የዮሐንስ ወንጌል 13

AMHEVGአማርኛ38 ጥቅሶች4:55 አዳምጥ
አዳምጥ 4:55 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።

2እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥

3ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥

4ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤

5በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።

6ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን?” አለው።

7ኢየሱስም መልሶ፦ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” አለው።

8ጴጥሮስም፦ “የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም፡” አለው። ኢየሱስም፦ “ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም፡” ብሎ መለሰለት።

9ስምዖን ጴጥሮስም፦ “ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም፡” አለው።

10ኢየሱስም፦ “የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም፡” አለው።

11አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ፦ “ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም” አለው።

12እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?

13እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።

14እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።

15እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።

16እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።

17ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።

18“ስለ ሁላችሁ አልናገርም፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ፦ ‘እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።

19በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፥ ከአሁን ጀምሬ አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።

20እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”

21ኢየሱስ ይህን ብሎ በመንፈሱ ታወከ መስክሮም፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል፡” አለ።

22ደቀ መዛሙርቱ ስለ ማን እንደ ተናገረ አመንትተው እርስ በርሳቸው ተያዩ።

23ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤

24ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ እርሱን ጠቅሶ፦ “ስለማን እንደ ተናገረ ንገረን” አለው።

25እርሱም በኢየሱስ ደረት እንዲህ ተጠግቶ፦ “ጌታ ሆይ፥ ማን ነው?” አለው።

26ኢየሱስም፦ “እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” ብሎ መለሰለት። ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው።

27ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት። እንግዲህ ኢየሱስ፦ “የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ” አለው።

28ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም፤

29ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦ “ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥” ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና።

30እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ።

31ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚአብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ፤

32እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል፡ ወዲያውም ያከብረዋል።

33ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድም፦ ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አይቻላችሁም’ እንዳልኋቸው፥ አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ።

34እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

35እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”

36ስምዖን ጴጥሮስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄዳለህ?” አለው። ኢየሱስም፦ “ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፥ ነገር ግን በኋላ ትከተለኛለህ፡” ብሎ መለሰለት።

37ጴጥሮስም፦ “ጌታ ሆይ፥ አሁን ልከተልህ አለመቻሌ ስለ ምንድር ነው? ነፍሴን ስንኳ ስለ አንተ እሰጣለሁ፡” አለው።

38ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “ነፍስህን ስለ እኔ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም።”

ማብራሪያ

ዮሐንስ 13:1-17

ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ዓለም ውስጥ የራሱ የሆኑ ሰዎች አሉት፤ እርሱም በውድ ዋጋ ገዝቷቸዋል፥ ለራሱም ለይቷቸዋል፤ እነርሱም ልዩ ሕዝብ ሆነው ራሳቸውን ለእርሱ አስገዝተዋል። ክርስቶስ የሚወዳቸውን እስከ መጨረሻው ይወዳቸዋል። እውነተኛ አማኝን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለይ የሚችል ምንም ነገር የለም። ሰዓታችን መቼ እንደሚመጣ አናውቅም፤ ስለዚህም ለዘወትር ዝግጅት ልናደርገው የሚገባንን ነገር በፍጹም ችላ ልንለው አይገባም። ዲያብሎስ ወደ ሰዎች ልብ እንዴት እንደሚገባ በትክክል መናገር አንችልም። ነገር ግን አንዳንድ ኃጢአቶች እጅግ በጣም ኃጢአተኞች ከመሆናቸው የተነሳ፣ ከዓለምና ከሥጋ የሚመጣ ፈተናም የሌላቸው በመሆናቸው፣ በቀጥታ ከሰይጣን የመጡ መሆናቸው ግልጽ ነው። ኢየሱስ የተማሪዎቹን እግር ያጠበው፣ የእግዚአብሔርን ክብርና የወንድሞቻችንን መልካም ነገር የምናደርግበትን ማንኛውንም ነገር ከክብራችን የሚያንስ አድርገን እንዳናስብ ሊያስተምረን ነው። ወደ ግዴታችን መቅረብ አለብን፤ ማድረግ ያለብንን ነገር እንዳንሠራ የሚያግደንንም ሁሉ አስወግደን መጣል አለብን። ክርስቶስ የተማሪዎቹን እግር ያጠበው የመንፈሳዊውን መታጠብ ዋጋ፥ ነፍስንም ከኃጢአት ርኩሰት የመንጻት አስፈላጊነትን ሊያሳያቸው ነው። ጌታችን ኢየሱስ አሁን ባለው ጊዜ ትርጉማቸውን የራሱ ደቀ መዛሙርት እንኳን የማያውቁትን ብዙ ነገሮችን ያደርጋል፤ ነገር ግን በኋላ ያውቃሉ። በመጨረሻ ላይ ደግሞ እጅግ አስቸጋሪ በሚመስሉ ክስተቶች ውስጥ የነበረውን ደግነት እናያለን። የወንጌልን ጥሪ ማራቅ ትህትና ሳይሆን አለማመን ነው፤ ለእኛ ለመሆን እንደማይገባን በጣም የበዛ ወይም እውነት ለመሆን እጅግ በጣም መልካም ዜና እንደሆነ አድርጎ ማሰብ። በክርስቶስ በመንፈስ የታጠቡት ሁሉ፣ እነርሱ ብቻ በክርስቶስ ድርሻ አላቸው። ክርስቶስ የራሱ ያደረጋቸውና ያዳናቸው ሁሉንም ያጸድቃል ያቀድሳል። ጴጥሮስ ከመገዛትም በላይ፣ በክርስቶስ ሊታጠብ ለመነ። የጌታችን የኢየሱስን የማንጻት ጸጋና የዚያንም ሙሉ በሙሉ የሆነ ውጤት፣ በእጆቹና በራሱ ላይ ጭምር ለማግኘት ምንኛ ቀናተኛ ነበር! በእውነት ሊቀደሱ የሚፈልጉ፣ ሙሉ በሙሉ ሊቀደሱ ይፈልጋሉ፤ አጠቃላይ ሰውነታቸውን ከክፍሎቹና ከኃይሎቹ ሁሉ ጋር ንጹሕ እንዲሆን ይፈልጋሉ። እውነተኛ አማኝ ክርስቶስን ለመዳኑ ሲቀበል በዚህ መንገድ ይታጠባል። እንግዲያውስ በጸጋ በጽድቅ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች የዕለት ተዕለት ጥንቃቄ ምን መሆን እንዳለበት ተመልከቱ፤ እርሱም እግራቸውን ማጠብ ነው፤ ከዕለታዊ ጥፋት ራሳቸውን ማንጻት፣ እንዲሁም የሚያረክሳቸውን ነገር ሁሉ መጠበቅ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV It was just before the Passover Feast. Jesus knew that the time had come for him to leave this world and go to the Fath… English BCV ኢየሱስ ቅድሚ በዓል ፋሲካ፥ ካብዝ ዓለም እዙይ፥ ናብ ኣብ፥ ዝኸደላ ሰዓት ከም ዝበፅሐት ፈሊጡ፥ ነቶም ዘፍቀሮም ኣብዛ ዓለም እዚኣ ዘለዉ ናቱ፥ ክሳዕ መወዳእታ ኣፍቀሮም። ትግርኛ GAZBIB Ayyaana Faasiikaa dura, Yesus biyya lafaa kana keessaa gara abbaa dhaquudhaaf yeroon isaa akka ga'e in beeke; inni biyy… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምቅድመ በዓለ ፋሲካ ሶበ ኮነ የአምር እግዚእ ኢየሱስ ከመ በጽሐ ጊዜሁ ከመ ይፈልስ እምዝንቱ ዓለም ወየሐውር ኀበ አብ። ዘፈነዎ ወአፍቀሮሙ ለእሊኣሁ እለ ውስተ ዓለም ወለዝሉፉ አፍቀሮሙ። giz GAZGAZ Ayyaana Faasiikaa dura, Yesus biyya lafaa kana keessaa gara abbaa dhaquudhaaf yeroon isaa akka ga'e in beeke; inni biyy… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ቅድሚ በዓል ፋሲካ፥ ካብዝ ዓለም እዙይ፥ ናብ ኣብ፥ ዝኸደላ ሰዓት ከም ዝበፅሐት ፈሊጡ፥ ነቶም ዘፍቀሮም ኣብዛ ዓለም እዚኣ ዘለዉ ናቱ፥ ክሳዕ መወዳእታ ኣፍቀሮም። ትግርኛ AMHNIV ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው። አማርኛ SWAHSUV Basi, kabla ya sikukuu ya Pasaka, Yesu, hali akijua ya kuwa saa yake imefika, atakayotoka katika ulimwengu kwenda kwa B… Kiswahili