ትንቢተ ኤርምያስ 28

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:04 አዳምጥ
አዳምጥ 3:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያም ዓመት በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦

2የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይናገራል፦ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር ሰብሬአለሁ።

3የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳትን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳታለሁ፤

4ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።

5ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ለሐናንያ ተናገረ።

6ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ትንቢት ይፈጽም።

7ነገር ግን በጆሮህና በሕዝብ ሁሉ ጆሮ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ፤

8ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነቢያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነፈርም ትንቢት ተናገሩ።

9ስለ ሰላም የተናገረ ነቢይ፥ የነቢዩ ቃል በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእውነት የሰደደው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።

10ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ሰበረው።

11ሐናንያም በሕዝብ ሁሉ ፊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ በሁለት ዓመት ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ፥ አለ። ነቢዩም ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።

12ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ከሰበረ በኋላ፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

13ሂድ፥ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨትን ቀንበር ሰብረሃል፥ እኔ ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር እሠራለሁ።

14የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፥ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።

15ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ ሐናንያ ሆይ፥ ስማ፤ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም።

16ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ፡ አለው።

17ነቢዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።

ማብራሪያ

28:1-9 ሐናንያ የሐሰት ትንቢት ተናገረ። እዚህ ላይ አይሁድን ንስሐ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ የሚያበረታታ አንድም የምክር ቃል የለም። በእግዚአብሔር ስም ጊዜያዊ ምህረቶችን ቢቀጥርም፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከምድራዊ በረከቶች ጋር ስለሚሰጣቸው መንፈሳዊ ምህረቶች ግን ምንም አልጠቀሰም። ኤርምያስ በእነርሱ ላይ ትንቢት ቢናገርም፣ ይህ ለሕዝቡ የጸለየበት የመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም። ሐናንያ የሐሰት ነቢይ መሆኑን ለማረጋገጥ በተፈጸመው ነገር ላይ ተመካ። ሰላምንና ብልጽግናን ብቻ የተናገረ ነቢይ፣ ሆን ብለው በሚሠሩት ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሞገስ እንዳያቆሙ ሳያክሉ፣ የሐሰት ነቢይ ሆኖ ይረ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the fifth month of that same year, the fourth year, early in the reign of Zedekiah king of Judah, the prophet Hanani… English BCV በታ ዓመት እቲኣ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ሓምሸይቲ ወርሒ ናይታ ራብዐይቲ ዓመት፥ ሃናንያ፥ ወዲ ነቢይ ዓዙር በዓል ገባዖን፥ ኣብ ቤተ መቕደስ፥ ኣብ ቅድሚ እቶም ካህናትን ኵሉ … ትግርኛ GAZBIB Zedeqiiyaan mootii Yihudaa ta'ee waggaa afuraffaa keessa, waggichattiis ji'a shanaffaatti Hanaaniiyaan raajichi ilmi Az… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ኮነ በውእቱ ዓመት በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ ለሴዴቅያስ ንጉሥ ይሁዳ በዓመት ራብዒት በኃምስ ወርኅ፤ ይቤለኒ ሐናንያ ወልደ ሐዞር ሐሳዊ ነቢይ ዘገባኦን በቤተ እግዚአብሔር በቅድመ ካህና… giz GAZGAZ Zedeqiiyaan mootii Yihudaa ta'ee waggaa afuraffaa keessa, waggichattiis ji'a shanaffaatti Hanaaniiyaan raajichi ilmi Az… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ዓመት እቲኣ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ሓምሸይቲ ወርሒ ናይታ ራብዐይቲ ዓመት፥ ሃናንያ፥ ወዲ ነቢይ ዓዙር በዓል ገባዖን፥ ኣብ ቤተ መቕደስ፥ ኣብ ቅድሚ እቶም ካህናትን ኵሉ … ትግርኛ AMHNIV በዚያው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንደ ነገሠ በዐራተኛው ዓመት፣ አምስተኛ ወር፣ የገባዖኑ ሰው የዓዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፤ አማርኛ SWAHSUV Ikawa, katika mwaka ule ule, mwanzo wa kutawala kwake Sedekia, mfalme wa Yuda, mwaka wa nne, mwezi wa tano, Hanania, mw… Kiswahili