ትንቢተ ኢሳይያስ 45

AMHEVGአማርኛ24 ጥቅሶች4:59 አዳምጥ
አዳምጥ 4:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦

2በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤

3በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።

4ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።

5እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።

7ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።

8እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፥ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።

9ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ፦ እጅ የለውም፡ ይላልን?

10አባትን፦ ምን ወልደሃል? ወይም ሴትን፦ ምን አማጥሽ? ለሚል ወዮ!

11የእስራኤል ቅዱስ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፥ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።

12እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።

13እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

14እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም፡ ብለው ይለምኑሃል።

15የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

16ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።

17እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፥ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም።

18ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

19በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ፡ አላልሁም፤ እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ።

20እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።

21ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።

22እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።

23ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም፦ ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል፡ ብዬ በራሴ ምያለሁ።

24ስለ እኔም፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።

25የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም፡ ይባላል።

ማብራሪያ

45:1-4 ቂሮስ የእግዚአብሔር ቅቡዕ ተብሎአል፤ እርሱም ለእርሱ ታላቅ አገልግሎት በእግዚአብሔር ምክር ታስቦለትና ብቁ ሆኖ የተዘጋጀ ነበር። ወደ ወንዙ የሚያስኬዱት የባቢሎን በሮች ቂሮስ ሠራዊቱን ባዶ ወደ ሆነው የውኃ ቦይ ባስገባበት ሌሊት ክፍት ሆነው ቀርተዋል። እግዚአብሔር ከፊቱ ሄደ፣ የከበባቸውንም ከተሞች እንዲገባ አስችሎታል። እርሱም በስውር ስፍራዎች ተደብቀው የነበሩትን ውድ ሀብቶችን ሰጠው። እውነተኛው አምላክ ለቂሮስ ያልታወቀ አምላክ ነበር፤ ቢሆንም እግዚአብሔር አስቀድሞ ያውቀው ነበር፤ በስሙም ጠራው። የዚህ ትክክለኛ ፍጻሜ ቂሮስ ይሖዋ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አስገንዝቦት ሊሆን ይገባል፣ እንዲሁም ለእስራኤል ሲል እንደተሳካለት። በመንግሥታትና በግዛቶች ለውጦች ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ መልካሙን ያደርጋል።

45:5-10 ከይሖዋ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ያለ እርሱም የሚሆን ምንም ነገር የለም። እርሱ ሰላምን ይፈጥራል፣ ይህም ለፍጹም በጎነት የተደረገ ነው። ክፋትንም ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ የኃጢአት ክፋት ሳይሆን የቅጣት ክፋት ነው። እርሱ የእውነት፣ የቅድስና፣ የበጎነት ወይም የደስታ ሁሉ ፈጣሪ ነው። ክፋት፣ ስህተትና መከራ ግን ወደ ዓለም የመጡት በእርሱ ፈቃድና በፍጥረታቱ ሆን ተብሎ በተደረገው ክህደት አማካኝነት ቢሆንም፣ ለጽድቅ ዓላማው ታስረው ተገልብጠዋል። ይህ ትምህርት ለእስራኤል ቤዛነት በብርቱ ለተመኙት፣ ነገር ግን በጸጥታ ለጠበቁት መጽናኛ ይሆን ዘንድ ተተግብሯል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “This is what the Lord says to his anointed, to Cyrus, whose right hand I take hold of to subdue nations before him and… English BCV እግዚኣብሄር ንዝቐባእኹዎ፥ ህዝብታት ኣብ ቅድሚኡ ኸግዝአሉ፥ ሕቘ ነገስታት ከፍትሕ፥ ደገታቱ ኸይዕፀዉ፥ መዓፁኡ ኣብ ቅድሚኡ ንኽኸፍት፥ የማነይቲ ኢዱ ንዝሓዝኩዎ ብዛዕባ ቂሮስ እግዚኣብሄር ከ… ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo, inni Qiirosin moosise, “Qiiros saba lafa irraa harka isaa jala akka galfatuuf, moototas mi'a waraanaa akka hi… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር አምላክ ለመሢሕየ ቂሮስ ዘአኀዝክዎ በእዴየ ከመ ኣግርሮመ ለአሕዛብ በቅድሜሁ፤ ወእነፅኅ ኀይለ ነገሥት ወኣርኁ አናቅጸ በቅድሜሁ ወኢይትዐጽዋ አህጉር፦ giz GAZGAZ Waaqayyo, inni Qiirosin moosise, “Qiiros saba lafa irraa harka isaa jala akka galfatuuf, moototas mi'a waraanaa akka hi… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ንዝቐባእኹዎ፥ ህዝብታት ኣብ ቅድሚኡ ኸግዝአሉ፥ ሕቘ ነገስታት ከፍትሕ፥ ደገታቱ ኸይዕፀዉ፥ መዓፁኡ ኣብ ቅድሚኡ ንኽኸፍት፥ የማነይቲ ኢዱ ንዝሓዝኩዎ ብዛዕባ ቂሮስ እግዚኣብሄር ከ… ትግርኛ AMHNIV “ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አማርኛ SWAHSUV Haya ndiyo Bwana amwambiayo Koreshi, masihi Kiswahili