ትንቢተ ሆሴዕ 10

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:34 አዳምጥ
አዳምጥ 3:34 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እስራኤል የተንዠረገገ ወይን ነበር፤ ብዙ ፍሬም አፈራ፤ ፍሬው በበዛ መጠን፣ ብዙ መሠዊያዎችን ሠራ፤ ምድሩ በበለጸገ መጠን፣ የጣዖታት ማምለኪያ ዐምዶችን አስጌጠ።

2ልባቸው አታላይ ነው፤ ስለዚህም በደላቸውን ይሸከማሉ። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያወድማል፤ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ያፈራርሳል።

3እነርሱም፣ “እኛ ንጉሥ የለንም፤ እግዚአብሔርን አላከበርንምና፤ ንጉሥ ቢኖረንስ፣ ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?” ይላሉ።

4ከንቱ ተስፋ ይሰጣሉ፤ በሐሰት በመማል፣ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ስለዚህም ፍርድ፣ በዕርሻ ውስጥ እንደሚገኝ መርዛማ ዐረም ይበቅላል።

5በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣ በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ ሕዝቡም ያለቅስለታል፤ በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣ አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤ በምርኮ ከእነርሱ ተወስዶአልና።

6ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ ወደ አሦር ይወሰዳል፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

7ሰማርያና ንጉሥዋ፣ በውሃ ላይ እንዳለ ኩበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።

8የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣ የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤ እሾኽና አሜኬላ ይበቅልባቸዋል፤ መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤ በዚያን ጊዜ ተራሮችን፣ “ሸፍኑን!” ኰረብታዎችንም፣ “ውደቁብን!” ይላሉ።

9“እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤ በዚያም ጸናችሁ፤ በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ ጦርነት አልጨረሳቸውምን?

10በፈለግሁ ጊዜ እቀጣቸዋለሁ፤ ስለ ድርብ ኀጢአታችሁም ይቀጧቸው ዘንድ፣ በእነርሱ ላይ ይሰበሰባሉ፤

11ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድ፣ እንደ ተገራች ጊደር ነው፤ በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ ቀንበርን አኖራለሁ፤ ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል።

12ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።

13እናንተ ግን ክፋትን ዘራችሁ፤ ኀጢአትንም ዐጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በላችሁ። በራሳችሁ ጒልበት፣ በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና፣

14ሰልማን፣ ቤትአርብኤልን በጦርነት ጊዜ እንዳፈራረሰ፣ እናቶችንም ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ እንደ ፈጠፈጣቸው፣ ሽብር በሕዝብህ ላይ ይመጣል፤ ምሽጎችህም ሁሉ ይፈራርሳሉ፤

15ስለዚህ ቤቴል ሆይ፤ ክፋትሽ ታላቅ ስለ ሆነ፣ በአንቺም ላይ እንደዚሁ ይሆናል፤ ያ ቀን ሲደርስም፣ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።

ማብራሪያ

፲፡፩-፰

የወይን ግንድ ዋጋው ፍሬው ብቻ ነው፤ እስራኤል ግን ፍሬን ሙሉ በሙሉ አላፈራም ነበር። ልቦቻቸው ተከፋፍለው ነበር። እግዚአብሔር የልብ ገዢ ነው፤ ሁሉንም ወይም ከቶውንም አይቀበልም። የልብ ፍሰት ሙሉ በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፣ በብርታት ይፈስ ነበር፤ በፊቱም ያለውን ሁሉ ያወርድ ነበር። ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ቃል ኪዳን አስመሳይ ነበር። የጽድቅም ሂደት እንደ መርዛማ እምቧይ ነበር። ወዮ! እስከ ዛሬም ድረስ የሚታየው ቤተ ክርስቲያን ምንኛ ባዶ ወይን ግንድ ነው! ነገር ግን ምድራዊ ብልጽግና ሁሉ የውሃ አረፋ ክምችት ብቻ ነው፣ በውሃ ላይ እንዳለ አረፋም ቶሎ ይጠፋል። ኃጢአተኞች አሁን እንደ አዳኝ የሚንቁትን ያንን ፈራጅ ከንቱ መጠጊያ ይፈልጋሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያውን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል። አማርኛ ENGNIV Israel was a spreading vine; he brought forth fruit for himself. As his fruit increased, he built more altars; as his l… English BCV እስራኤል ብዙሕ ዝሰፍሐን ብዙሕ ፍረ ዝፈሪ ወይንን እዩ። ከም መጠን ምብዛሕ ፍረኡ፥ ብዙሕ መሰውኢታት ኣብዝሐ፤ ከም መጠን ምፅባቕ ምድሩውን፥ እናመልክዑ ሓወልትታት ሰርሑ። ትግርኛ GAZBIB Warri Israa'elis akka muka waynii of jaallatee ija baay'ee naqatuu ti; hammuma iji hojii isaanii baay'ate iddoo aarsaas… Afaan Oromoo BCV GIZ ዓፀደ ወይን ዘሠረፀ ኤፍሬም ወሠምረ ፍሬሁ፤ ወበከመ ብዝኀ ፍሬሆሙ ከማሁ አብዝኀ መሥዋዕቶሙ ወበአምጣነ ብሔሩ ሐነፁ ሐውልተ። giz GAZGAZ Warri Israa'elis akka muka waynii of jaallatee ija baay'ee naqatuu ti; hammuma iji hojii isaanii baay'ate iddoo aarsaas… Afaan Oromoo BCV aksum እስራኤል ብዙሕ ዝሰፍሐን ብዙሕ ፍረ ዝፈሪ ወይንን እዩ። ከም መጠን ምብዛሕ ፍረኡ፥ ብዙሕ መሰውኢታት ኣብዝሐ፤ ከም መጠን ምፅባቕ ምድሩውን፥ እናመልክዑ ሓወልትታት ሰርሑ። ትግርኛ SWAHSUV Israeli ni mzabibu, utoao matunda yake; kwa kadiri ya wingi wa matunda yake, kwa kadiri iyo hiyo ameongeza madhabahu za… Kiswahili