የዮሐንስ ወንጌል 13

AMHNIVአማርኛ38 ጥቅሶች6:06 አዳምጥ
አዳምጥ 6:06 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው።

2እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር።

3ኢየሱስም፣ አብ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር እንዳደረገለት፣ ከእግዚአብሔር እንደ ተላከና ወደ እግዚአብሔርም እንደሚመለስ ዐውቆ፣

4ከእራት ተነሣ፤ መጐናጸፊያውን አስቀመጠ፤ ወገቡንም በፎጣ ታጠቀ።

5ከዚያም በመታጠቢያው ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር እያጠበ በታጠቀው ፎጣ ያብስ ጀመር።

6ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እግሬን ታጥባለህ?” አለው።

7ኢየሱስም መልሶ፣ “የማደርገውን አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።

8ጴጥሮስም፣ “የለም፤ እግሬን ከቶ አታጥብም” አለው። ኢየሱስም፣ “ካላጠብሁህማ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም” አለው።

9ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ እንግዲያውስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንም ራሴንም እጠበኝ” አለው።

10ኢየሱስም፣ “ገላውን የታጠበ ሰው የሚያስፈልገው እግሩን ብቻ መታጠብ ነው፤ የቀረው አካሉ ግን ንጹሕ ነው። ሁላችሁም ባትሆኑ፣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ” አለው።

11“ሁላችሁም ንጹሓን አይደላችሁም” ያለው አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለ ነበር ነው።

12እግራቸውን አጥቦ ካበቃ በኋላም፣ ልብሱን ለብሶ ተመልሶ በቦታው ተቀመጠ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?

13እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና።

14እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል።

15እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ።

16እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው፣ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።

17እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ።

18“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን አብሮኝ የቈረሰ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።

19“ሲፈጸም እኔ እንደሆንሁ ታምኑ ዘንድ፣ ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ነገርኋችሁ።

20እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የላክሁትን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለም የላከኝን ይቀበላል።”

21ይህን ካለ በኋላም ኢየሱስ በመንፈሱ ታውኮ፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል” ሲል በግልጽ ተናገረ።

22ደቀ መዛሙርቱም ማንን ማለቱ እንደሆነ ግራ ተጋብተው እርስ በርሳቸው ተያዩ።

23ከእነርሱ አንዱ፣ ኢየሱስ ይወደው የነበረ ደቀ መዝሙር ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር።

24ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ደቀ መዝሙር በምልክት ጠቅሶ “ማንን ማለቱ እንደሆነ ጠይቀው” አለው።

25እርሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ደገፍ ብሎ፣ “ጌታ ሆይ፤ ማን ይሆን?” ብሎ ጠየቀው።

26ኢየሱስም፣ “ይህን ቊራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቊራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።

27ይሁዳም ቊራሹን እንጀራ እንደ ተቀበለ ወዲያው ሰይጣን ገባበት። ኢየሱስም፣ “የምታደርገውን ቶሎ አድርግ” አለው፤

28ይሁን እንጂ ኢየሱስ ለምን እንዲህ እንዳለው ማንም አላወቀም ነበረ።

29ይሁዳ ገንዘብ ያዥ ስለ ነበር፣ አንዳንዶቹ ለበዓሉ የሚያስፈልግ ነገር እንዲገዛ ወይም ለድኾች እንዲሰጥ ኢየሱስ የተናገረው መሰላቸው።

30ይሁዳም ያን ቊራሽ እንጀራ እንደ ተቀበለ ወጥቶ ሄደ፤ ሌሊትም ነበረ።

31ይሁዳ ከወጣ በኋላ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ በእርሱም እግዚአብሔር ከበረ።

32እንግዲህ እግዚአብሔር በእርሱ ከከበረ፣ እግዚአብሔር ልጁን በራሱ ዘንድ ያከብረዋል፤ ወዲያውም ያከብረዋል።

33“ልጆቼ ሆይ፤ ከእናንተ ጋር የምቈየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድ፣ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኋቸው፣ አሁንም ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ።

34“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።

35እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”

36ስምዖን ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትሄደው ወዴት ነው?” አለው። ኢየሱስም፣ “ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ ኋላ ግን ትከተለኛለህ” ሲል መለሰለት።

37ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስለ አንተ ሕይወቴንም ቢሆን አሳልፌ እሰጣለሁ” አለው።

38ኢየሱስም፣ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕይወትህን በርግጥ ለእኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት እልሃለሁ፤ ዶሮ ሳይጮኸ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ።”

ማብራሪያ

ዮሐንስ 13:1-17

ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ዓለም ውስጥ የራሱ የሆኑ ሰዎች አሉት፤ እርሱም በውድ ዋጋ ገዝቷቸዋል፥ ለራሱም ለይቷቸዋል፤ እነርሱም ልዩ ሕዝብ ሆነው ራሳቸውን ለእርሱ አስገዝተዋል። ክርስቶስ የሚወዳቸውን እስከ መጨረሻው ይወዳቸዋል። እውነተኛ አማኝን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለይ የሚችል ምንም ነገር የለም። ሰዓታችን መቼ እንደሚመጣ አናውቅም፤ ስለዚህም ለዘወትር ዝግጅት ልናደርገው የሚገባንን ነገር በፍጹም ችላ ልንለው አይገባም። ዲያብሎስ ወደ ሰዎች ልብ እንዴት እንደሚገባ በትክክል መናገር አንችልም። ነገር ግን አንዳንድ ኃጢአቶች እጅግ በጣም ኃጢአተኞች ከመሆናቸው የተነሳ፣ ከዓለምና ከሥጋ የሚመጣ ፈተናም የሌላቸው በመሆናቸው፣ በቀጥታ ከሰይጣን የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው። ኢየሱስ የተማሪዎቹን እግር ያጠበው፣ የእግዚአብሔርን ክብርና የወንድሞቻችንን መልካም ነገር የምናደርግበትን ማንኛውንም ነገር ከክብራችን የሚያንስ አድርገን እንዳናስብ ሊያስተምረን ነው። ወደ ግዴታችን መቅረብ አለብን፤ ማድረግ ያለብንን ነገር እንዳንሠራ የሚያግደንንም ሁሉ አስወግደን መጣል አለብን። ክርስቶስ የተማሪዎቹን እግር ያጠበው የመንፈሳዊውን መታጠብ ዋጋ፥ ነፍስንም ከኃጢአት ርኩሰት የመንጻት አስፈላጊነትን ሊያሳያቸው ነው። ጌታችን ኢየሱስ አሁን ባለው ጊዜ ትርጉማቸውን የራሱ ደቀ መዛሙርት እንኳን የማያውቁትን ብዙ ነገሮችን ያደርጋል፤ ነገር ግን በኋላ ያውቃሉ። በመጨረሻ ላይ ደግሞ እጅግ አስቸጋሪ በሚመስሉ ክስተቶች ውስጥ የነበረውን ደግነት እናያለን። የወንጌልን ጥሪ ማራቅ ትህትና ሳይሆን አለማመን ነው፤ ለእኛ ለመሆን እንደማይገባን በጣም የበዛ ወይም እውነት ለመሆን እጅግ በጣም መልካም ዜና እንደሆነ አድርጎ ማሰብ። በክርስቶስ በመንፈስ የታጠቡት ሁሉ፣ እነርሱ ብቻ በክርስቶስ ድርሻ አላቸው። ክርስቶስ የራሱ ያደረጋቸውና ያዳናቸው ሁሉንም ያጸድቃል ያቀድሳል። ጴጥሮስ ከመገዛትም በላይ፣ በክርስቶስ ሊታጠብ ለመነ። የጌታችን የኢየሱስን የማንጻት ጸጋና የዚያንም ሙሉ በሙሉ የሆነ ውጤት፣ በእጆቹና በራሱ ላይ ጭምር ለማግኘት ምንኛ ቀናተኛ ነበር! በእውነት ሊቀደሱ የሚፈልጉ፣ ሙሉ በሙሉ ሊቀደሱ ይፈልጋሉ፤ አጠቃላይ ሰውነታቸውን ከክፍሎቹና ከኃይሎቹ ሁሉ ጋር ንጹሕ እንዲሆን ይፈልጋሉ። እውነተኛ አማኝ ክርስቶስን ለመዳኑ ሲቀበል በዚህ መንገድ ይታጠባል። እንግዲያውስ በጸጋ በጽድቅ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች የዕለት ተዕለት ጥንቃቄ ምን መሆን እንዳለበት ተመልከቱ፤ እርሱም እግራቸውን ማጠብ ነው፤ ከዕለታዊ ጥፋት ራሳቸውን ማንጻት፣ እንዲሁም የሚያረክሳቸውን ነገር ሁሉ መጠበቅ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። አማርኛ ENGNIV It was just before the Passover Feast. Jesus knew that the time had come for him to leave this world and go to the Fath… English BCV ኢየሱስ ቅድሚ በዓል ፋሲካ፥ ካብዝ ዓለም እዙይ፥ ናብ ኣብ፥ ዝኸደላ ሰዓት ከም ዝበፅሐት ፈሊጡ፥ ነቶም ዘፍቀሮም ኣብዛ ዓለም እዚኣ ዘለዉ ናቱ፥ ክሳዕ መወዳእታ ኣፍቀሮም። ትግርኛ GAZBIB Ayyaana Faasiikaa dura, Yesus biyya lafaa kana keessaa gara abbaa dhaquudhaaf yeroon isaa akka ga'e in beeke; inni biyy… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምቅድመ በዓለ ፋሲካ ሶበ ኮነ የአምር እግዚእ ኢየሱስ ከመ በጽሐ ጊዜሁ ከመ ይፈልስ እምዝንቱ ዓለም ወየሐውር ኀበ አብ። ዘፈነዎ ወአፍቀሮሙ ለእሊኣሁ እለ ውስተ ዓለም ወለዝሉፉ አፍቀሮሙ። giz GAZGAZ Ayyaana Faasiikaa dura, Yesus biyya lafaa kana keessaa gara abbaa dhaquudhaaf yeroon isaa akka ga'e in beeke; inni biyy… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ቅድሚ በዓል ፋሲካ፥ ካብዝ ዓለም እዙይ፥ ናብ ኣብ፥ ዝኸደላ ሰዓት ከም ዝበፅሐት ፈሊጡ፥ ነቶም ዘፍቀሮም ኣብዛ ዓለም እዚኣ ዘለዉ ናቱ፥ ክሳዕ መወዳእታ ኣፍቀሮም። ትግርኛ SWAHSUV Basi, kabla ya sikukuu ya Pasaka, Yesu, hali akijua ya kuwa saa yake imefika, atakayotoka katika ulimwengu kwenda kwa B… Kiswahili