ትንቢተ ኢሳይያስ 54

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች2:51 አዳምጥ
አዳምጥ 2:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።

2የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።

3በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።

4አታፍሪምና አትፍሪ፤ አተዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።

5ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።

6እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፥ ይላል አምላክሽ።

7ጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፥ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።

8በጥቂት ቍጣ ለቅጽበት ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፥ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፥ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።

9ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።

10ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር።

11አንቺ የተቸገርሽ በዐውል ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።

12የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።

13ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።

14በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፥ አትፈሪምም፥ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።

15እነሆ፥ ይሰበሰባሉ፥ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚሰበሰቡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።

16እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።

17በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

54:1-5 ክርስትና ከመመሥረቱ በፊት ለረጅም ዘመናት በዓለም ላይ የሃይማኖት ዝቅተኛ ሁኔታን አስተውሉ። ነገር ግን ወንጌልን በመስበክ፣ እልፍ አዕላፋት ሰዎች ከጣዖታት ወደ ሕያው እግዚአብሔር ተመለሱ። ይህ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ የደስታ ምንጭ ነው። የቤተ ክርስቲያን ወሰኖች ሰፉ። በምድር ላይ ያላት ሁኔታ እንደ ድንኳን ወይም ማደሪያ ድንኳን ቀላልና ተንቀሳቃሽ ብትሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ግን እያደገች ያለች ሁኔታ ውስጥ ናት፤ ቤተሰቡም እየበዛ ሲሄድ መሰፋት ይኖርባታል። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ይበልጥ በምትበዛበት መጠን፣ ከስህተቶችና ከብልሹነቶች ለመከላከል ራሷን ይበልጥ ማጠናከር ይኖርባታል። ፈጣሪሽ ባልሽ ነው። ክርስቶስ የእስራኤል ቅዱስ፣ ከብሉይ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ጋር የተደረገው የቃል ኪዳኑ መካከለኛ ነው። ለረጅም ጊዜ የእስራኤል አምላክ ተብሎ ሲጠራ ነበር፤ አሁን ግን የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል። ከኃጢአትም ያነጻል፣ እያንዳንዱንም እውነተኛ አማኝ በዚህ ቅዱስ አንድነት እንዲደሰት ያደርጋል። ይህን ምሕረት በበቂ ሁኔታ ማድነቅ ፈጽሞ አንችልም፣ ወይም ይህን ልዩ መብት በሚገባ ማክበር ፈጽሞ አንችልም።

54:6-10 እግዚአብሔር ቁጣውን ለማሳየት የዘገየ እንደሆነ፣ ምሕረትን ለማሳየትም ፈጣን ነው። እግዚአብሔር መጥቶ ሲያጽናናቸው የምሕረቱ ምላሽ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው! እርሱ በእነርሱ ላይ ይምራልናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Sing, O barren woman, you who never bore a child; burst into song, shout for joy, you who were never in labor; because… English BCV “ኣቲ ዘይወለድኪ መኻን ዘምሪ፤ ኣቲ ፃዕሪ ሕርሲ ዘይትፈልጢ፥ ዕልል በሊ ብሓጐስውን ኣድምፂ፤ ካብታ ሰብኣይ ዘለዋስ፥ ደቂ እታ ፍትሕቲ ኽበዝሑ እዮምሞ” ይብል እግዚኣብሄር። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Dubartii ishee abbaa manaa qabdu caalaa, dubartiin isheen abbaan manaa,“Ijoollee in dhabde” jedhee dhiisee ij… Afaan Oromoo BCV GIZ ትትፌሣሕ መካን እንተ ኢትወልድ ትኬልሕ ወተአወዩ እንተ ኢተሐምም፡ እስመ ብዙኅ ውሉዳ ለመዓስብ እምእንተ ባቲ ምተ፡ እስመ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር። giz GAZGAZ Waaqayyo,“Dubartii ishee abbaa manaa qabdu caalaa, dubartiin isheen abbaan manaa,“Ijoollee in dhabde” jedhee dhiisee ij… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቲ ዘይወለድኪ መኻን ዘምሪ፤ ኣቲ ፃዕሪ ሕርሲ ዘይትፈልጢ፥ ዕልል በሊ ብሓጐስውን ኣድምፂ፤ ካብታ ሰብኣይ ዘለዋስ፥ ደቂ እታ ፍትሕቲ ኽበዝሑ እዮምሞ” ይብል እግዚኣብሄር። ትግርኛ AMHNIV “አንቺ መካን ሴት፤ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ SWAHSUV Imba, wewe uliye tasa, wewe usiyezaa; paza sauti yako kwa kuimba, piga kelele, wewe usiyekuwa na utungu; maana watoto w… Kiswahili