንም? ኃጢአተኞች የእግዚአብሔርን ክብር የሚዘርፉና ነፍሳቸውን የሚገድሉ ተወዳጅ ኃጢአቶቻቸውን ለማቆየት ድኅነትን በሚጥሉበት ጊዜ፣ በርባስ በኢየሱስ ላይ አልተመረጠምን? የክርስቶስ ደም፣ በአይሁዶች ውድቀት/መካድ ምክንያት፣ በምሕረት አሁን ለመልካም በእኛ ላይ ሆኖአል። ኦህ፣ ለመጠጊያነት ወደ እርሱ እንሽሽ!

27:26-30 ስቅለት በሮማውያን ዘንድ ብቻ ይፈጸም የነበረ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ሞት ነበር። መስቀል መሬት ላይ ይቀመጥ ነበር፤ እጆችና እግሮችም በእርሱ ላይ ይሰመሩ ነበር፤ ከዚያም ተነስቶ ቀጥ ብሎ ይቆም ነበር፤ የሰውነት ክብደትም በችንካሮቹ ላይ እንዲንጠለጠል በማድረግ፣ ተሰቃዩት በስቃይ እስኪሞት ድረስ ይቆይ ነበር። ክርስቶስም እንዲህ በማድረግ በአዕማድ ላይ የተሰቀለውን የነሐሱን እባብ ምሳሌ ፈጸመ። ክርስቶስ እዚህ የተገለጸውን መከራና ውርደት ሁሉ የተቀበለው ለእኛ ዘላለማዊ ሕይወትን፣ ደስታንና ክብርን ይገዛልን ዘንድ ነበር።

27:31-34 ክርስቶስ እንደ በግ ወደ መታረድ፣ እንደ መሥዋዕትም ወደ መሠዊያ ተነድቷል። የክፉዎች ምሕረት እንኳ በእውነት ጨካኝ ነው። መስቀሉን ከእርሱ ወስደው፣ ሲሞን የሚባል አንድ ሰው እንዲሸከም አስገደዱት። አቤቱ፣ የሾምከብንን መስቀል ለመሸከም፣ በየዕለቱም በደስታ አንስተን አንተን ለመከተል ዝግጁ አድርገን። እንደ እርሱ ሐዘን ያለ ሐዘን ሆኖ አያውቅም? እርሱ የሞተውን የሞት ዓይነት ስንመለከትም፣ በዚያ ውስጥ እንዴት ያለ ፍቅር እንደወደደን እንመልከት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6