ትንቢተ ኢሳይያስ 45

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:58 አዳምጥ
አዳምጥ 4:58 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

2‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።

3በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።

4ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣ አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።

5እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔ በቀር አምላክ የለም። አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣ እኔ አበረታሃለሁ።

6ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣ እስከ መጥለቂያው፣ ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።

7እኔ ብርሃንን ሠራሁ፤ ጨለማንም ፈጠርሁ፤ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’

8“እናንት ሰማያት፣ ጽድቅን ከላይ አዝንቡ፤ ደመናትም ወደ ታች አንጠብጥቡ፤ ምድር ትከፈት፤ ድነት ይብቀል፤ ጽድቅም አብሮት ይደግ፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።

9“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋር ክርክር ለሚገጥም ወዮለት፤ ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?

10አባቱን፣ ‘የወለድኸው ምንድን ነው?’ ለሚል፣ እናቱንም፣ ‘ምን ወለድሽ’? ለሚል ወዮለት።

11“የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪውም የሆነ እግዚአብሔር፣ ስለሚመጡ ነገሮች እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ ልጆቼ ትጠይቁኛላችሁን? ስለ እጆቼስ ሥራ ታዙኛላችሁን?

12ምድርን የሠራሁ እኔ ነኝ፤ ሰውንም በላይዋ ፈጥሬአለሁ፤ እጆቼ ሰማያትን ዘርግተዋል፤ የሰማይንም ሰራዊት አሰማርቻለሁ።

13ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”

14እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የግብፅ ሀብትና የኢትዮጵያ ንግድ፣ ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎች፣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ የአንተ ይሆናሉ፤ ከኋላ ይከተሉሃል፤ በሰንሰለትም ታስረው ወደ አንተ በመምጣት፣ በፊትህ እየሰገዱ፣ ‘በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለው ይለምኑሃል።”

15አዳኙ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ አንተ በእውነት ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

16ጣዖት ሠሪዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀላሉ፤ በአንድነት ይዋረዳሉ።

17እስራኤል ግን በእግዚአብሔር፣ በዘላለም ድነት ይድናል፤ እናንተም ለዘላለም፣ አታፍሩም፤ አትዋረዱም።

18ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

19በጨለማ ምድር፣ በምስጢር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብም ዘር፣ “በከንቱ ፈልጉኝ” አላልሁም። እኔ እግዚአብሔር እውነትን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለው።

20“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንት ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።

21ጒዳያችሁን ተናገሩ፤ አቅርቡ፤ ተሰብስበውም ይማከሩ። ይህን አስቀድሞ ማን ዐወጀ? ከጥንትስ ማን ተናገረ? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ጻድቅና አዳኝ የሆነ አምላክ፣ ከእኔ በቀር ማንም የለም፤ ከእኔ ሌላ አምላክ የለም።

22“እናንት የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።

23ጕልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቶአል።

24ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በእርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ።

25ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ሞገስንም ያገኛሉ።

ማብራሪያ

45:1-4 ቂሮስ የእግዚአብሔር ቅቡዕ ተብሎአል፤ እርሱም ለእርሱ ታላቅ አገልግሎት በእግዚአብሔር ምክር ታስቦለትና ብቁ ሆኖ የተዘጋጀ ነበር። ወደ ወንዙ የሚያስኬዱት የባቢሎን በሮች ቂሮስ ሠራዊቱን ባዶ ወደ ሆነው የውኃ ቦይ ባስገባበት ሌሊት ክፍት ሆነው ቀርተዋል። እግዚአብሔር ከፊቱ ሄደ፣ የከበባቸውንም ከተሞች እንዲገባ አስችሎታል። እርሱም በስውር ስፍራዎች ተደብቀው የነበሩትን ውድ ሀብቶችን ሰጠው። እውነተኛው አምላክ ለቂሮስ ያልታወቀ አምላክ ነበር፤ ቢሆንም እግዚአብሔር አስቀድሞ ያውቀው ነበር፤ በስሙም ጠራው። የዚህ ትክክለኛ ፍጻሜ ቂሮስ ይሖዋ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አስገንዝቦት ሊሆን ይገባል፣ እንዲሁም ለእስራኤል ሲል እንደተሳካለት። በመንግሥታትና በግዛቶች ለውጦች ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ መልካሙን ያደርጋል።

45:5-10 ከይሖዋ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ያለ እርሱም የሚሆን ምንም ነገር የለም። እርሱ ሰላምን ይፈጥራል፣ ይህም ለፍጹም በጎነት የተደረገ ነው። ክፋትንም ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ የኃጢአት ክፋት ሳይሆን የቅጣት ክፋት ነው። እርሱ የእውነት፣ የቅድስና፣ የበጎነት ወይም የደስታ ሁሉ ፈጣሪ ነው። ክፋት፣ ስህተትና መከራ ግን ወደ ዓለም የመጡት በእርሱ ፈቃድና በፍጥረታቱ ሆን ተብሎ በተደረገው ክህደት አማካኝነት ቢሆንም፣ ለጽድቅ ዓላማው ታስረው ተገልብጠዋል። ይህ ትምህርት ለእስራኤል ቤዛነት በብርቱ ለተመኙት፣ ነገር ግን በጸጥታ ለጠበቁት መጽናኛ ይሆን ዘንድ ተተግብሯል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ አማርኛ ENGNIV “This is what the Lord says to his anointed, to Cyrus, whose right hand I take hold of to subdue nations before him and… English BCV እግዚኣብሄር ንዝቐባእኹዎ፥ ህዝብታት ኣብ ቅድሚኡ ኸግዝአሉ፥ ሕቘ ነገስታት ከፍትሕ፥ ደገታቱ ኸይዕፀዉ፥ መዓፁኡ ኣብ ቅድሚኡ ንኽኸፍት፥ የማነይቲ ኢዱ ንዝሓዝኩዎ ብዛዕባ ቂሮስ እግዚኣብሄር ከ… ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo, inni Qiirosin moosise, “Qiiros saba lafa irraa harka isaa jala akka galfatuuf, moototas mi'a waraanaa akka hi… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር አምላክ ለመሢሕየ ቂሮስ ዘአኀዝክዎ በእዴየ ከመ ኣግርሮመ ለአሕዛብ በቅድሜሁ፤ ወእነፅኅ ኀይለ ነገሥት ወኣርኁ አናቅጸ በቅድሜሁ ወኢይትዐጽዋ አህጉር፦ giz GAZGAZ Waaqayyo, inni Qiirosin moosise, “Qiiros saba lafa irraa harka isaa jala akka galfatuuf, moototas mi'a waraanaa akka hi… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ንዝቐባእኹዎ፥ ህዝብታት ኣብ ቅድሚኡ ኸግዝአሉ፥ ሕቘ ነገስታት ከፍትሕ፥ ደገታቱ ኸይዕፀዉ፥ መዓፁኡ ኣብ ቅድሚኡ ንኽኸፍት፥ የማነይቲ ኢዱ ንዝሓዝኩዎ ብዛዕባ ቂሮስ እግዚኣብሄር ከ… ትግርኛ SWAHSUV Haya ndiyo Bwana amwambiayo Koreshi, masihi Kiswahili