ትንቢተ ኤርምያስ 19

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች3:23 አዳምጥ
አዳምጥ 3:23 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሂድ፥ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፥ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤

2በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፥

3እንዲህም በል፦ የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ነገር፥ እነሆ፥ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።

4ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና፥

5እኔም ያላዘዝሁትን ያልተናገርሁትንም ወደ ልቤም ያልገባውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አድርገው ለበኣል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና ስለዚህ፥

6እነሆ፥ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

7በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።

8ይህችንም ከተማ ለመደነቂያና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነቃል ከንፈሩንም ይመጥጣል።

9የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፥ ሁሉም ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።

10ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፥

11እንዲህም ትላቸዋለህ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።

12እንዲሁ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ አደርጋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ይህችንም ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋለሁ።

13የረከሱትም የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፥ እነዚያ በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፥ እንደ ቶፌት ስፍራ ይሆናሉ።

14ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ፦

15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።

ማብራሪያ

19:1-9

ነቢዩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ማስጠንቀቅ አለበት። ገዢዎችም ተገዢዎችም ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። ቅድስና የምድር ሁሉ ደስታ ያደረገው ያ ስፍራ፣ ኃጢአት ግን የምድር ሁሉ መወገዝያና እፍረት አደረገው። ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ የሚቻለው ወደ ምሕረቱ በመሸሽ ብቻ ነው።

19:10-15 የሸክላ ሠሪ ዕቃ ከደረቀ በኋላ ከተሰበረ ፈጽሞ ሊጠገን አይችልም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is what the Lord says: “Go and buy a clay jar from a potter. Take along some of the elders of the people and of th… English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፦ “ኪድ፤ ካብቲ ሰራሒ መሬት ሳርማ ዓድግ። ካብቶም ዓበይቲ ህዝብን ካብቶም ዓበይቲ ኻህናትንውን ንገሊኣቶም ምሳኻ ተማላእ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo wanta kanatti fufee jiru dubbatee,“Dhaqii nama suphee dha'u irraa cuggee tokko bitadhuu maanguddoota sabaa kee… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሑር ተሣየጥ ለከ ቀሡተ ልሕኵት ግብረ እደ ለብሐዊ፡ ወንሣእ እምውስተ ረበናቶሙ ለሕዝብ ወእም ረበናተ ካህናት። giz GAZGAZ Waaqayyo wanta kanatti fufee jiru dubbatee,“Dhaqii nama suphee dha'u irraa cuggee tokko bitadhuu maanguddoota sabaa kee… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፦ “ኪድ፤ ካብቲ ሰራሒ መሬት ሳርማ ዓድግ። ካብቶም ዓበይቲ ህዝብን ካብቶም ዓበይቲ ኻህናትንውን ንገሊኣቶም ምሳኻ ተማላእ። ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ታላላቅ የሆኑትን አንዳንዶቹን ይዘህ፣ አማርኛ SWAHSUV Bwana akasema hivi, Enenda ukanunue gudulia la mfinyanzi, ukachukue pamoja nawe baadhi ya wazee wa watu, na baadhi ya w… Kiswahili