ትንቢተ ኤርምያስ 20

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች4:07 አዳምጥ
አዳምጥ 4:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አለቃ የነበረው፣ የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር እነዚህን ነገሮች ኤርምያስ እንደ ተነበየ በሰማ ጊዜ፣

2ነቢዩ ኤርምያስን መታው፣ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።

3በማግስቱም ጳስኮር ኤርምያስን ከተጠረቀበት ግንድ አወጣው፤ ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ከእንግዲህ ማጎርሚሳቢብ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም፤

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ባልንጀሮችህን ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።

5የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ።

6ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ባልንጆሮችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”

7እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ።

8በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ።

9ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የእርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።

10“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።

11ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።

12ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጒዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁና ስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ።

13ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤ የችግረኛውን ነፍስ፣ ከክፉዎች እጅ ታድጎአልና።

14የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።

15“ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል” ብሎ፣ ለአባቴ የምሥራች የነገረ፣ ደስ ያሰኘውም ሰው የተረገመ ይሁን።

16ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣ እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤ በማለዳ ዋይታን፣ በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤

17እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣ ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣ ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና።

18ችግርና ሐዘንን ለማየት፣ ዘመኔንም በውርደት ለመፈጸም፣ ለምን ከማሕፀን ወጣሁ?

ማብራሪያ

ኤርምያስ 20:1-6

ጳስኩር ኤርምያስን መታውና በመቆሚያ አሰረው። እግዚአብሔር ቃል በአፉ እስኪከትለት ድረስ ኤርምያስ ዝም አለ። ይህን ለማረጋገጥ፣ ጳስኩር “በዙሪያው ሁሉ ፍርሃት” የሚል ስም ተሰጠው። ይህ የሚያመለክተው ሰውዬው በጭንቀት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በፍጹም ተስፋ መቁረጥ ውስጥም እንደሆነ፤ አደጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ከየአቅጣጫው ፍርሃት እንደያዘው ነው። ክፉዎች ፍርሃት በሌለበት ስፍራም ቢሆን በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ናቸው፤ እግዚአብሔር እጅግ ደፋር የሆነውን ኃጢአተኛ እንኳን ለራሱ ፍርሃት እንዲሆን ሊያደርግ ይችላልና። ከእግዚአብሔር ነቢያት ጥፋታቸውን የማይሰሙት፣ ከህሊናቸው እንዲሰሙ ይገደዳሉ። እንዲህ ለራሱ አስፈሪ የሆነ ሰው ምንኛ ጎስቋላ ነው! ጓደኞቹ ይተውታል፤ እግዚአብሔርም የመለኮታዊ ፍትህ መታሰቢያ እንዲሆን በጎስቋላነት እንዲኖር ይፈቅድለታል።

20:7-13 ነቢዩ ስለደረሰበት ስድብና ጉዳት ቅሬታውን ያቀርባል። ነገር ግን ቁጥር 7 እንዲህ ተብሎ ሊነበብ ይችላል፦ "አንተ አሳመንከኝ፣ እኔም ታመንኩኝ። አንተ ከእኔ ብርቱ ነበርህና በመንፈስህ ኃይል በእኔ ላይ አሸነፍከኝ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ። አማርኛ ENGNIV When the priest Pashhur son of Immer, the chief officer in the temple of the Lord, heard Jeremiah prophesying these thi… English BCV ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ከም ዝተነበየ ምስ ሰምዑ፥ እቲ ኣብ ቤተ መቕደስ ሓለቓ ኾይኑ ዝተሸመ ጳስኮር፥ ወዲ ኻህን ኢሜር፥ ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ክንበ እንተሎ ሰምዐ፤ ትግርኛ GAZBIB Yeroo sana Phashhur lubichi ilmi Iimer geggeessituu hojii mana qulqullummaa inni ture, Ermiyaas raajii kana utuu dubbat… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሰምዐ ጳስኮር ወልደ ኤሞር ካህን እስመ ውእቱ ተሠይመ መኰንነ ለቤተ እግዚአብሔር እንዘ ይትኔበይ ኤርምያስ ዘ ነገረ። giz GAZGAZ Yeroo sana Phashhur lubichi ilmi Iimer geggeessituu hojii mana qulqullummaa inni ture, Ermiyaas raajii kana utuu dubbat… Afaan Oromoo BCV aksum ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ከም ዝተነበየ ምስ ሰምዑ፥ እቲ ኣብ ቤተ መቕደስ ሓለቓ ኾይኑ ዝተሸመ ጳስኮር፥ ወዲ ኻህን ኢሜር፥ ኤርሚያስ እዝ ነገር እዙይ ክንበ እንተሎ ሰምዐ፤ ትግርኛ SWAHSUV Basi Pashuri, mwana wa Imeri, kuhani, aliyekuwa msimamizi mkuu katika nyumba ya Bwana, alimsikia Yeremia alipokuwa akit… Kiswahili