ትንቢተ አሞጽ 2

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:43 አዳምጥ
አዳምጥ 2:43 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶምያስን ንጉሥ አጥንት አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞዓብ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

2በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤

3ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ሐሰታቸው አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

5በይሁዳ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም አዳራሾች ትበላለች።”

6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጻድቁን ስለ ብር፥ ችጋረኛውንም ስለ አንድ ጥንድ ጫማ ሽጠውታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእስራኤል ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።

7የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፥ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፤ ቅዱሱንም ስሜን ያረክሱ ዘንድ አባትና ልጁ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤

8በመሠዊያውም ሁሉ አጠገብ ለመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ ይተኛሉ፤ በአምላካቸውም ቤት ውስጥ በካሣ የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።

9“እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ኮምበል ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።

10የአሞራዊውንም ምድር ትወርሱ ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፥ በምድረ በዳም አርባ ዓመት መራኋችሁ።

11ከወንድ ልጆቻችሁም ነቢያትን፥ ከጐበዛዝቶቻችሁም ናዝራውያንን አስነሣሁ፤ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ ይህ እንደዚህ አይደለምን?” ይላል እግዚአብሔር።

12“እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም፦ ‘ትንቢትን አትናገሩ፡’ ብላችሁ አዘዛችኋቸው።

13እነሆ፥ ነዶ የተሞላች ሰረገላ እንደምትደቀድቅ እንዲሁ እደቀድቃችኋለሁ።

14ከርዋጪም ሽሽት ይጠፋል፥ ብርቱውም በብርታቱ አይበረታም፥ ኃያሉም ነፍሱን አያድንም፤

15ቀስተኛውም አይቆምም፥ ፈጣኑም አይድንም፥ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም፤

16በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው በዚያ ቀን ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

2:1-8 የልብ ክፉ ምኞቶች በተለያየ መልክ ይገለጣሉ፤ ነገር ግን ጌታ ምግባራችንን ብቻ ሳይሆን የልባችንን ሃሳብም ይመለከታል። በጭካኔ የሚይዙት በጭካኔ ይያዛሉ። ሌሎች አሕዛብ በሰዎች ላይ ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ ሲሆኑ፤ ይሁዳ ግን እግዚአብሔርን ባለማክበሯ ተጠያቂ ሆነች። ይሁዳም የእግዚአብሔርን ሕግ ናቀች፤ እርሱም በጽድቅ ለከባድ ማታለል አሳልፎ ሰጣቸው። አባቶቻቸው የተከተሏቸው ውሸቶችና ጣዖታት መሆናቸው ለኃጢአታቸው ምንም ሰበብ ሊሆናቸው አልቻለም። እጅግ አስከፊ የሆኑ ርኩሰቶችና ታላቅ ጭቆናዎች እግዚአብሔርን እናመልካለን በሚሉ አንዳንድ ሰዎች ተፈጽመዋል። እንዲህ ዓይነቱ ምግባር ብዙዎችን ወደ አለማመንና ወደ አስጸያፊ ጣዖት አምልኮ ይመራል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is what the Lord says: “For three sins of Moab, even for four, I will not turn back my wrath. Because he burned, a… English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ “ኣዕፅምቲ ንጉስ ኤዶምያስ ሓመድ ክሳዕ ዝኸውን ኣቃፂልዎ እዩሞ፥ ስለ ሰለስተ ወይ ስለ ኣርባዕተ ሓጢኣት ሞኣብ፥ መቅሰፍተይ ካብ ምግባር ኣይምለስን። ትግርኛ GAZBIB Amos ammas,“Waaqayyo akka jedhu! “Warri biyya Mo'aab lafee mootii Edoom gubanii nooraa mana diban waan godhataniif, ani… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ በእንተ ሠላስ ኀጢአተ ሞአብ ወበእንተ አርባዕ ኢይመይጥ እስመ አውዐዩ አዕፅምቲሁ ለንጉሠ ኢዶምያ ለግምስስ። giz GAZGAZ Amos ammas,“Waaqayyo akka jedhu! “Warri biyya Mo'aab lafee mootii Edoom gubanii nooraa mana diban waan godhataniif, ani… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ “ኣዕፅምቲ ንጉስ ኤዶምያስ ሓመድ ክሳዕ ዝኸውን ኣቃፂልዎ እዩሞ፥ ስለ ሰለስተ ወይ ስለ ኣርባዕተ ሓጢኣት ሞኣብ፥ መቅሰፍተይ ካብ ምግባር ኣይምለስን። ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣ ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና፤ አማርኛ SWAHSUV Haya ndiyo asemayo Bwana; Kwa makosa matatu ya Moabu, naam, kwa manne, sitaizuia adhabu yake isimpate; kwa sababu aliic… Kiswahili