ትንቢተ አሞጽ 2

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:16 አዳምጥ
አዳምጥ 3:16 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣ ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና፤

2የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መሐል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።

3ገዧን እደመስሳለሁ፣ አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር እገድላለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤ አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣ በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።

5የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣ በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ።

6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣ ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና።

7የድኾችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ ፍትሕንም ከጭቊኖች ይነጥቃሉ፤ አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፤ እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።

8በመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ፣ በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤ በአምላካቸው ቤት፣ በመቀጫነት የተወሰደውን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

9ቁመቱ እንደ ዝግባ፣ ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረ ቢሆንም፣ አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁት፣ ከላይ ፍሬውን፣ ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።

10“የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣ ከግብፅ አወጣኋችሁ፤ አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።

11ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣ ናዝራውያንንም ከጐልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።

12“እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።

13“እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅ፣ እኔም አደቃችኋለሁ።

14ፈጣኑ አያመልጥም፤ ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።

15ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።

16ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣ በዚያ ቀን ዕራቁታቸውን ይሸሻሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

2:1-8 የልብ ክፉ ምኞቶች በተለያየ መልክ ይገለጣሉ፤ ነገር ግን ጌታ ምግባራችንን ብቻ ሳይሆን የልባችንን ሃሳብም ይመለከታል። በጭካኔ የሚይዙት በጭካኔ ይያዛሉ። ሌሎች አሕዛብ በሰዎች ላይ ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ ሲሆኑ፤ ይሁዳ ግን እግዚአብሔርን ባለማክበሯ ተጠያቂ ሆነች። ይሁዳም የእግዚአብሔርን ሕግ ናቀች፤ እርሱም በጽድቅ ለከባድ ማታለል አሳልፎ ሰጣቸው። አባቶቻቸው የተከተሏቸው ውሸቶችና ጣዖታት መሆናቸው ለኃጢአታቸው ምንም ሰበብ ሊሆናቸው አልቻለም። እጅግ አስከፊ የሆኑ ርኩሰቶችና ታላቅ ጭቆናዎች እግዚአብሔርን እናመልካለን በሚሉ አንዳንድ ሰዎች ተፈጽመዋል። እንዲህ ዓይነቱ ምግባር ብዙዎችን ወደ አለማመንና ወደ አስጸያፊ ጣዖት አምልኮ ይመራል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶምያስን ንጉሥ አጥንት አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞዓብ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። አማርኛ ENGNIV This is what the Lord says: “For three sins of Moab, even for four, I will not turn back my wrath. Because he burned, a… English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ “ኣዕፅምቲ ንጉስ ኤዶምያስ ሓመድ ክሳዕ ዝኸውን ኣቃፂልዎ እዩሞ፥ ስለ ሰለስተ ወይ ስለ ኣርባዕተ ሓጢኣት ሞኣብ፥ መቅሰፍተይ ካብ ምግባር ኣይምለስን። ትግርኛ GAZBIB Amos ammas,“Waaqayyo akka jedhu! “Warri biyya Mo'aab lafee mootii Edoom gubanii nooraa mana diban waan godhataniif, ani… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ በእንተ ሠላስ ኀጢአተ ሞአብ ወበእንተ አርባዕ ኢይመይጥ እስመ አውዐዩ አዕፅምቲሁ ለንጉሠ ኢዶምያ ለግምስስ። giz GAZGAZ Amos ammas,“Waaqayyo akka jedhu! “Warri biyya Mo'aab lafee mootii Edoom gubanii nooraa mana diban waan godhataniif, ani… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ “ኣዕፅምቲ ንጉስ ኤዶምያስ ሓመድ ክሳዕ ዝኸውን ኣቃፂልዎ እዩሞ፥ ስለ ሰለስተ ወይ ስለ ኣርባዕተ ሓጢኣት ሞኣብ፥ መቅሰፍተይ ካብ ምግባር ኣይምለስን። ትግርኛ SWAHSUV Haya ndiyo asemayo Bwana; Kwa makosa matatu ya Moabu, naam, kwa manne, sitaizuia adhabu yake isimpate; kwa sababu aliic… Kiswahili