ትንቢተ ኤርምያስ 45

AMHEVGአማርኛ5 ጥቅሶች1:02 አዳምጥ
አዳምጥ 1:02 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ እነዚህን ቃሎች ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

2ባሮክ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፦

3አንተ፦ እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም፡ ብለሃል።

4እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሠራሁትን አፈርሳለሁ፥ የተከልሁትንም እነቅላለሁ፤ ይኸውም በምድር ሁሉ ነው።

5ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልገው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።

ማብራሪያ

፵፭፡፩-፭ ባሮክን የሚያበረታታ መልእክት።

ባሮክ የኤርምያስን ትንቢቶች በመጻፍና በማንበብ ተሰማርቶ ነበር (ኤር ፴፮ን ተመልከት)፣ እናም በዚህም ምክንያት በንጉሡ ማስፈራሪያ ደርሶበት ነበር። በሃይማኖት ሕይወት ገና የጀመሩ ወጣቶች በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን አገልግሎት ሲጀምሩ በሚያጋጥሟቸው ጥቃቅን ችግሮች በቀላሉ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ አላቸው። እነዚህ ቅሬታዎችና ፍራቻዎች የመጡት ከኃጢአተኛ ተፈጥሮው ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is what Jeremiah the prophet told Baruch son of Neriah in the fourth year of Jehoiakim son of Josiah king of Judah… English BCV ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፥ ንሱውን ነዘን ቃላት እዚኣተን፥ ካብ ኣፍ ኤርሚያስ ክፅሕፈን እንተሎ፥ ነቢይ ኤርሚያስ ንባሮክ ወዲ ኔሪ ዝነገሮ ቓል እዙ… ትግርኛ GAZBIB Ani Ermiyaas, Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaa isaatti, Baaruk ilma Neriiyaatti n… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር ዘነገሮ ኤርምያስ ነቢይ ለባሮክ ወልደ ኔርዩ አመ ጸሐፈ እሎንተ ቃላት ውስተ መጽሐፍ እምአፈ ኤርምያስ ነብይ በራብዕ ዓመተ መንግሥቱ ለኢዮአቄም ወልደ ኢዮስያስ ንጉሠ ይሁዳ። giz GAZGAZ Ani Ermiyaas, Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaa isaatti, Baaruk ilma Neriiyaatti n… Afaan Oromoo BCV aksum ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፥ ንሱውን ነዘን ቃላት እዚኣተን፥ ካብ ኣፍ ኤርሚያስ ክፅሕፈን እንተሎ፥ ነቢይ ኤርሚያስ ንባሮክ ወዲ ኔሪ ዝነገሮ ቓል እዙ… ትግርኛ AMHNIV በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት፣ ኤርምያስ በቃል የነገረውን ባሮክ በብራና ላይ ከጻፈ በኋላ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የተናገረው ይህ … አማርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo ambalo Yeremia, nabii, alimwambia Baruku, mwana wa Neria, alipoyaandika maneno haya katika kitabu kwa k… Kiswahili