ትንቢተ ኢሳይያስ 54

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:32 አዳምጥ
አዳምጥ 3:32 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“አንቺ መካን ሴት፤ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።

2“የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤ የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ ፈጽሞ አትቈጥቢ፤ ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ።

3ወደ ቀኝም ወደ ግራም ትስፋፊያለሽ፤ ዘሮችሽ መንግሥታትን ይወርሳሉ፤ በባድማ ከተሞቻቸውም ይኖራሉና።

4“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

5ባልሽ ፈጣሪሽ ነውና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ታዳጊሽ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።

6እንደ ተናቀች የልጅነት ሚስት፣ ከልብ እንዳዘነችና እንደ ተጠላች ሚስት፣ እግዚአብሔር እንደ ገና ይጠራሻል” ይላል አምላክሽ።

7“ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ ነገር ግን በታላቅ ርኅራኄ መልሼ እሰበስብሻለሁ።

8ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።

9“ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣ እንደ ኖኅ ዘመን ነው፤ አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቈጣ፣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።

10ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

11“አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።

12ጒልላትሽን በቀይ ዕንቊ፣ በሮችሽን በሚያብረቀርቁ ዕንቊዎች፣ ቅጥሮችሽንም በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።

13ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል።

14በጽድቅ ትመሠረቻለሽ፤ የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤ የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤ አጠገብሽም አይደርስም።

15ማንም ጒዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጒዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።

16“እነሆ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣ የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ አንጥረኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤

17በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

54:1-5 ክርስትና ከመመሥረቱ በፊት ለረጅም ዘመናት በዓለም ላይ የሃይማኖት ዝቅተኛ ሁኔታን አስተውሉ። ነገር ግን ወንጌልን በመስበክ፣ እልፍ አዕላፋት ሰዎች ከጣዖታት ወደ ሕያው እግዚአብሔር ተመለሱ። ይህ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ የደስታ ምንጭ ነው። የቤተ ክርስቲያን ወሰኖች ሰፉ። በምድር ላይ ያላት ሁኔታ እንደ ድንኳን ወይም ማደሪያ ድንኳን ቀላልና ተንቀሳቃሽ ብትሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ግን እያደገች ያለች ሁኔታ ውስጥ ናት፤ ቤተሰቡም እየበዛ ሲሄድ መሰፋት ይኖርባታል። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ይበልጥ በምትበዛበት መጠን፣ ከስህተቶችና ከብልሹነቶች ለመከላከል ራሷን ይበልጥ ማጠናከር ይኖርባታል። ፈጣሪሽ ባልሽ ነው። ክርስቶስ የእስራኤል ቅዱስ፣ ከብሉይ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ጋር የተደረገው የቃል ኪዳኑ መካከለኛ ነው። ለረጅም ጊዜ የእስራኤል አምላክ ተብሎ ሲጠራ ነበር፤ አሁን ግን የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል። ከኃጢአትም ያነጻል፣ እያንዳንዱንም እውነተኛ አማኝ በዚህ ቅዱስ አንድነት እንዲደሰት ያደርጋል። ይህን ምሕረት በበቂ ሁኔታ ማድነቅ ፈጽሞ አንችልም፣ ወይም ይህን ልዩ መብት በሚገባ ማክበር ፈጽሞ አንችልም።

54:6-10 እግዚአብሔር ቁጣውን ለማሳየት የዘገየ እንደሆነ፣ ምሕረትን ለማሳየትም ፈጣን ነው። እግዚአብሔር መጥቶ ሲያጽናናቸው የምሕረቱ ምላሽ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው! እርሱ በእነርሱ ላይ ይምራልናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ ENGNIV “Sing, O barren woman, you who never bore a child; burst into song, shout for joy, you who were never in labor; because… English BCV “ኣቲ ዘይወለድኪ መኻን ዘምሪ፤ ኣቲ ፃዕሪ ሕርሲ ዘይትፈልጢ፥ ዕልል በሊ ብሓጐስውን ኣድምፂ፤ ካብታ ሰብኣይ ዘለዋስ፥ ደቂ እታ ፍትሕቲ ኽበዝሑ እዮምሞ” ይብል እግዚኣብሄር። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Dubartii ishee abbaa manaa qabdu caalaa, dubartiin isheen abbaan manaa,“Ijoollee in dhabde” jedhee dhiisee ij… Afaan Oromoo BCV GIZ ትትፌሣሕ መካን እንተ ኢትወልድ ትኬልሕ ወተአወዩ እንተ ኢተሐምም፡ እስመ ብዙኅ ውሉዳ ለመዓስብ እምእንተ ባቲ ምተ፡ እስመ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር። giz GAZGAZ Waaqayyo,“Dubartii ishee abbaa manaa qabdu caalaa, dubartiin isheen abbaan manaa,“Ijoollee in dhabde” jedhee dhiisee ij… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣቲ ዘይወለድኪ መኻን ዘምሪ፤ ኣቲ ፃዕሪ ሕርሲ ዘይትፈልጢ፥ ዕልል በሊ ብሓጐስውን ኣድምፂ፤ ካብታ ሰብኣይ ዘለዋስ፥ ደቂ እታ ፍትሕቲ ኽበዝሑ እዮምሞ” ይብል እግዚኣብሄር። ትግርኛ SWAHSUV Imba, wewe uliye tasa, wewe usiyezaa; paza sauti yako kwa kuimba, piga kelele, wewe usiyekuwa na utungu; maana watoto w… Kiswahili