ወደ ዕብራውያን 10

AMHEVGአማርኛ36 ጥቅሶች4:53 አዳምጥ
አዳምጥ 4:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።

2እንደዚህማ ባይሆን፥ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን?

3ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤

4የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።

5ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ “መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

6በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።

7በዚያን ጊዜ፦ ‘እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ፡’ አልሁ፥ ይላል።”

8በዚህ ላይ፦ “መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፡ በእርሱም ደስ አላለህም፡” ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥

9ቀጥሎ፦ “እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ፡” ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።

10በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።

11ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤

12እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥

13ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።

14አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።

15መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፤

17ብሎ ከተናገረ በኋላ፦ “ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም፡” ይላል።

18የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።

19እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥

21በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥

22ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤

23የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤

24ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤

25በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

26የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥

27የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።

28የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤

29የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?

30በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፡ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።”

31በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

32ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ።

34የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ።

35እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።

36የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።

37ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤

38ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።

39እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

ማብራሪያ

፲፥፩-፲ ሐዋርያው የመገናኛ ድንኳኑና የሲናይ ኪዳን ሥርዓቶች የወንጌል ምሳሌዎችና ምልክቶች ብቻ እንደነበሩ ካሳየ በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ያለማቋረጥ ያቀርቧቸው የነበሩት መሥዋዕቶች አምላኪዎችን ይቅርታን እና የኅሊናቸውን መንጻት በተመለከተ ፍጹም ሊያደርጓቸው እንደማይችሉ ደምድሟል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ መሥዋዕት ሲሆን፣ በተረገመው እንጨት ላይ የሞተው ሞትም ቤዛነት ሲሆን፣ ያ መከራ የተቀበለው ገደብ የሌለው ዋጋ ያለው በመሆኑ፣ በፈቃደኝነት የተቀበላቸው መከራዎችም ገደብ የሌለው ዋጋ ነበራቸው። የማስተስሪያው መሥዋዕት ለመስማማት የሚችል መሆን አለበት፣ በራሱ ፈቃድም ራሱን በኃጢአተኛው ስፍራ ማኖር አለበት፤ ክርስቶስም እንዲህ አደረገ። ክርስቶስ ለሕዝቡ ስላደረገው ሁሉ ምንጩ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድና ጸጋ ነው። የመጣው ጽድቅና በክርስቶስ አንድ ጊዜ የቀረበው መሥዋዕት የዘላለም ኃይል ያላቸው ናቸው፤ መዳኑም ፈጽሞ አይሻርም። ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ፍጹም የማድረግ ኃይል አላቸው፤ ከሚያስተሰርየው ደምም ለመታዘዝ ብርታትና ተነሳሽነትን፣ እንዲሁም ውስጣዊ መጽናናትን ያገኛሉ።

10:11-18 በአዲስ ኪዳን ወይም በወንጌል ዘመን ሙሉና የመጨረሻ ይቅርታ ይገኛል። ይህ በአዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን መካከል ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል። በብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች በተደጋጋሚ መቅረብ ነበረባቸው፤ ከሁሉም በኋላም በእነዚያ አማካኝነት የሚገኘው ይቅርታ የዚህ ዓለም ብቻ ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን፣ አንድ መሥዋዕት ብቻ ለሁሉም ብሔራትና ዘመናት መንፈሳዊ ይቅርታን፣ ወይም በሚመጣው ዓለም ከቅጣት ነፃ መሆንን ለማስገኘት በቂ ነው። ይህ በእርግጥ አዲስ ኪዳን ተብሎ መጥራቱ ተገቢ ነው። የሰው ፈጠራዎች የእግዚአብሔርን ልጅ መሥዋዕት ምትክ አድርገው ለሚወስዱት ሊጠቅሙ እንደሚችሉ ማንም ሊያስብ አይገባም።

እንግዲህ ምን ይቀራል? በእምነት በዚህ መሥዋዕት ተጠቃሚነትን ከመፈለግና፣ የመንፈስ ቅዱስም ቅድሳት ለመታዘዝ ወደሚመራው የነፍሳችን ማኅተም ከመሻት በቀር? ስለዚህም ሕግ በልባችን ተጽፎልን፣ ጻድቅ እንደሆንንና እግዚአብሔርም ኃጢአታችንን ከእንግዲህ ወዲህ እንደማያስታውስ ልናውቅ እንችላለን።

10:19-25 ሐዋርያው የዚህን መልእክት የመጀመሪያ ክፍል ከዘጋ በኋላ፣ ትምህርቱ ለተግባራዊ ዓላማዎች ይተገበራል። አማኞች ወደ እግዚአብሔር መገኘት ክፍት መንገድ ስላገኙ፣ ይህን ልዩ መብት መጠቀም ይገባቸዋል። ክርስቲያኖች እንደዚህ ያሉ ልዩ መብቶችን የሚያገኙበት መንገድና ዘዴ በኢየሱስ ደም ነው፤ እርሱ እንደ ማስተስሪያ መስዋዕት አድርጎ ባቀረበው በዚያ ደም በጎነት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The law is only a shadow of the good things that are coming–not the realities themselves. For this reason it can never,… English BCV ሕጊ፥ ናይቲ ኽመፅእ ዘለዎ ሰናይ ነገር ፅላሎት እምበር፥ ንሱ ባዕሉ ኣይኮነን። በዝ ምኽንያት እዙይ ድማ፥ እቲ በብዓመት ኵልሻዕ ዝቐርብ መስዋእትታት፥ ነቶም ዘቕርብዎ ኸቶ ፍፁማት ክገብሮም … ትግርኛ GAZBIB Seerichi garuu gaadidduu wanta gaggaarii dhufuuf jiran sanaa ti malee, bifa dhugaa isa isaan ittiin mul'atan miti; inni… Afaan Oromoo BCV GIZ እስመ ጽላሎታ ይእቲ ኦሪት ለእንተ ትመጽእ ሠናይት እስመ ኢኮነት ለሊሃ፣ ወበእንተ ዝንቱ አመ ያበውኡ መሥዋዕተ ዘልፈ በኵሉ ዓመት ኢይክል ለሊሁ ግሙራ ፈጽሞ ለእለ ያበውእዎ። giz GAZGAZ Seerichi garuu gaadidduu wanta gaggaarii dhufuuf jiran sanaa ti malee, bifa dhugaa isa isaan ittiin mul'atan miti; inni… Afaan Oromoo BCV aksum ሕጊ፥ ናይቲ ኽመፅእ ዘለዎ ሰናይ ነገር ፅላሎት እምበር፥ ንሱ ባዕሉ ኣይኮነን። በዝ ምኽንያት እዙይ ድማ፥ እቲ በብዓመት ኵልሻዕ ዝቐርብ መስዋእትታት፥ ነቶም ዘቕርብዎ ኸቶ ፍፁማት ክገብሮም … ትግርኛ AMHNIV ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ፣ እውነተኛው አካል አይደለም፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር ያለ ማቋረጥ የሚቀርበው ተደጋጋሚ መሥዋዕት፣ ለአምልኮ የሚቀርቡትን ሰዎች ፍጹ… አማርኛ SWAHSUV Basi torati, kwa kuwa ni kivuli cha mema yatakayokuwa, wala si sura yenyewe ya mambo hayo, kwa dhabihu zile zile wanazo… Kiswahili