መጽሐፈ መክብብ 6

AMHNIVአማርኛ12 ጥቅሶች2:11 አዳምጥ
አዳምጥ 2:11 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከፀሓይ በታች ሌላ ክፉ ነገር አየሁ፤ እርሱም ለሰዎች እጅግ የሚከብድ ነው፤

2ሰው ልቡ የሚሻውን እንዳያጣ፣ እግዚአብሔር ባለጠግነትን፣ ሀብትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ እግዚአብሔር ግን እንዲደሰትበት ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይልቁን ባዕድ ይደሰትበታል። ይህም ከንቱ፣ እጅግም ክፉ ነገር ነው።

3አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሰኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤

4ምክንያቱም በከንቱ ይመጣል፤ በጨለማም ይሄዳል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኖአል።

5ፀሓይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅ እንኳ፣ እርሱ ከዚያ ሰው ይልቅ ዕረፍት አለው፤

6ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ነገር ግን በሀብቱ ደስ ባይሰኝበት ሁሉ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?

7የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም።

8ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው? ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ ትርፉ ምንድን ነው?

9በምኞት ከመቅበዝበዝ፣ በዐይን ማየት ይሻላል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

10አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋር፣ ማንም አይታገልም።

11ቃል በበዛ ቊጥር፤ ከንቱነት ይበዛል፤ ይህ ታዲያ ለሰው ምን ይጠቅማል?

12ሰው በሕይወት ሳለ፣ እንደ ጥላ በሚያልፉት ጥቂትና ከንቱ በሆኑት ቀኖቹ፣ ለሰው መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ከሄደ በኋላስ ከፀሓይ በታች የሚሆነውን ማን ሊነግረው ይችላል?

ማብራሪያ

6:1-6

ሰው ብዙውን ጊዜ ለውጫዊ ደስታው የሚያስፈልገውን ሁሉ አለው፤ ሆኖም ጌታ ለስስት ወይም ለክፉ ዝንባሌዎች አሳልፎ ይሰጠዋልና ያለውን ነገር በመልካም ወይም በሚያስደስት መንገድ መጠቀም አይችልም። በሆነ መንገድ ወይም በሌላ ንብረቶቹ ለባዕድ እጅ ይወድቃሉ፤ ይህ ከንቱነትና ክፉ ደዌ ነው። በዕብራውያን ዘንድ ብዙ ቤተሰብ ትልቅ ምኞትና የከበረ ክብር ነበር፤ ረጅም ዕድሜም በአጠቃላይ የሰው ልጆች ሁሉ ምኞት ነው። እነዚህ ነገሮች ቢጨመሩለትም አንድ ሰው ሀብቱን፣ ቤተሰቡንና ሕይወቱን ሊደሰትበት አይችልም። እንዲህ ያለው ሰው በሕይወቱ ጉዞ ያለ ዓላማ ወይም ጥቅም የተወለደ ይመስላል። ለቅፅበት ብቻ ወደ ሕይወት የገባና በሚቀጥለው ቅፅበት የሚተዋት ሰው ለረጅም ጊዜ ለመሰቃየት ብቻ ከኖረ ሰው የተሻለ ዕጣ ፈንታ አለው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6