ትንቢተ ኤርምያስ 24

AMHNIVአማርኛ10 ጥቅሶች2:32 አዳምጥ
አዳምጥ 2:32 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ የኢዮአቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም የይሁዳን አናጺዎችና ብረት ቀጥቃጮች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር ሁለት ቅርጫት በለስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጦ አሳየኝ።

2አንዱ ቅርጫት፣ ቶሎ የደረሰ ፍሬ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፣ በሌላው ቅርጫት ግን ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበላ የማይቻል እጅግ መጥፎ በለስ ነበረበት።

3እግዚአብሔርም፣ “ኤርምያስ ሆይ፤ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፣ “በለስን አያለሁ፤ ጥሩ የሆነው እጅግ መልካም ነው፤ የተበላሸው ግን እጅግ መጥፎ በመሆኑ ሊበላ የማይችል ነው” አልሁ።

4እንደ ገናም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤

5“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎናውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳ ምርኮ በመልካም አስበዋለሁ።

6ዐይኔን ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።

7እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።

8“ ‘ነገር ግን ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበላ እንደ ማይቻለው እንደ መጥፎ በለስ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የቀሩትንም ሆነ በግብፅ የሚኖሩትን፣ እንዲሁ አደርግባቸዋለሁ።

9በምድር መንግሥታት ሁሉ ፊት የሚያስጸይፉና የሚሰደቡ ይሆናሉ፤ በምበትናቸውም ስፍራ ሁሉ ለማላገጫና ለመተረቻ፣ ለመሣለቂያና ለርግማን አደርጋቸዋለሁ።

10ለእነርሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ ሰይፍ፣ ራብና መቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ።

ማብራሪያ

24:1-10

ጥሩና መጥፎ በለሶች በምርኮ ያሉትን አይሁድና በገዛ ምድራቸው የቀሩትን ይወክላሉ። ነቢዩ ሁለት የቅድሚያ ፍሬዎች መባ የሆኑ የበለስ ቅርጫቶች ከመቅደሱ ፊት ሲቀመጡ አየ። በአንድ ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች እጅግ በጣም ጥሩ ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት ደግሞ እጅግ በጣም መጥፎ ነበሩ። ከክፉ ሰው የባሰ ፍጥረት ማን ነው? ከእግዚአብሔር ሰውስ የበለጠ ዋጋ ያለው ማነው? ይህ ራእይ በምርኮ ላሉት መልካም መመለስን በማረጋገጥ መንፈሳቸውን ከፍ ለማድረግ፤ እንዲሁም ገና በኢየሩሳሌም ላሉት ትዕቢተኛና ደኅንነት ይሰማቸው የነበሩትን ደግሞ እጅግ አስከፊ ምርኮን በማረጋገጥ ለማዋረድና ለማንቃት ነበር።

መልካሞቹ በለሶች ታማኞቹን ምርኮኞች ይወክላሉ። በእኛ ፊት ባለው ነገር የእግዚአብሔርን ፍቅር ወይም ጥላቻ መወሰን አንችልም። ቀድሞ የሚመጣ መከራ አንዳንድ ጊዜ ለበጎ ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ እግዚአብሔር አሳ… አማርኛ ENGNIV After Jehoiachin son of Jehoiakim king of Judah and the officials, the craftsmen and the artisans of Judah were carried… English BCV ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ንኢኮንያን፥ ወዲ ኢዮኣቄም ንጉስ ይሁዳ፥ ምስ ኣሕሉቕ ይሁዳን ሃነፅትን ሰራሕቲ ሓፃውንን፥ ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ምስ ወሰዶም፥ እንሆ፥ እግዚኣብሄር፥ … ትግርኛ GAZBIB Ergasiis Waaqayyo, guuboo ija harbuu baatu lama balbala mana qulqullummaa dura kan kaa'aman anatti in argisiise; kunis … Afaan Oromoo BCV GIZ ወአርአየኒ እግዚአብሔር ፪ አዕፁቀ በለስ ንቡራነ ቅድመ ቤተ እግዚአብሔር እምድኅረ አፍለሶ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን ለኢኮንያን ወልደ ኢዮአቄም ንጉሠ ይሁዳ ወለመላእክተ ይሁዳኒ ወለኪነቶሂ … giz GAZGAZ Ergasiis Waaqayyo, guuboo ija harbuu baatu lama balbala mana qulqullummaa dura kan kaa'aman anatti in argisiise; kunis … Afaan Oromoo BCV aksum ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ንኢኮንያን፥ ወዲ ኢዮኣቄም ንጉስ ይሁዳ፥ ምስ ኣሕሉቕ ይሁዳን ሃነፅትን ሰራሕቲ ሓፃውንን፥ ካብ ኢየሩሳሌም ማሪኹ ናብ ባቢሎን ምስ ወሰዶም፥ እንሆ፥ እግዚኣብሄር፥ … ትግርኛ SWAHSUV Bwana akanionyesha, na tazama, vikapu viwili vya tini, vimewekwa mbele ya hekalu la Bwana, baada ya Nebukadreza, mfalme… Kiswahili