ትንቢተ ኢሳይያስ 42

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:39 አዳምጥ
አዳምጥ 4:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣ በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።

2አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።

3የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።

4ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”

5ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ያበጀ፣ ለሕዝቧ እስትንፋስን፣ ለሚኖሩባትም ሕይወትን የሚሰጥ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

6“እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ እጅህንም እይዛለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፤ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን፣ ለአሕዛብም ብርሃን አደርግሃለሁ።

7የዕውሮችን ዐይን ትከፍታለህ፤ ምርኮኞችን ከእስር ቤት፣ በጨለማ የተቀመጡትንም ከወህኒ ታወጣለህ።

8“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።

9እነሆ፤ የቀድሞው ነገር ተፈጽሞአል፤ እኔም አዲስ ነገር እናገራለሁ፤ ከመብቀሉም በፊት፣ ለእናንተ አስታውቃለሁ።

10እናንት ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ።

11ምድረ በዳውና ከተሞቹ ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ ቄዳር ያለችበት መንደር ደስ ይበለው፤ የሴላ ሕዝቦች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ራስ ላይ ይጩኹ።

12ክብር ለእግዚአብሔር ይስጡ፤ ምስጋናውንም በደሴቶች ያውጁ።

13እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤ እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤ የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።

14“ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤ ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።

15ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ ኵሬውን አደርቃለሁ።

16ዕውሮችን በማያወቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ። ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ። ይህን አደርጋለሁ፤ አልተዋቸውም።

17በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።

18“እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤ እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።

19አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ? ለእኔ ታማኝ እንደሆነ ሰው የታወረ፣ እንደ እግዚአብሔርስ አገልጋይ ዕውር ማነው?

20ብዙ ነገርን አያችሁ፤ ነገር ግን አላስተዋላችሁም፤ ጆሮአችሁ ክፍት ነው፤ ነገር ግን ምንም አትሰሙም።”

21እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሲል፣ ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስ አለው።

22ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣ በጒድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣ በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ ተበዝብዘዋል፣ የሚያድናቸውም የለም፤ ተማርከዋል፣ “መልሷቸው” የሚልም የለም።

23ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣ ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው?

24ያዕቆብን ለዝርፊያ፣ እስራኤልን ለምርኮ የዳረገ ማነው? በኀጢአት የበደልነው፣ እግዚአብሔር አይደለምን? መንገዱን ለመከተል፣ ለሕጉም መታዘዝ አልፈለጉምና።

25ስለዚህ የሚነድ ቍጣውን፣ የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤ በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።

ማብራሪያ

ኢሳይያስ 42:1-4 ይህ ትንቢት በክርስቶስ ተፈጽሟል (ማቴዎስ 12:17)። ነፍሳችን በእርሱ ላይ ትደገፍ፣ በእርሱም ደስ ይበላት፤ ያንጊዜም በእርሱ ተብሎ አብ በእኛ ደስ ይሰኛል። መንፈስ ቅዱስ መጣ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ላይ አረፈ፣ ያለ መጠን። እርሱ የኃጢአተኞችን ተቃውሞ በትዕግሥት ተሸከመ። መንግሥቱ መንፈሳዊ ነው፤ በምድራዊ ክብር ሊገለጥ አልነበረም። እርሱ በጥርጣሬና በፍርሃት ለተጨነቁ፣ እንደተቀጠቀጠ ሸንበቆ ለሆኑት፣ እንደሚያጨስ የተልባ ፈትል ላሉት፣ ወይም አዲስ እንደበራ የመብራት ክር ሆኖ ሊጠፋ የተቃረበን ርኅሩኅ ነው። እርሱ አይንቃቸውም፣ የማይችሉትንም ከባድ ሥራ ወይም መከራ አይጭንባቸውም። እርሱ በብዙ ተአምራቱና በትንሣኤው የቅዱስ ሃይማኖቱን እውነት ሙሉ በሙሉ አሳየ። በወንጌሉ ኃይልና በጸጋው በሰዎች አእምሮ ውስጥ ጠቢባንና ጻድቃን የሚያደርጋቸውን መርሆች ይሰርጻል። እጅግ ሩቅ የሆኑ ብሔራት ሕጉንና ወንጌሉን ይጠብቃሉ፣ በደስታም ይቀበሉታል። ጥሪያችንንና ምርጫችንን እርግጠኛ ለማድረግ፣ አብም በእኛ ላይ ለበጎ ደስ እንዲሰኝ ከፈለግን፣ ክርስቶስን ማየት፣ መስማት፣ ማመንና መታዘዝ አለብን።

ኢሳ ፵፪፥፭-፲፪ የቤዛነት ሥራ ሰውን እንደ ፈጣሪው ለእግዚአብሔር ሊታዘዝ ወደሚገባው ታዛዥነት ይመልሰዋል። ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነው። በጸጋውም ሰይጣን ያሳወራቸውን አእምሮአቸውን ይከፍታል፤ ከኃጢአት ባርነትም ነፃ ያወጣል። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን አግዟል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። አማርኛ ENGNIV “Here is my servant, whom I uphold, my chosen one in whom I delight; I will put my Spirit on him and he will bring just… English BCV “እንሆ፥ ደጊፈ ዝሓዝኩዎ ባርያይ፥ ኣነ ዝሓረኽዎ፥ ብእኡ ኸዓ ደስ ዝብለኒ፥ ሕሩየይ፥ መንፈሰይ ኣብ ልዕሊኡ ኣሕዲረ ኣለኹ፤ ንሱ ኸዓ ንኣህዛብ ፍትሒ ኸውፅአሎም እዩ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo itti fufee,“Kunoo, garbichi koo inni ani ol ol qabu, inni ani fo'adhe, inni ani jaalladhu isa kana! Ani hafuur… Afaan Oromoo BCV GIZ ናሁ ቍልዔየ ዘአኀዝክዎ፤ ወእስራኤል ኅሩይየ ዘተወክፈቶ ነፍስየ፤ ወወሀብኩ መንፈስየ ዲቤሁ ያመጽእ ፍትሐ ለአሕዛብ። giz GAZGAZ Waaqayyo itti fufee,“Kunoo, garbichi koo inni ani ol ol qabu, inni ani fo'adhe, inni ani jaalladhu isa kana! Ani hafuur… Afaan Oromoo BCV aksum “እንሆ፥ ደጊፈ ዝሓዝኩዎ ባርያይ፥ ኣነ ዝሓረኽዎ፥ ብእኡ ኸዓ ደስ ዝብለኒ፥ ሕሩየይ፥ መንፈሰይ ኣብ ልዕሊኡ ኣሕዲረ ኣለኹ፤ ንሱ ኸዓ ንኣህዛብ ፍትሒ ኸውፅአሎም እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Tazama mtumishi wangu nimtegemezaye; mteule wangu, ambaye nafsi yangu imependezwa naye; nimetia roho yangu juu yake; na… Kiswahili