ትንቢተ ሆሴዕ 4

AMHNIVአማርኛ19 ጥቅሶች3:52 አዳምጥ
አዳምጥ 3:52 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ክስ ስላለው፣ እናንት እስራኤላውያን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ “ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።

2በዚያ ያለው ርግማን፣ መዋሸት፣ መግደል፣ መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤ ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤ ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።

3ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕርም ዓሦች አለቁ።

4“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤ ማንም ሌላውን አይወንጅል፤ በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣ ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።

5ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤ ነቢያትም ከእናንተ ጋር ይደናበራሉ፤ ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤

6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። “ዕውቀትን ስለናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

7ካህናት በበዙ ቊጥር፣ በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቶአል፤ ክብራቸውንም በውርደት ለውጠዋል።

8የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤ ርኵሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።

9ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤ ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።

10“ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤ ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤ እግዚአብሔርን በመተው፣ ራሳቸውን

11ለአመንዝራነት፣ ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤ በእነዚህም

12የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ፤ ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤ ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል። የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤ ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።

13በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤ መልካም ጥላ ባለው፣ በባሉጥ፣ በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣ በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቊርባን ያቀርባሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማዊ፣ ምራቶቻችሁም አመንዝራ ይሆናሉ።

14“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣ የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ አልቀጣቸውም። ወንዶች ከጋለሞቶች ጋር ይሴስናሉ፤ ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋር ይሠዋሉና፤ የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!

15“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣ ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ። “ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።

16እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣ እልኸኞች ናቸው፤ ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች እንዴት ያሰማራቸዋል?

17ኤፍሬም ከጣዖት ጋር ተጣምሮአል፤ እስቲ ተውት፤

18መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣ ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤ ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ።

19ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።

ማብራሪያ

4:1-5 ሆሴዕ ስለ ሥነ ምግባር ብልሹነት እንዲሁም ስለ ጣዖት አምልኮ ይገስጻል። በምድሪቱ ውስጥ እውነት፣ ምሕረት ወይም የእግዚአብሔር እውቀት አልነበረም። ግድያ ሞልቶባት ነበርና (2ኛ ነገሥት 21:16)። ስለዚህ ምድሪቱን ባዶ የሚያደርጉ መከራዎች ተቃርበው ነበር። ኃጢአቶቻችን እንደ እያንዳንዳችን፣ እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ሰፈር፣ እንደ ሕዝብ ሆነው ጌታ ከእኛ ጋር ክርክር እንዲኖረው ያደርጋሉ። እርሱም እንዳያጠፋን ዘንድ ከፊቱ ራሳችንን እናስገዛና እናዋርድ።

4:6-11

ካህናቱም ሕዝቡም እውቀትን ጥለዋልና፤ እግዚአብሔርም በጽድቅ ይጥላቸዋል። የእግዚአብሔርን ሕግ ረስተዋል፤ በልባቸውም ሊይዙት ወይም መታሰቢያውን ለትውልዳቸው ለማስተላለፍ አልተመኙም አልጣሩም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እነርሱንም ልጆቻቸውንም በጽድቅ ይረሳቸዋል። ክብራችን በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ካዋረድነው፣ ይዋል ይደር እንጂ ውርደት ሆኖ ይገኝብናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። አማርኛ ENGNIV Hear the word of the Lord, you Israelites, because the Lord has a charge to bring against you who live in the land: “Th… English BCV ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ “ሓቅን ምሕረትን ንእግዚኣብሄር ምፍላጥን፥ ኣብታ ምድሪ የለን፤ እግዚኣብሄር ምስቶም ኣብታ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ነገር ኣለዎ እሞ፥ ቃል እግዚኣብሄር ስምዑ። ትግርኛ GAZBIB Yaa namoota Israa'el, biyyicha keessa amanamummaan, jaalalli, Waaqayyoon beekuun waan hin jirreef, Waaqayyo warra biyyi… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ቃለ እግዚአብሔር ደቂቀ እስራኤል እስመ ይትዋቀሦሙ እግዚአብሔር ለእለ ይነብሩ ውስተ ምድር። giz GAZGAZ Yaa namoota Israa'el, biyyicha keessa amanamummaan, jaalalli, Waaqayyoon beekuun waan hin jirreef, Waaqayyo warra biyyi… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ “ሓቅን ምሕረትን ንእግዚኣብሄር ምፍላጥን፥ ኣብታ ምድሪ የለን፤ እግዚኣብሄር ምስቶም ኣብታ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ነገር ኣለዎ እሞ፥ ቃል እግዚኣብሄር ስምዑ። ትግርኛ SWAHSUV Lisikieni neno la Bwana, enyi wana wa Israeli; kwa maana Bwana ana mateto nao wakaao katika nchi, kwa sababu hapana kwe… Kiswahili