ትንቢተ ሆሴዕ 4

AMHEVGአማርኛ19 ጥቅሶች2:54 አዳምጥ
አዳምጥ 2:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

2እርግማንና ሐሰት ግዳይና ስርቆት ምንዝርናም ወጥተዋል፤ ደምም ወደ ደም ደርሶአል።

3ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርስዋም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር ይደክማሉ፤ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።

4ነገር ግን ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚከራከሩ ናቸውና ማንም አይከራከር፥ ማንም አይዝለፍ።

5በቀንም ትሰናከላለህ፥ ነቢዩም ከአንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላል፤ እናትህንም አጠፋታለሁ።

6ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።

7እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፤ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።

8የሕዝቤም ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፥ ልባቸውንም ወደ በደላቸው አድርገዋል።

9እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ ይሆናል፤ በመንገዳቸውም እበቀላቸዋለሁ፥ ሥራቸውንም እመልስባቸዋለሁ።

10እግዚአብሔርንም መጠበቅ ትተዋልና ሲበሉ አይጠግቡም፥ ሲያመነዝሩም አይበዙም።

11ግልሙትናና የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል።

12የግልሙትና መንፈስ ሕዝቤን አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና በትራቸውን ይጠይቃሉ፥ ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።

13በተራሮችም ራስ ላይ ይሠዋሉ፤ ጥላውም መልካም ነውና ከኮምበልና ከልብን ከአሆማም ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ፤ ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ይገለሙታሉ፥ ሙሽሮቻችሁም ያመነዝራሉ።

14ወንዶችም ደግሞ ከጋለሞቶች ጋር ይጫወታሉና፥ ከጋለሞቶችም ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ በገለሞቱ ጊዜ፥ ሙሽሮቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም፤ የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል።

15እስራኤል ሆይ፥ አንተ ብታመነዝር ይሁዳ አይበድል፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብላችሁ አትማሉ።

16እስራኤል እንደ እልከኛ ጊደር እንቢ ብሎአል፤ እግዚአብሔርስ በሰፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰማራዋልን?

17ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ተወው።

18ስካርን ፈጽመዋል፥ ግልሙትናንም አብዝተዋል፤ አለቆችዋም ነውርን እጅግ ወደዱ።

19ነፋስ በክንፍዋ አስሮአታል፤ ከመሥዋዕታቸውም የተነሣ ያፍራሉ።

ማብራሪያ

4:1-5 ሆሴዕ ስለ ሥነ ምግባር ብልሹነት እንዲሁም ስለ ጣዖት አምልኮ ይገስጻል። በምድሪቱ ውስጥ እውነት፣ ምሕረት ወይም የእግዚአብሔር እውቀት አልነበረም። ግድያ ሞልቶባት ነበርና (2ኛ ነገሥት 21:16)። ስለዚህ ምድሪቱን ባዶ የሚያደርጉ መከራዎች ተቃርበው ነበር። ኃጢአቶቻችን እንደ እያንዳንዳችን፣ እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ሰፈር፣ እንደ ሕዝብ ሆነው ጌታ ከእኛ ጋር ክርክር እንዲኖረው ያደርጋሉ። እርሱም እንዳያጠፋን ዘንድ ከፊቱ ራሳችንን እናስገዛና እናዋርድ።

4:6-11

ካህናቱም ሕዝቡም እውቀትን ጥለዋልና፤ እግዚአብሔርም በጽድቅ ይጥላቸዋል። የእግዚአብሔርን ሕግ ረስተዋል፤ በልባቸውም ሊይዙት ወይም መታሰቢያውን ለትውልዳቸው ለማስተላለፍ አልተመኙም አልጣሩም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እነርሱንም ልጆቻቸውንም በጽድቅ ይረሳቸዋል። ክብራችን በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ካዋረድነው፣ ይዋል ይደር እንጂ ውርደት ሆኖ ይገኝብናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Hear the word of the Lord, you Israelites, because the Lord has a charge to bring against you who live in the land: “Th… English BCV ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ “ሓቅን ምሕረትን ንእግዚኣብሄር ምፍላጥን፥ ኣብታ ምድሪ የለን፤ እግዚኣብሄር ምስቶም ኣብታ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ነገር ኣለዎ እሞ፥ ቃል እግዚኣብሄር ስምዑ። ትግርኛ GAZBIB Yaa namoota Israa'el, biyyicha keessa amanamummaan, jaalalli, Waaqayyoon beekuun waan hin jirreef, Waaqayyo warra biyyi… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ቃለ እግዚአብሔር ደቂቀ እስራኤል እስመ ይትዋቀሦሙ እግዚአብሔር ለእለ ይነብሩ ውስተ ምድር። giz GAZGAZ Yaa namoota Israa'el, biyyicha keessa amanamummaan, jaalalli, Waaqayyoon beekuun waan hin jirreef, Waaqayyo warra biyyi… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ደቂ እስራኤል፥ “ሓቅን ምሕረትን ንእግዚኣብሄር ምፍላጥን፥ ኣብታ ምድሪ የለን፤ እግዚኣብሄር ምስቶም ኣብታ ምድሪ ዝነብሩ ዘለዉ ነገር ኣለዎ እሞ፥ ቃል እግዚኣብሄር ስምዑ። ትግርኛ AMHNIV በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ክስ ስላለው፣ እናንት እስራኤላውያን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ “ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በም… አማርኛ SWAHSUV Lisikieni neno la Bwana, enyi wana wa Israeli; kwa maana Bwana ana mateto nao wakaao katika nchi, kwa sababu hapana kwe… Kiswahili