ትንቢተ ኢሳይያስ 12

AMHNIVአማርኛ6 ጥቅሶች1:01 አዳምጥ
አዳምጥ 1:01 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።

2እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖአል።”

3ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።

4በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።

5ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤ ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።

6የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።

ማብራሪያ

12:10-16

ወንጌል በይፋ በሚሰበክበት ጊዜ፣ አሕዛብ ጌታቸውና መድኃኒታቸው አድርገው ክርስቶስ ኢየሱስን ይፈልጋሉ፤ ለነፍሳቸውም ዕረፍትን ያገኛሉ። የእግዚአብሔር ጊዜ ሕዝቡን ለማዳን ሲደርስ፣ የተቃውሞ ተራሮች በእርሱ ፊት ሜዳ ይሆናሉ። እግዚአብሔር የጨለማ ቀናትን በፍጥነት ወደ ክብር ቀናት ሊለውጥ ይችላል። ጌታ ጥንት የነበረውን ሕዝቡን ይሰበስብ ዘንድ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያኑም ይመልሳቸው ዘንድ፣ እንዲሁም የአሕዛብም ሙላት ይገባ ዘንድ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6