ትንቢተ ኢሳይያስ 12

AMHEVGአማርኛ6 ጥቅሶች0:54 አዳምጥ
አዳምጥ 0:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያም ቀን፦ አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ።

2እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም፡ ትላለህ።

3ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።

4በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።

5ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ።

6አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።

ማብራሪያ

12:10-16

ወንጌል በይፋ በሚሰበክበት ጊዜ፣ አሕዛብ ጌታቸውና መድኃኒታቸው አድርገው ክርስቶስ ኢየሱስን ይፈልጋሉ፤ ለነፍሳቸውም ዕረፍትን ያገኛሉ። የእግዚአብሔር ጊዜ ሕዝቡን ለማዳን ሲደርስ፣ የተቃውሞ ተራሮች በእርሱ ፊት ሜዳ ይሆናሉ። እግዚአብሔር የጨለማ ቀናትን በፍጥነት ወደ ክብር ቀናት ሊለውጥ ይችላል። ጌታ ጥንት የነበረውን ሕዝቡን ይሰበስብ ዘንድ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያኑም ይመልሳቸው ዘንድ፣ እንዲሁም የአሕዛብም ሙላት ይገባ ዘንድ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6