የማቴዎስ ወንጌል 26

AMHEVGአማርኛ75 ጥቅሶች10:01 አዳምጥ
አዳምጥ 10:01 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስም እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፥

2ለደቀ መዛሙርቱ፦ “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፥ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል፡” አለ።

3በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥

4ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ፤

5ነገር ግን፦ “በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን፡” አሉ።

6ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥

7አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

8ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና፦ “ይህ ጥፋት ለምንድር ነው?

9ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና፡” አሉ።

10ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?

11ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤

12እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች።

13እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።”

14በዚያን ጊዜ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፦

15“ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ?” እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።

16ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ አሳልፎ ሊሰጠው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር።

17በቂጣው በዓል በመጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ልናሰናዳልህ ትወዳለህ፡” አሉት።

18እርሱም፦ “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ፣ ‘መምህር፦ ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ፥ ይላል’ በሉት” አለ።

19ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ ፋሲካንም አሰናዱ።

20በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።

21ሲበሉም እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል።”

22እጅግም አዝነው እያንዳንዱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?” ይሉት ጀመር።

23እርሱም መልሶ፦ “ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው።

24የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፡” አለ።

25አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም መልሶ፦ “መምህር ሆይ፥ እኔ እሆንን?” አለ፤ “አንተ አልህ፡” አለው።

26ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ።

27ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤

28ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

29“ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣውም።”

30መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።

31በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ የሚል ተጽፎአልና፤

32ከተነሣሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ።”

33ጴጥሮስም መልሶ፦ “ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም፡” አለው።

34ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ።”

35ጴጥሮስ፦ “ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን፥ ከቶ አልክድህም፡” አለው። ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

36በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ፡ ደቀ መዛሙርቱንም፦ “ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ፡” አላቸው።

37ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመር።

38“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ” አላቸው።

39ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ “አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን፡” አለ።

40ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን፦ “እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን?

41ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው፡” አለው።

42ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፦ “አባቴ፥ ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን፡” አለ።

43ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው።

44ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፥ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።

45ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።

46ተነሡ፥ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል።”

47ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።

48አሳልፎ የሚሰጠውም፦ “የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት፤” ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።

49ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና፦ “መምህር ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን፡” ብሎ ሳመው።

50ኢየሱስም፦ “ወዳጄ ሆይ፥ ለምን ነገር መጣህ?” አለው። በዚያን ጊዜ ቀረቡ እጃቸውንም በኢየሱስ ላይ ጭነው ያዙት።

51እነሆም፥ ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቈረጠው።

52በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።

53ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን?

54እንዲህ ከሆነስ፦ ‘እንደዚህ ሊሆን ይገባል፡’ የሚሉ መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?”

55በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ፦ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።

56ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፡” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።

57ኢየሱስን የያዙትም ጻፎችና ሽማግሎች ወደ ተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት።

58ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።

59የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጐውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤

60ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም።

61በኋላም ሁለት ቀርበው፦ ይህ ሰው፦ “ ‘የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ልሠራው እችላለሁ፥’ ብሎአል፡” አሉ።

62ሊቀ ካህናቱም ተነሥቶ፦ “እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን?” አለው።

63ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፡” አለው።

64ኢየሱስም አለው፦ “አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ።”

65በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ፦ “ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።

66እነርሱም፦ “ሞት ይገባዋል፡” ብለው መለሱ።

67በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፊ መትተው፦

68“ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን፡” አሉ።

69ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ፦ “አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ” አለችው።

70እርሱ ግን፦ “የምትዪውን አላውቀውም” ብሎ በሁሉ ፊት ካደ።

71ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፦ “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፡” አለች።

72ዳግመኛም ሲምል፦ “ሰውየውን አላውቀውም፡” ብሎ ካደ።

73ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፦ “አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ፡” አሉት።

74በዚያን ጊዜ፦ “ሰውየውን አላውቀውም፡” ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።

75ጴጥሮስም፦ “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፡” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።

ማብራሪያ

26:1-5 ጌታችን ስለ መከራው ብዙ ጊዜ ገና ሩቅ እንደሆነ ሲናገር ነበር፤ አሁን ግን ቅርብ እንደሆነ ይናገራል። በዚያው ጊዜም የአይሁድ ሸንጎ በስውር እንዴት ሊገድሉት እንደሚችሉ ተመካከረ። ነገር ግን እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ማፍረስ ወደደ። ኢየሱስ፣ እውነተኛው የፋሲካ በግ፣ በዚያው በትክክለኛው ጊዜ ስለ እኛ ሊሰዋ ነበር፤ ሞቱና ትንሣኤውም በይፋ እንዲታወቅ ተደረገ።

፳፮፥፮-፲፫ በክርስቶስ ራስ ላይ የተቀባው ሽቱ የታላቅ ክብርና አክብሮት ምልክት ነበር። በልብ ውስጥ ለእየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ፍቅር ሲኖር፣ ለእርሱ ለመስጠት በጣም ውድ ነው የሚባል ነገር የለም። የክርስቶስ አገልጋዮችና አገልግሎታቸው በበዙ ቁጥር ሲነቀፉ፣ እርሱ ደግሞ ይበልጥ መቀበሉን ያሳያል። ይህ የእምነትና የፍቅር ተግባር እጅግ አስደናቂ ስለነበር፣ የማርያም እምነትና ፍቅር መታሰቢያ ሆኖ፣ ለሁሉም ለሚመጡት ትውልዶችና ወንጌል በሚሰበክበት ስፍራ ሁሉ እንደሚነገርለት ተነግሯል። ይህ ትንቢትም ተፈጽሟል።

26:14-16 ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት አስራ ሁለት ብቻ ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ እንደ ሰይጣን ነበረ፤ በእርግጥም ከሰማይ ወዲህ ያለ ማኅበረሰብ ፍጹም ንጹሕ ይሆናል ብለን ልንጠብቅ አይገባም። ሰዎች ሃይማኖተኛነታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በገለጹ ቁጥር፣ ልባቸው ከእግዚአብሔር ጋር ቅን ካልሆነ፣ ጉዳት የማድረስ ታላቅ ዕድል ይኖራቸዋል። አስተውሉ፤ የክርስቶስ የገዛ ደቀ መዝሙር፣ ትምህርቱንና የአኗኗሩን መንገድ እጅግ በሚገባ ያውቅ የነበረውና ለእርሱ የከዳው ይሁዳ፣ ክህደቱን ለማጽደቅ ይጠቅመው የነበረ ቢሆንም እንኳ፣ በምንም ዓይነት ወንጀል ሊከስሰው አልቻለም። ይሁዳ ምን ፈልጎ ነበር? ጌታው ባለበት ሁሉ ተቀባይነት አልነበረውምን? ኑሮው እንደ ክርስቶስ አልነበረምን? የክፉ ሁሉ ሥር የሆነው የገንዘብ እጦት ሳይሆን የገንዘብ ፍቅር ነው። ያን ክፉ ድርድር ከፈጸመ በኋላ፣ ይሁዳ ንስሐ ለመግባትና ለመሰረዝ ጊዜ ነበረው፤ ነገር ግን ትናንሽ ሐቀኝነት የጎደላቸው ተግባራት ሕሊናን ባደነደኑት ጊዜ፣ ሰዎች ያለምንም ማመንታት ይበልጥ የሚያሳፍርን ነገር ያደርጋሉ።

26:17-25

ልብ በሉ፤ ፋሲካውን የሚበሉበት ስፍራ በክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ተጠቁሞ ነበር። እርሱ ለዓላማው የሚቆሙትን የተደበቁትን ያውቃል፤ እርሱን ለመቀበል ፈቃደኛ የሆኑትን ሁሉ በጸጋ ይጎበኛል። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። በወንጌል ፋሲካ የክርስቶስ መገኘት እንዲኖራቸው የሚሻ ሁሉ እርሱ የሚለውን ማድረግ አለበት። ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በተለይም በፈተና ወቅት ሁልጊዜ ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባቸዋል። ምን ያህል በብርቱ እንደምንፈተን፣ እግዚአብሔርም ምን ያህል ለራሳችን እንደሚተወን አናውቅም፤ ስለዚህ ትዕቢተኞች ከመሆን ይልቅ መፍራት አለብን። የልብ ምርመራና ትጉህ ጸሎት በተለይም ከጌታ እራት በፊት ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ፋሲካችን ሆኖ አሁን ስለ እኛ እንደ ታረደ፣ ንስሐችንንና በደሙ ያለንን እምነት በማደስ፣ እንዲሁም ራሳችንን ለአገልግሎቱ በማስረከብ ይህን በዓል እንድናከብር።

26:26-30 ይህ የጌታ እራት ሥርዓት ለእኛ የፋሲካ እራት ነው፤ በእርሱም እስራኤል ከግብፅ ከወጣችበት መዳን ይልቅ እጅግ ታላቅ የሆነ መዳንን እናስታውሳለን። ውሰዱ፤ ብሉ፤ ክርስቶስ እንደተሰጣችሁ ተቀበሉት፤ የማስተስረያውን ክፍያ ተቀበሉ፣ አጽድቁት፣ ለጸጋውና ለመንግሥቱ ተገዙ። የታየ ምግብ፣ ወይም ሳህኑ የቱንም ያህል ቢያጌጥ፣ አይመግብም፤ መበላት አለበት፤ የክርስቶስ ትምህርትም እንዲሁ ነው። "ይህ ሥጋዬ ነው"፤ ይህም ማለት፣ መንፈሳዊ በሆነ መንገድ፣ ሥጋውን ያመለክታል እንዲሁም ይወክላል። ፀሐይን የምንካፈለው ፀሐይ በእጃችን በመግባቷ ሳይሆን፣ የፀሐይ ጨረሮች በእኛ ላይ በመውረዳቸው ነው፤ እንደዚሁም ክርስቶስን የምንካፈለው ጸጋውን እና ሥጋው በመሰበሩ የተገኙትን የተባረኩ ፍሬዎች በመካፈል ነው። የክርስቶቶስ ደም በወይን ያመለክታል እንዲሁም ይወከላል። ምስጋና አቀረበ፣ ይህም በሥርዓቱ በእያንዳንዱ ክፍል ወደ እግዚአብሔር እንድንመለከት ለማስተማር ነው። ይህን ጽዋም ለደቀ መዛሙርቱ ትእዛዝ በመስጠት ሰጣቸው፡- "ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ።" የኃጢአት ስርየት፣ በጌታ እራት ውስጥ፣ ለሁሉም እውነተኛ አማኞች የሚሰጥ ታላቅ በረከት ነው፤ እርሱም የሌሎች በረከቶች ሁሉ መሠረት ነው። ከእንዲህ ዓይነቱ ኅብረት ይሰናበታል፤ በመጨረሻም ደስ የሚያሰኝ ስብሰባ እንደሚጠብቃቸው ያረጋግጥላቸዋል። "እኔ ከእናንተ ጋር በአዲስነት እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ" የሚለው ቃል፣ ቅዱሳን ከጌታ ኢየሱስ ጋር የሚካፈሏቸውን የወደፊቱ ሁኔታ ደስታዎችና ክብሮች ያመለክታል። ይህ የአባቱ መንግሥት ይሆናል፤ የመጽናናት ወይንም እዚያ ሁልጊዜ አዲስ ይሆናል። ለኃጢአታችን ስርየት የተሰበረውን የክርስቶስን ሥጋና የፈሰሰውን ደሙን ውጫዊ ምልክቶች ስንመለከት፣ ይህ በዓል ሥጋውን እንድንበላ ደሙንም እንድንጠጣ ቃል በቃል እንደሰጠን ያህል ዋጋ እንዳስከፈለው እናስታውስ።

26:31-35 እንደ ጴጥሮስ እንደነበረው ተገቢ ያልሆነ ራስን መተማመን የመውደቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6