ትንቢተ ኤርምያስ 24

AMHEVGአማርኛ10 ጥቅሶች2:13 አዳምጥ
አዳምጥ 2:13 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ እግዚአብሔር አሳየኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር።

2በአንደኛይቱ ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረባት፤ በሁለተኛይቱ ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረባት።

3እግዚአብሔርም፦ ኤርምያስ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው፡ አልሁ።

4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

5የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጐነት እመለከተዋለሁ።

6ዓይኔንም ለበጐነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።

7እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።

8እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቅሬታ በግብፅም አገር የሚቀመጡትን እጥላቸዋለሁ።

9በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።

10ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።

ማብራሪያ

24:1-10

ጥሩና መጥፎ በለሶች በምርኮ ያሉትን አይሁድና በገዛ ምድራቸው የቀሩትን ይወክላሉ። ነቢዩ ሁለት የቅድሚያ ፍሬዎች መባ የሆኑ የበለስ ቅርጫቶች ከመቅደሱ ፊት ሲቀመጡ አየ። በአንድ ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች እጅግ በጣም ጥሩ ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት ደግሞ እጅግ በጣም መጥፎ ነበሩ። ከክፉ ሰው የባሰ ፍጥረት ማን ነው? ከእግዚአብሔር ሰውስ የበለጠ ዋጋ ያለው ማነው? ይህ ራእይ በምርኮ ላሉት መልካም መመለስን በማረጋገጥ መንፈሳቸውን ከፍ ለማድረግ፤ እንዲሁም ገና በኢየሩሳሌም ላሉት ትዕቢተኛና ደኅንነት ይሰማቸው የነበሩትን ደግሞ እጅግ አስከፊ ምርኮን በማረጋገጥ ለማዋረድና ለማንቃት ነበር።

መልካሞቹ በለሶች ታማኞቹን ምርኮኞች ይወክላሉ። በእኛ ፊት ባለው ነገር የእግዚአብሔርን ፍቅር ወይም ጥላቻ መወሰን አንችልም። ቀድሞ የሚመጣ መከራ አንዳንድ ጊዜ ለበጎ ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV After Jehoiachin son of Jehoiakim king of Judah and the officials, the craftsmen and the artisans of Judah were carried… English BCV ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ንኢኮንያን፥ ወዲ ኢዮኣቄም ንጉስ ይሁዳ፥ ምስ ኣሕሉቕ ይሁዳን ሃነፅትን ሰራሕቲ ሓፃውንን፥ ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ምስ ወሰዶም፥ እንሆ፥ እግዚኣብሄር፥ … ትግርኛ GAZBIB Ergasiis Waaqayyo, guuboo ija harbuu baatu lama balbala mana qulqullummaa dura kan kaa'aman anatti in argisiise; kunis … Afaan Oromoo BCV GIZ ወአርአየኒ እግዚአብሔር ፪ አዕፁቀ በለስ ንቡራነ ቅድመ ቤተ እግዚአብሔር እምድኅረ አፍለሶ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን ለኢኮንያን ወልደ ኢዮአቄም ንጉሠ ይሁዳ ወለመላእክተ ይሁዳኒ ወለኪነቶሂ … giz GAZGAZ Ergasiis Waaqayyo, guuboo ija harbuu baatu lama balbala mana qulqullummaa dura kan kaa'aman anatti in argisiise; kunis … Afaan Oromoo BCV aksum ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ንኢኮንያን፥ ወዲ ኢዮኣቄም ንጉስ ይሁዳ፥ ምስ ኣሕሉቕ ይሁዳን ሃነፅትን ሰራሕቲ ሓፃውንን፥ ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ምስ ወሰዶም፥ እንሆ፥ እግዚኣብሄር፥ … ትግርኛ AMHNIV የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ የኢዮአቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም የይሁዳን አናጺዎችና ብረት ቀጥቃጮች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው በኋላ፣ እ… አማርኛ SWAHSUV Bwana akanionyesha, na tazama, vikapu viwili vya tini, vimewekwa mbele ya hekalu la Bwana, baada ya Nebukadreza, mfalme… Kiswahili