ትንቢተ ኤርምያስ 21

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች3:01 አዳምጥ
አዳምጥ 3:01 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።

2ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ፦ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል፡ ብሎ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ነው።

3ኤርምያስም እንዲህ አላቸው፦ ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦

4የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ፥ እነዚያንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ።

5እኔም በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።

6በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፥ በጽኑም ቸነፈር ይሞታሉ።

7ከዚህ በኋላ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።

8ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ።

9በዚህች ከተማ ውስጥ የሚዘገይ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል፥ ነፍሱም ምርኮ ትሆንለታለች።

10ለመልካም ሳይሆን ለክፋ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፥ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።

11የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

12የዳዊት ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።

13እነሆ፥ በሸለቆው ውስጥ በሜዳ ላይም ባለው አምባ የምትቀመጪ ሆይ፥ እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ በእኛ ላይ የሚወርድ ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ፥ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤

14እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፤ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።

ማብራሪያ

21:1-10 ከበባው ሲጀመር፣ ንጉሥ ጽድቅያስ ስለ ሁኔታው ኤርምያስን ለመጠየቅ ላከ። በመከራና በችግር ጊዜያት ሰዎች ብዙ ጊዜ በሌላ ጊዜ የሚንቋቸውንና የሚቃወሟቸውን ሰዎች ሊመክሯቸውና ሊጸልዩላቸው ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ከቅጣት መዳንን እንጂ ሌላን አይሹም። አማኞች ባለመታዘዝ ሲጸኑና በውጫዊ መብቶቻቸው ላይ በመታበይ ሲቀጥሉ፣ ጌታ በግልጽ ጠላቶቹን በእነርሱ ላይ እንደሚያሳካላቸው ይነገራቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The word came to Jeremiah from the Lord when King Zedekiah sent to him Pashhur son of Malkijah and the priest Zephaniah… English BCV ናይ ይሁዳ ንጉስ ሴዴቅያስ፥ ንጳስኮር ወዲ መልክያን ነቲ ኻህን ሶፎንያስ ካህን መኣስያን “ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ‘ክዋግአኩም እየ’ ይብል ኣሎ እሞ፥ ምናልባሽ እግዚኣብሄር ከም ኵሉ ተኣ… ትግርኛ GAZBIB Bara Zedeqiiyaan mootichi Phashhur ilma Malkiiyaa fi Sefaaniyaa lubicha ilma Ma'aseyaa gara Ermiyaasitti erge, dubbiin … Afaan Oromoo BCV GIZ ቃለ ዘኮነ ኀበ ኤርምያስ እምኀበ እግዚአብሔር፤ giz GAZGAZ Bara Zedeqiiyaan mootichi Phashhur ilma Malkiiyaa fi Sefaaniyaa lubicha ilma Ma'aseyaa gara Ermiyaasitti erge, dubbiin … Afaan Oromoo BCV aksum ናይ ይሁዳ ንጉስ ሴዴቅያስ፥ ንጳስኮር ወዲ መልክያን ነቲ ኻህን ሶፎንያስ ካህን መኣስያን “ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎን ‘ክዋግአኩም እየ’ ይብል ኣሎ እሞ፥ ምናልባሽ እግዚኣብሄር ከም ኵሉ ተኣ… ትግርኛ AMHNIV የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ጳስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበ… አማርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo lililomjia Yeremia, kutoka kwa Bwana, hapo mfalme Sedekia alipompelekea Pashuri, mwana wa Malkiya, na S… Kiswahili