ትንቢተ ኤርምያስ 20

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:38 አዳምጥ
አዳምጥ 3:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ።

2ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን መታው፥ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው በእግር ግንድ ውስጥ አኖረው።

3በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዓይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።

5የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያፈልሱአቸዋል።

6አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።

7አቤቱ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል።

8በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።

9እኔም፦ የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም፡ ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።

10የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን፡ ይላሉ።

11እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ።

12አቤቱ፥ ጻድቅን የምትመረምር ኵላሊትንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ክርክሬን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ለይ።

13ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፤ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።

14የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።

15ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል ብሎ ለአባቴ የምሥራች ነግሮ ደስ ያሰኘው ሰው የተረገመ ይሁን።

16ያም ሰው እግዚአብሔር ሳይጸጸት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤

17እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና።

18ድካምንና ጣርን አይ ዘንድ ዘመኔም በእፍረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማኅፀን ወጣሁ?

ማብራሪያ

ኤርምያስ 20:1-6

ጳስኩር ኤርምያስን መታውና በመቆሚያ አሰረው። እግዚአብሔር ቃል በአፉ እስኪከትለት ድረስ ኤርምያስ ዝም አለ። ይህን ለማረጋገጥ፣ ጳስኩር “በዙሪያው ሁሉ ፍርሃት” የሚል ስም ተሰጠው። ይህ የሚያመለክተው ሰውዬው በጭንቀት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በፍጹም ተስፋ መቁረጥ ውስጥም እንደሆነ፤ አደጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ከየአቅጣጫው ፍርሃት እንደያዘው ነው። ክፉዎች ፍርሃት በሌለበት ስፍራም ቢሆን በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ናቸው፤ እግዚአብሔር እጅግ ደፋር የሆነውን ኃጢአተኛ እንኳን ለራሱ ፍርሃት እንዲሆን ሊያደርግ ይችላልና። ከእግዚአብሔር ነቢያት ጥፋታቸውን የማይሰሙት፣ ከህሊናቸው እንዲሰሙ ይገደዳሉ። እንዲህ ለራሱ አስፈሪ የሆነ ሰው ምንኛ ጎስቋላ ነው! ጓደኞቹ ይተውታል፤ እግዚአብሔርም የመለኮታዊ ፍትህ መታሰቢያ እንዲሆን በጎስቋላነት እንዲኖር ይፈቅድለታል።

20:7-13 ነቢዩ ስለደረሰበት ስድብና ጉዳት ቅሬታውን ያቀርባል። ነገር ግን ቁጥር 7 እንዲህ ተብሎ ሊነበብ ይችላል፦ "አንተ አሳመንከኝ፣ እኔም ታመንኩኝ። አንተ ከእኔ ብርቱ ነበርህና በመንፈስህ ኃይል በእኔ ላይ አሸነፍከኝ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV When the priest Pashhur son of Immer, the chief officer in the temple of the Lord, heard Jeremiah prophesying these thi… English BCV ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ከም ዝተነበየ ምስ ሰምዑ፥ እቲ ኣብ ቤተ መቕደስ ሓለቓ ኾይኑ ዝተሸመ ጳስኮር፥ ወዲ ኻህን ኢሜር፥ ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ክንበ እንተሎ ሰምዐ፤ ትግርኛ GAZBIB Yeroo sana Phashhur lubichi ilmi Iimer geggeessituu hojii mana qulqullummaa inni ture, Ermiyaas raajii kana utuu dubbat… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሰምዐ ጳስኮር ወልደ ኤሞር ካህን እስመ ውእቱ ተሠይመ መኰንነ ለቤተ እግዚአብሔር እንዘ ይትኔበይ ኤርምያስ ዘ ነገረ። giz GAZGAZ Yeroo sana Phashhur lubichi ilmi Iimer geggeessituu hojii mana qulqullummaa inni ture, Ermiyaas raajii kana utuu dubbat… Afaan Oromoo BCV aksum ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ከም ዝተነበየ ምስ ሰምዑ፥ እቲ ኣብ ቤተ መቕደስ ሓለቓ ኾይኑ ዝተሸመ ጳስኮር፥ ወዲ ኻህን ኢሜር፥ ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ክንበ እንተሎ ሰምዐ፤ ትግርኛ AMHNIV በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አለቃ የነበረው፣ የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር እነዚህን ነገሮች ኤርምያስ እንደ ተነበየ በሰማ ጊዜ፣ አማርኛ SWAHSUV Basi Pashuri, mwana wa Imeri, kuhani, aliyekuwa msimamizi mkuu katika nyumba ya Bwana, alimsikia Yeremia alipokuwa akit… Kiswahili