ትንቢተ ሆሴዕ 10

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:54 አዳምጥ
አዳምጥ 2:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያውን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።

2ልባቸው ተከፈለ፤ አሁንም በደላቸውን ይሸከማሉ፤ እርሱ መሠዊያቸውን ያፈርሳል፥ ሐውልቶቻቸውን ያጠፋል።

3አሁንም፦ “ንጉሥ የለንም፥ እግዚአብሔርን አልፈራንምና፤ ንጉሥስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።

4የማይረባውን ቃል ይናገራሉ፤ ቃል ኪዳን በገቡ ጊዜ በሐሰት ይምላሉ፤ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት ይበቅልባቸዋል።

5የሰማርያ ሰዎች ስለ ቤትአዌን እምቦሳ ይፈራሉ፤ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና ሕዝቡ ያለቅሱለታል፥ የጣዖቱ ካህናትም በኀዘን ይንተባተባሉ።

6ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ወደ አሦር ይማረካል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።

7ሰማርያ ከንጉሥዋ ጋር በውኃ ላይ እንዳለ አረፋ ጠፍታለች።

8የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ ተራሮችንም፦ “ክደኑን፥ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን፡” ይሉአቸዋል።

9እስራኤል ሆይ፥ ከጊብዓ ዘመን ጀምረህ ኃጢአትን ሠርተሃል፤ በዚያ ጸንተዋል፤ በጊብዓ ላይ ሰልፍ አይደርስባቸውምን?

10በፈቀድሁም ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ፤ ስለ ሁለቱም ኃጢአታቸው በታሰሩ ጊዜ አሕዛብ ይሰበሰቡባቸዋል።

11ኤፍሬም ማበራየት እንደ ለመደች ጊደር ነው፥ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፥ ይሁዳም ያርሳል፥ ያዕቆብም አፈሩን ያለሰልሳል።

12እግዚአብሔር መጥቶ ጽድቅን እስኪያዘንብላችሁ ድረስ እርሱን የምትሹበት ዘመን ነውና ለእናንተ በጽድቅ ዝሩ፥ እንደ ምሕረቱም መጠን እጨዱ፥ ጥጋታችሁንም እረሱ።

13ክፋትን አርሳችኋል፥ ኃጢአትንም አጭዳችኋል፥ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በኃያላንህ ብዛት፥ በመንገድህም ላይ ታምነሃልና።

14በሕዝብህም መካከል ሽብር ይነሣል፤ እናትም ከልጆችዋ ጋር በተፈጠፈጠች ጊዜ ሰልማን ቤትአርብኤልን በሰልፍ ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።

15ከኃጢአታችሁም ክፋት የተነሣ ቤቴል እንዲሁ ያደርግባችኋል፤ በነጋ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

ማብራሪያ

፲፡፩-፰

የወይን ግንድ ዋጋው ፍሬው ብቻ ነው፤ እስራኤል ግን ፍሬን ሙሉ በሙሉ አላፈራም ነበር። ልቦቻቸው ተከፋፍለው ነበር። እግዚአብሔር የልብ ገዢ ነው፤ ሁሉንም ወይም ከቶውንም አይቀበልም። የልብ ፍሰት ሙሉ በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፣ በብርታት ይፈስ ነበር፤ በፊቱም ያለውን ሁሉ ያወርድ ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ቃል ኪዳን አስመሳይ ነበር። የጽድቅም ሂደት እንደ መርዛማ እምቧይ ነበር። ወዮ! እስከ ዛሬም ድረስ የሚታየው ቤተ ክርስቲያን ምንኛ ባዶ ወይን ግንድ ነው! ነገር ግን ምድራዊ ብልጽግና ሁሉ የውሃ አረፋ ክምችት ብቻ ነው፣ በውሃ ላይ እንዳለ አረፋም ቶሎ ይጠፋል። ኃጢአተኞች አሁን እንደ አዳኝ የሚንቁትን ያንን ፈራጅ ከንቱ መጠጊያ ይፈልጋሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Israel was a spreading vine; he brought forth fruit for himself. As his fruit increased, he built more altars; as his l… English BCV እስራኤል ብዙሕ ዝሰፍሐን ብዙሕ ፍረ ዝፈሪ ወይንን እዩ። ከም መጠን ምብዛሕ ፍረኡ፥ ብዙሕ መሰውኢታት ኣብዝሐ፤ ከም መጠን ምፅባቕ ምድሩውን፥ እናመልክዑ ሓወልትታት ሰርሑ። ትግርኛ GAZBIB Warri Israa'elis akka muka waynii of jaallatee ija baay'ee naqatuu ti; hammuma iji hojii isaanii baay'ate iddoo aarsaas… Afaan Oromoo BCV GIZ ዓፀደ ወይን ዘሠረፀ ኤፍሬም ወሠምረ ፍሬሁ፤ ወበከመ ብዝኀ ፍሬሆሙ ከማሁ አብዝኀ መሥዋዕቶሙ ወበአምጣነ ብሔሩ ሐነፁ ሐውልተ። giz GAZGAZ Warri Israa'elis akka muka waynii of jaallatee ija baay'ee naqatuu ti; hammuma iji hojii isaanii baay'ate iddoo aarsaas… Afaan Oromoo BCV aksum እስራኤል ብዙሕ ዝሰፍሐን ብዙሕ ፍረ ዝፈሪ ወይንን እዩ። ከም መጠን ምብዛሕ ፍረኡ፥ ብዙሕ መሰውኢታት ኣብዝሐ፤ ከም መጠን ምፅባቕ ምድሩውን፥ እናመልክዑ ሓወልትታት ሰርሑ። ትግርኛ AMHNIV እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ ብዙ ፍሬም አፈራ፤ ፍሬው በበዛ መጠን፣ ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ ምድሩ በበለጸገ መጠን፣ የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ። አማርኛ SWAHSUV Israeli ni mzabibu, utoao matunda yake; kwa kadiri ya wingi wa matunda yake, kwa kadiri iyo hiyo ameongeza madhabahu za… Kiswahili