ትንቢተ ሆሴዕ 7

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:08 አዳምጥ
አዳምጥ 3:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

2ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣ እነርሱ አይገነዘቡም፤ ኀጢአታቸው ከቦአቸዋል፤ ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።

3“ንጉሡን በክፋታቸው፣ አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።

4ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣ ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣ እንደሚነድ ምድጃ፣ ሁሉም አመንዝራ ናቸው።

5በንጉሣችን የበዓል ቀን፣ አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።

6ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ በተንኰል ይቀርቡታል፤ ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤ እንደሚነድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።

7ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ ገዦቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።

8“ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።

9እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤ እርሱ ግን አላስተዋለም። ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤ እርሱ ግን ልብ አላለም።

10የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እርሱንም አልፈለገም።

11ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣ አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤ አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።

12ሲበሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ክፉ ሥራቸውም በጒባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።

13ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።

14ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፤ ነገር ግን በዐልጋቸው ላይ ሆነው ያለቅሳሉ። ስለ እህልና ስለ አዲስ የወይን ጠጅ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን ከእኔ ዘወር ብለዋል።

15እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤ እነርሱ ግን አደሙብኝ።

16ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ ዒላማውን እንደሳተ ቀስት ናቸው፤ መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር፣ መዘባበቻ ይሆናሉ።

ማብራሪያ

7:1-7 የእግዚአብሔርን አገዛዝ በተግባር አለማመን ለሁሉ የእስራኤል ክፋት መሠረት ነበር፤ እግዚአብሔር ማየት እንደማይችል ወይም ትኩረት እንደማይሰጥ ሁሉ ነበር። ኃጢአቶቻቸውም በየአቅጣጫው ይታዩ ነበር። ልቦቻቸውም በሚንቦገቦግ ምድጃ ውስጥ እንዳለ እሳት በክፉ ምኞቶች ነድደው ነበር። ብሔር እንደመሆናቸው በመካከላቸው በነበረው ችግር ውስጥ ሳሉ፣ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር እርዳታ መፈለግን አስበው አያውቁም። የሰዎች ሕይወት ትክክለኛ ክፋት በልቦቻቸው ውስጥ ካለው ጋር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ክፍልፋይ ነው። ነገር ግን ምኞት በልብ ውስጥ ሲታቀፍ፣ ወደ ውጫዊ ኃጢአት ይፈነዳል። ሌሎችን ወደ ስካር የሚፈትኑ ሰዎች በፍጹም እውነተኛ ወዳጆቻቸው ሊሆኑ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም ጥፋታቸውን ያቅዳሉ። እንዲህም ሰዎች እርስ በርሳቸው መለኮታዊውን የበቀል እርምጃ ያስፈጽማሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በውጭም ወንበዴዎች ቀምተዋልና እስራኤልን እፈውስ ዘንድ በወደድሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ። አማርኛ ENGNIV whenever I would heal Israel, the sins of Ephraim are exposed and the crimes of Samaria revealed. They practice deceit,… English BCV ሓሰት ኣዘውቲሮም እዮም እሞ፥ ሰራቒ ይኣቱ፤ ኣብ ወፃኢ ድማ ሸፋቱ ይኸትሩ ኣለዉ እሞ፥ ንእስራኤል ክፍውሶ ምስ ደለኹ፥ ሓጢኣት ኤፍሬምን፥ ክፍኣት ሰማርያን ተቐልዐ። ትግርኛ GAZBIB “Yeroo ani Israa'elin fayyisuu barbaadutti, yakki Efreem, jal'inni Samaariyaas in mul'ata; isaan gowwoomsaadhaan in hoj… Afaan Oromoo BCV GIZ ወሶበ ሰፋሕክዎ ለእስራኤል ትትከሠት ዓመፃሁ ለኤፍሬም ወእከያ ለሰማርያ እስመ ሐሰተ ገብሩ፤ ወያበውእ ሰራቄ ኀቤሁ ይስእል ወይሰልብ በፍኖት ከመ ይኅበር ማዕሌቶሙ። giz GAZGAZ “Yeroo ani Israa'elin fayyisuu barbaadutti, yakki Efreem, jal'inni Samaariyaas in mul'ata; isaan gowwoomsaadhaan in hoj… Afaan Oromoo BCV aksum ሓሰት ኣዘውቲሮም እዮም እሞ፥ ሰራቒ ይኣቱ፤ ኣብ ወፃኢ ድማ ሸፋቱ ይኸትሩ ኣለዉ እሞ፥ ንእስራኤል ክፍውሶ ምስ ደለኹ፥ ሓጢኣት ኤፍሬምን፥ ክፍኣት ሰማርያን ተቐልዐ። ትግርኛ SWAHSUV Wakati nitakapo kumponya Israeli, ndipo yafunuliwapo maovu ya Efraimu, na ubaya wa Samaria; maana wanatenda uongo, na m… Kiswahili