ትንቢተ ኤርምያስ 28

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:26 አዳምጥ
አዳምጥ 3:26 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንደ ነገሠ በዐራተኛው ዓመት፣ አምስተኛ ወር፣ የገባዖኑ ሰው የዓዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፤

2“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ የጫነባችሁን ቀንበር እሰብራለሁ፤

3የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከእግዚአብሔር ቤት ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መልሼ አመጣለሁ።

4የይሁዳንም ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ ሌሎች ከይሁዳ ወደ ባቢሎን ተማርከው የተወሰዱትንም ሁሉ ወደዚህ ስፍራ እመልሳለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ የባቢሎን ንጉሥ የጫነባቸውን ቀንበር እሰብራለሁና።’ ”

5ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት፣ ለነቢዩ ለሐናንያ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦

6“አሜን፤ እግዚአብሔር ያድርገው፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ሁሉ፣ ተማርከው የተወሰዱትንም ምርኮኞች ሁሉ ከባቢሎን በመመለስ፣ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ቃል ይፈጽም።

7ነገር ግን ለአንተም ለዚህም ሕዝብ የምናገረውን ቃል ስማ፤

8ከአንተና ከእኔ በፊት ጥንት የተነሡ ነቢያት፣ በብዙ አገሮችና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ጦርነት፣ ስለ ጥፋትና ስለ መቅሠፍት ትንቢት ተናግረዋል።

9ነገር ግን ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይ እግዚአብሔር በእውነት እንደላከው የሚታወቀው የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም ነው።

10ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ ዐንገት ወስዶ ሰበረው፤

11በሕዝቡም ፊት፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የና ቡከደናፆርን ቀንበር ከሕዝቡ ሁሉ ጫንቃ ላይ ልክ እንደዚህ እሰብራለሁ’ አለ። በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።

12ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ከሰበረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

13“ሄደህ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አንተ የዕንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤ እኔ ግን በምትኩ የብረት ቀንበር እሠራለሁ።

14የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲያገለግሉ፣ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ በዱር አራዊት ላይ እንኳ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።’ ”

15ነቢዩ ኤርምያስም ለነቢዩ ሐናንያ እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፤ ስማ! እግዚአብሔር ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል፤

16ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅ ተናግረሃልና፣ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።”

17ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።

ማብራሪያ

28:1-9 ሐናንያ የሐሰት ትንቢት ተናገረ። እዚህ ላይ አይሁድን ንስሐ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ የሚያበረታታ አንድም የምክር ቃል የለም። በእግዚአብሔር ስም ጊዜያዊ ምህረቶችን ቢቀጥርም፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከምድራዊ በረከቶች ጋር ስለሚሰጣቸው መንፈሳዊ ምህረቶች ግን ምንም አልጠቀሰም። ኤርምያስ በእነርሱ ላይ ትንቢት ቢናገርም፣ ይህ ለሕዝቡ የጸለየበት የመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም። ሐናንያ የሐሰት ነቢይ መሆኑን ለማረጋገጥ በተፈጸመው ነገር ላይ ተመካ። ሰላምንና ብልጽግናን ብቻ የተናገረ ነቢይ፣ ሆን ብለው በሚሠሩት ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሞገስ እንዳያቆሙ ሳያክሉ፣ የሐሰት ነቢይ ሆኖ ይረ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያም ዓመት በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ… አማርኛ ENGNIV In the fifth month of that same year, the fourth year, early in the reign of Zedekiah king of Judah, the prophet Hanani… English BCV በታ ዓመት እቲኣ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ሓምሸይቲ ወርሒ ናይታ ራብዐይቲ ዓመት፥ ሃናንያ፥ ወዲ ነቢይ ዓዙር በዓል ገባዖን፥ ኣብ ቤተ መቕደስ፥ ኣብ ቅድሚ እቶም ካህናትን ኵሉ … ትግርኛ GAZBIB Zedeqiiyaan mootii Yihudaa ta'ee waggaa afuraffaa keessa, waggichattiis ji'a shanaffaatti Hanaaniiyaan raajichi ilmi Az… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ኮነ በውእቱ ዓመት በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ ለሴዴቅያስ ንጉሥ ይሁዳ በዓመት ራብዒት በኃምስ ወርኅ፤ ይቤለኒ ሐናንያ ወልደ ሐዞር ሐሳዊ ነቢይ ዘገባኦን በቤተ እግዚአብሔር በቅድመ ካህና… giz GAZGAZ Zedeqiiyaan mootii Yihudaa ta'ee waggaa afuraffaa keessa, waggichattiis ji'a shanaffaatti Hanaaniiyaan raajichi ilmi Az… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ዓመት እቲኣ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ሓምሸይቲ ወርሒ ናይታ ራብዐይቲ ዓመት፥ ሃናንያ፥ ወዲ ነቢይ ዓዙር በዓል ገባዖን፥ ኣብ ቤተ መቕደስ፥ ኣብ ቅድሚ እቶም ካህናትን ኵሉ … ትግርኛ SWAHSUV Ikawa, katika mwaka ule ule, mwanzo wa kutawala kwake Sedekia, mfalme wa Yuda, mwaka wa nne, mwezi wa tano, Hanania, mw… Kiswahili