ወደ ዕብራውያን 10

AMHNIVአማርኛ39 ጥቅሶች5:59 አዳምጥ
አዳምጥ 5:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ፣ እውነተኛው አካል አይደለም፤ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር ያለ ማቋረጥ የሚቀርበው ተደጋጋሚ መሥዋዕት፣ ለአምልኮ የሚቀርቡትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው ከቶ አይችልም።

2ፍጹም ሊያደርጋቸው ቢችል ኖሮ፣ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረምን? ደግሞም ለአምልኮ የሚቀርቡት ሰዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለሚነጹ፣ በኅሊናቸው ኀጢአተኝነት ባልተሰማቸውም ነበር።

3ነገር ግን እነዚህ መሥዋዕቶች በየዓመቱ ኀጢአትን የሚያስታውሱ ናቸው፤

4ምክንያቱም የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኀጢአትን ማስወገድ አይችልም።

5ስለዚህ ክርስቶስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ ብሎአል፤ “መሥዋዕትንና መባን አልፈለግህም፤ ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

6በሚቃጠል መሥዋዕትና ለኀጢአት በሚቀርብ መሥዋዕት ደስ አልተሰኘህም።

7በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፤ ‘ስለ እኔ በመጽሐፍ እንደ ተጻፈ፣ አምላክ ሆይ፤ እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ።’ ”

8ሕጉ ይህ እንዲደረግ ቢያዝም፣ እርሱ ግን በመጀመሪያ፣ “መሥዋዕትንና መባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም፤ ደስም አልተሰኘህበትም” ይላል።

9ቀጥሎም፣ “እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ፤ ሁለተኛውን ለመመሥረት የመጀመሪያውን ሻረ።

10በዚህ ፈቃድ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካይነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቀረበው መሥዋዕት ተቀድሰናል።

11ካህን ሁሉ በየዕለቱ ቆሞ አገልግሎቱን ያከናውናል፤ ኀጢአትን ማስወገድ ከቶ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች ዘወትር ያቀርባል።

12ይህኛው ካህን ግን አንዱን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል፤

13ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጠላቶቹ የእግሩ መረገጫ እስኪሆኑ ድረስ ይጠብቃል፤

14ምክንያቱም በአንዱ መሥዋዕት እነዚያን የሚቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋል።

15መንፈስ ቅዱስም ስለዚህ ነገር ይመሰክርልናል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላል፤

16“ከዚያም በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።”

17ደግሞም፣ “ኀጢአታቸውንና ዐመፃቸውን፣ ከእንግዲህ አላስብም” ይላል።

18እነዚህ ይቅር ከተባሉ በኋላ ከእንግዲህ ስለ ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት አይኖርም።

19እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በኢየሱስ ደም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ድፍረት አግኝተናል፤

20ይኸውም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል በከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።

21በእግዚአብሔር ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን

22ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።

23የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ።

24እርስ በርሳችንም ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።

25አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ።

26የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆን ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤

27የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

28የሙሴን ሕግ የናቀ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይገደል ነበር።

29ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቈጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል?

30“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል።

31በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው።

32ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ፣ በመከራ ውስጥ በብርቱ ተጋድሎ ጸንታችሁ የቆማችሁበትን የቀድሞውን ዘመን ዐስቡ።

33አንዳንድ ጊዜ በአደባባይ ለስድብና ለስደት ተጋልጣችሁ ነበር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ያለ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር አብራችሁ መከራን ተቀብላችኋል።

34እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ።

35ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።

36የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል፤

37ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ “የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም።

38ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ ነፍሴ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”

39እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።

ማብራሪያ

፲፥፩-፲ ሐዋርያው የመገናኛ ድንኳኑና የሲናይ ኪዳን ሥርዓቶች የወንጌል ምሳሌዎችና ምልክቶች ብቻ እንደነበሩ ካሳየ በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ያለማቋረጥ ያቀርቧቸው የነበሩት መሥዋዕቶች አምላኪዎችን ይቅርታን እና የኅሊናቸውን መንጻት በተመለከተ ፍጹም ሊያደርጓቸው እንደማይችሉ ደምድሟል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ መሥዋዕት ሲሆን፣ በተረገመው እንጨት ላይ የሞተው ሞትም ቤዛነት ሲሆን፣ ያ መከራ የተቀበለው ገደብ የሌለው ዋጋ ያለው በመሆኑ፣ በፈቃደኝነት የተቀበላቸው መከራዎችም ገደብ የሌለው ዋጋ ነበራቸው። የማስተስሪያው መሥዋዕት ለመስማማት የሚችል መሆን አለበት፣ በራሱ ፈቃድም ራሱን በኃጢአተኛው ስፍራ ማኖር አለበት፤ ክርስቶስም እንዲህ አደረገ። ክርስቶስ ለሕዝቡ ስላደረገው ሁሉ ምንጩ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድና ጸጋ ነው። የመጣው ጽድቅና በክርስቶስ አንድ ጊዜ የቀረበው መሥዋዕት የዘላለም ኃይል ያላቸው ናቸው፤ መዳኑም ፈጽሞ አይሻርም። ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ፍጹም የማድረግ ኃይል አላቸው፤ ከሚያስተሰርየው ደምም ለመታዘዝ ብርታትና ተነሳሽነትን፣ እንዲሁም ውስጣዊ መጽናናትን ያገኛሉ።

10:11-18 በአዲስ ኪዳን ወይም በወንጌል ዘመን ሙሉና የመጨረሻ ይቅርታ ይገኛል። ይህ በአዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን መካከል ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል። በብሉይ ኪዳን መሥዋዕቶች በተደጋጋሚ መቅረብ ነበረባቸው፤ ከሁሉም በኋላም በእነዚያ አማካኝነት የሚገኘው ይቅርታ የዚህ ዓለም ብቻ ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን፣ አንድ መሥዋዕት ብቻ ለሁሉም ብሔራትና ዘመናት መንፈሳዊ ይቅርታን፣ ወይም በሚመጣው ዓለም ከቅጣት ነፃ መሆንን ለማስገኘት በቂ ነው። ይህ በእርግጥ አዲስ ኪዳን ተብሎ መጥራቱ ተገቢ ነው። የሰው ፈጠራዎች የእግዚአብሔርን ልጅ መሥዋዕት ምትክ አድርገው ለሚወስዱት ሊጠቅሙ እንደሚችሉ ማንም ሊያስብ አይገባም።

እንግዲህ ምን ይቀራል? በእምነት በዚህ መሥዋዕት ተጠቃሚነትን ከመፈለግና፣ የመንፈስ ቅዱስም ቅድሳት ለመታዘዝ ወደሚመራው የነፍሳችን ማኅተም ከመሻት በቀር? ስለዚህም ሕግ በልባችን ተጽፎልን፣ ጻድቅ እንደሆንንና እግዚአብሔርም ኃጢአታችንን ከእንግዲህ ወዲህ እንደማያስታውስ ልናውቅ እንችላለን።

10:19-25 ሐዋርያው የዚህን መልእክት የመጀመሪያ ክፍል ከዘጋ በኋላ፣ ትምህርቱ ለተግባራዊ ዓላማዎች ይተገበራል። አማኞች ወደ እግዚአብሔር መገኘት ክፍት መንገድ ስላገኙ፣ ይህን ልዩ መብት መጠቀም ይገባቸዋል። ክርስቲያኖች እንደዚህ ያሉ ልዩ መብቶችን የሚያገኙበት መንገድና ዘዴ በኢየሱስ ደም ነው፤ እርሱ እንደ ማስተስሪያ መስዋዕት አድርጎ ባቀረበው በዚያ ደም በጎነት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም። አማርኛ ENGNIV The law is only a shadow of the good things that are coming–not the realities themselves. For this reason it can never,… English BCV ሕጊ፥ ናይቲ ኽመፅእ ዘለዎ ሰናይ ነገር ፅላሎት እምበር፥ ንሱ ባዕሉ ኣይኮነን። በዝ ምኽንያት እዙይ ድማ፥ እቲ በብዓመት ኵልሻዕ ዝቐርብ መስዋእትታት፥ ነቶም ዘቕርብዎ ኸቶ ፍፁማት ክገብሮም … ትግርኛ GAZBIB Seerichi garuu gaadidduu wanta gaggaarii dhufuuf jiran sanaa ti malee, bifa dhugaa isa isaan ittiin mul'atan miti; inni… Afaan Oromoo BCV GIZ እስመ ጽላሎታ ይእቲ ኦሪት ለእንተ ትመጽእ ሠናይት እስመ ኢኮነት ለሊሃ፣ ወበእንተ ዝንቱ አመ ያበውኡ መሥዋዕተ ዘልፈ በኵሉ ዓመት ኢይክል ለሊሁ ግሙራ ፈጽሞ ለእለ ያበውእዎ። giz GAZGAZ Seerichi garuu gaadidduu wanta gaggaarii dhufuuf jiran sanaa ti malee, bifa dhugaa isa isaan ittiin mul'atan miti; inni… Afaan Oromoo BCV aksum ሕጊ፥ ናይቲ ኽመፅእ ዘለዎ ሰናይ ነገር ፅላሎት እምበር፥ ንሱ ባዕሉ ኣይኮነን። በዝ ምኽንያት እዙይ ድማ፥ እቲ በብዓመት ኵልሻዕ ዝቐርብ መስዋእትታት፥ ነቶም ዘቕርብዎ ኸቶ ፍፁማት ክገብሮም … ትግርኛ SWAHSUV Basi torati, kwa kuwa ni kivuli cha mema yatakayokuwa, wala si sura yenyewe ya mambo hayo, kwa dhabihu zile zile wanazo… Kiswahili