ትንቢተ ሆሴዕ 9

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:38 አዳምጥ
አዳምጥ 3:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እስራኤል ሆይ፤ ደስ አይበልሽ፤ እንደ ሌሎችም ሕዝቦች ሐሤት አታድርጊ፤ ለአምላክሽ ታማኝ አልሆንሽምና፤ በየእህል ዐውድማውም ላይ፣ ለጋለሞታ የሚከፈለውን ዋጋ ወደሻል።

2የእህል አውድማዎችና የወይን መጭመቂያዎች ሕዝቡን አይመግቡም፤ አዲሱም የወይን ጠጅ ይጐድልባቸዋል።

3በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤ የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል።

4የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈሱም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ። ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።

5በእግዚአብሔር የበዓል ቀናት፣ በዓመት በዓሎቻችሁም ቀን ምን ታደርጋላችሁ?

6ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውም እሾኽ ይወርሰዋል።

7የቅጣት ቀን መጥቶአል፤ የፍርድም ቀን ቀርቦአል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ሞኝ፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሮአል።

8ነቢዩ ከአምላኬ ጋር ሆኖ፣ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ዳሩ ግን በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ፣ በአምላኩም ቤት ጠላትነት ይጠብቀዋል።

9በጊብዓ እንደ ነበረው፣ በርኵሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤ እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።

10“እስራኤልን ማግኘቴ፣ የወይንን ፍሬ፣ በምድረ በዳ የማግኘት ያህል ነበር፤ አባቶቻችሁንም ማየቴ፣ የመጀመሪያውን የበለስ ፍሬ የማየት ያህል ነበር፤ ወደ ብዔልፌጎር በመጡ ጊዜ ግን፣ ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ራሳቸውን ለዩ፤ እንደ ወደዱትም ጣዖት የረከሱ ሆኑ።

11የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤ መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።

12ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ ወዮ ለእነርሱ

13ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣ በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤ አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”

14እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣ የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው።

15“በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣ እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ ስለሠሩት ኀጢአት፣ ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አልወዳቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።

16ኤፍሬም ተመታ፤ ሥራቸው ደረቀ፤ ፍሬም አያፈሩም፤ ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”

17ባለመታዘዛቸው ምክንያት፣ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።

ማብራሪያ

9:1-6 እስራኤል ለጣዖቶቻቸው በሚያቀርቡት መባ አማካኝነት ሽልማት ሰጧቸው። በሃይማኖት ጉዳይ ንፉግ የሆኑ ሰዎች በፍትወቶቻቸው ላይ ደግሞ አባካኝ መሆን የተለመደ ነው። ከእግዚአብሔር ሞገስና ከዘላለም ሕይወት ከሚገኘው ሽልማት ይልቅ፣ በሰብል በረከት ውስጥ ያለውን ሽልማት የሚወዱ ሰዎች እንደ ጣዖት አምላኪዎች ይቆጠራሉ። በመከር ደስታ የተሞሉ ናቸው፤ ለኃጢአትም የማዘን ዝንባሌ የላቸውም። ዓለምንና የዓለምን ነገሮች ጣዖታችንና ድርሻችን ስናደርግ፣ እግዚአብሔር ስንፍናችንን ሊያሳየንና ሊያርመን ፍትሐዊ ነው። የጌታን ሕጎች የማይገዛለት ወይም በፍቅሩ የማይነዳ ማንም በእግዚአብሔር ምድር ለመኖር ሊጠብቅ አይችልም። የጸጋን መንገዶች ስንጠቀምባቸው፣ ከእኛ ቢወሰዱ ምን እንደምናደርግ ልናስብ ይገባል። ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የማድረግ ደስታዎች ለለውጥ የማይገዙ ሲሆኑ፣ በብር የተገዙ ወይም ሰዎች ብራቸውን የሚያስቀምጡባቸው ደስ የሚያሰኙ ቦታዎች ግን ሊወድሙ ይችላሉ። እንደ ነፍስ ረሃብ የከፋ ረሃብ የለም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እስራኤል ሆይ፥ ከአምላክህ ተለይተህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፥ ሐሴትንም አታድርግ፤ በእህሉ አውድማ ሁሉ ላይ የግልሙትናን ዋጋ ወድደሃል። አማርኛ ENGNIV Do not rejoice, O Israel; do not be jubilant like the other nations. For you have been unfaithful to your God; you love… English BCV ኦ እስራኤል፥ ካብ ኣምላኽካ ተፈሊኻ ኣመንዚርካ፥ ኣብ ኵሉ ዓውዲ ስርናይ ዋጋ ምንዝርና ፈቲኻ ኢኻሞ፥ ከም ኣህዛብ ደስ ኣይበልካ፤ ኣይትተሓጐስውን። ትግርኛ GAZBIB Yaa Israa'el, ati ejjuu keetiin Waaqayyo kee irraa waan gara galteef, midhaan oobdii hundumaa irratti argattus “Gatii g… Afaan Oromoo BCV GIZ ኢትትፈሣሕ ወኢትትሐሠይ እስራኤል ከመ አሕዛብ እስመ ዘመውከ እምአምላክከ፤ ወአፍቀርከ ሀብተ እምኵሉ ዓውደ እክል ወምክያደ ወይን። giz GAZGAZ Yaa Israa'el, ati ejjuu keetiin Waaqayyo kee irraa waan gara galteef, midhaan oobdii hundumaa irratti argattus “Gatii g… Afaan Oromoo BCV aksum ኦ እስራኤል፥ ካብ ኣምላኽካ ተፈሊኻ ኣመንዚርካ፥ ኣብ ኵሉ ዓውዲ ስርናይ ዋጋ ምንዝርና ፈቲኻ ኢኻሞ፥ ከም ኣህዛብ ደስ ኣይበልካ፤ ኣይትተሓጐስውን። ትግርኛ SWAHSUV Usifurahi, Israeli, kwa sababu ya furaha, kama hao mataifa; kwa kuwa umezini juu ya Mungu wako, umependa ujira katika k… Kiswahili