ትንቢተ ኤርምያስ 45

AMHNIVአማርኛ5 ጥቅሶች1:11 አዳምጥ
አዳምጥ 1:11 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት፣ ኤርምያስ በቃል የነገረውን ባሮክ በብራና ላይ ከጻፈ በኋላ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የተናገረው ይህ ነው፤

2“ባሮክ ሆይ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፤

3አንተ፣ ‘እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜያለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም’ ብለሃል።”

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በምድር ሁሉ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልሁትን እነቅላለሁ።

5ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ”

ማብራሪያ

፵፭፡፩-፭ ባሮክን የሚያበረታታ መልእክት።

ባሮክ የኤርምያስን ትንቢቶች በመጻፍና በማንበብ ተሰማርቶ ነበር (ኤር ፴፮ን ተመልከት)፣ እናም በዚህም ምክንያት በንጉሡ ማስፈራሪያ ደርሶበት ነበር። በሃይማኖት ሕይወት ገና የጀመሩ ወጣቶች በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን አገልግሎት ሲጀምሩ በሚያጋጥሟቸው ጥቃቅን ችግሮች በቀላሉ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ አላቸው። እነዚህ ቅሬታዎችና ፍራቻዎች የመጡት ከኃጢአተኛ ተፈጥሮው ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ እነዚህን ቃሎች ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። አማርኛ ENGNIV This is what Jeremiah the prophet told Baruch son of Neriah in the fourth year of Jehoiakim son of Josiah king of Judah… English BCV ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፥ ንሱውን ነዘን ቃላት እዚኣተን፥ ካብ ኣፍ ኤርሚያስ ክፅሕፈን እንተሎ፥ ነቢይ ኤርሚያስ ንባሮክ ወዲ ኔሪ ዝነገሮ ቓል እዙ… ትግርኛ GAZBIB Ani Ermiyaas, Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaa isaatti, Baaruk ilma Neriiyaatti n… Afaan Oromoo BCV GIZ ነገር ዘነገሮ ኤርምያስ ነቢይ ለባሮክ ወልደ ኔርዩ አመ ጸሐፈ እሎንተ ቃላት ውስተ መጽሐፍ እምአፈ ኤርምያስ ነብይ በራብዕ ዓመተ መንግሥቱ ለኢዮአቄም ወልደ ኢዮስያስ ንጉሠ ይሁዳ። giz GAZGAZ Ani Ermiyaas, Yehoyaaqiim ilmi Yosiyaas biyya Yihudaa irratti mo'ee waggaa afuraffaa isaatti, Baaruk ilma Neriiyaatti n… Afaan Oromoo BCV aksum ኢዮኣቄም ወዲ ኢዮስያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ራብዐይቲ ዓመቱ፥ ንሱውን ነዘን ቃላት እዚኣተን፥ ካብ ኣፍ ኤርሚያስ ክፅሕፈን እንተሎ፥ ነቢይ ኤርሚያስ ንባሮክ ወዲ ኔሪ ዝነገሮ ቓል እዙ… ትግርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo ambalo Yeremia, nabii, alimwambia Baruku, mwana wa Neria, alipoyaandika maneno haya katika kitabu kwa k… Kiswahili