ትንቢተ ኢሳይያስ 52

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች2:58 አዳምጥ
አዳምጥ 2:58 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።

2ትቢያሽን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ።

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”

4ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመጀመሪያ ሕዝቤ ይኖር ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በኋላም አሦር ያለ ምክንያት አስጨንቆ ገዛው።

5“አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዶአል፤ የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “ቀኑን ሙሉ፣ ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል።

6ስለዚህ ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤ በዚያ ቀንም፣ አስቀድሜ የተናገርሁ እኔ መሆኔን ይረዳል፤ እነሆ፤ እኔው ነኝ።”

7በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራች ይዘው የሚመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበስሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።

8ስሚ፤ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ።

9እናንት የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቶአልና።

10እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።

11እናንት የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ፤ ተለዩ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኵስ ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ።

12ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤ የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።

13እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።

14ብዙዎች በእርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣ መልኩ ከማንም ከሰው የተለየ፤ ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።

15ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤ በእርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ ያልሰሙትን ያስተውላሉ።

ማብራሪያ

52:1-12 ወንጌል በፍርሃት ለታሰሩት ነጻነትን ያውጃል። በኃጢአት ሸክም ደክመውና ከብደው ያሉት በክርስቶስ እፎይታን ያግኙ፤ የጥርጣሬያቸውንና የፍርሃታቸውን አቧራ ከራሳቸው ላይ ያራግፉ፤ ከእነዚያም ማሰሪያዎች ራሳቸውን ይፍቱ። ቤዛው ለድነታችን የከፈለው ዋጋ ብር ወይም ወርቅ፣ ወይም በሚያልፉ ነገሮች አልነበረም፤ ነገር ግን የራሱ ክቡር ደም ነበር። የዚህን ድነት ነጻነት ስንመለከት፣ እንዲሁም ኃጢአቶች ለጊዜያዊ ምቾት ምን ያህል ጎጂ እንደሆኑ ስናስብ፣ በክርስቶስ ያለውን ቤዛነት ይበልጥ እናደንቃለን። የእግዚአብሔር ክብር በእያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ ውስጥ ቅድስናን እንደሚፈልግ እያስታወስን፣ በየኃጢአቱ ሁሉ ላይ ድልን እንፈልጋለንን? መልካሙ ዜና ጌታ ኢየሱስ ይነግሣል የሚለው ነው። ክርስቶስ ራሱ እነዚህን የምሥራች ዜናዎች መጀመሪያ አመጣ። አገልጋዮቹ እነዚህን መልካም ዜናዎች ያውጃሉ፤ ከዓለም ብልሹነት ራሳቸውን ንጹሕ በማድረግ፣ ለተላኩላቸው ሰዎች ውብ ናቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። አማርኛ ENGNIV Awake, awake, O Zion, clothe yourself with strength. Put on your garments of splendor, O Jerusalem, the holy city. The … English BCV ኣቲ ፅዮን ተስኢ፤ ተስኢ፤ ሓይልኺ ልበሲ፤ ኣቲ ቕድስቲ ኸተማ ኢየሩሳሌም፥ ናይ መዓርግ ልብስኺ ልበሲ፤ ድሕሪ ሕዚ ዘይተገርዘን ርኹስን፥ ናባኺ ኣይኣቱን እዩ እሞ። ትግርኛ GAZBIB Dammaqi yaa Xiyoon, humna godhadhuutii ka'i! Yaa Yerusaalem mandara qulqulluu nana, ka'ii uffata miidhaginaa keetii uff… Afaan Oromoo BCV GIZ ተንሥኢ ተንሥኢ ጽዮን ልበሲ ኀይለኪ ወእንቲኒ ኢየሩሳሌም ልበሲ ትርሲተኪ ሀገር ቅደስት፤ ወኢየኀልፍ እንከ እንተ ኀቤኪ ቈላፍ ወርኩስ። giz GAZGAZ Dammaqi yaa Xiyoon, humna godhadhuutii ka'i! Yaa Yerusaalem mandara qulqulluu nana, ka'ii uffata miidhaginaa keetii uff… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቲ ፅዮን ተስኢ፤ ተስኢ፤ ሓይልኺ ልበሲ፤ ኣቲ ቕድስቲ ኸተማ ኢየሩሳሌም፥ ናይ መዓርግ ልብስኺ ልበሲ፤ ድሕሪ ሕዚ ዘይተገርዘን ርኹስን፥ ናባኺ ኣይኣቱን እዩ እሞ። ትግርኛ SWAHSUV Amka, amka, jivike nguvu zako, Ee Sayuni; Jivike mavazi yako mazuri, Ee Yerusalemu, mji mtakatifu; Kwa maana tokea sasa… Kiswahili