የሐዋርያት ሥራ 6

AMHEVGአማርኛ15 ጥቅሶች2:18 አዳምጥ
አዳምጥ 2:18 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚህም ወራት ደቀ መዛሙርት እየበዙ ሲሄዱ ከግሪክ አገር መጥተው የነበሩት አይሁድ በይሁዳ ኖረው በነበሩት አይሁድ አንጐራጐሩባቸው፥ በየቀኑ በተሠራው አገልግሎት መበለቶቻቸውን ችላ ይሉባቸው ነበርና።

2አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ “የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

3ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤

4እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።”

5ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።

6በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።

7የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።

8እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።

9የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤

10ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም።

11በዚያን ጊዜ፦ “በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል፥” የሚሉ ሰዎችን አስነሡ።

12ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና።

13“ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤

14ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና” የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ።

15በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት።

ማብራሪያ

6:1-7 እስከዚያው ድረስ ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ልብ ነበሩ፤ ይህ ደግሞ ለክብራቸው በተደጋጋሚ ተመስክሮላቸዋል፤ አሁን ግን ቁጥራቸው በበዛ ጊዜ ማጉረምረም ጀመሩ። የእግዚአብሔር ቃል የሐዋርያትን ሙሉ ሀሳብ፣ እንክብካቤና ጊዜ የሚወስድ በቂ ነገር ነበር። ማዕድ ለማገልገል የተመረጡት ሰዎች በብቃት የተሟሉ መሆን አለባቸው። እነርሱም ይህን አደራ በትክክል ለማስተዳደር አስፈላጊ በሆኑ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ጸጋዎች የተሞሉ፣ የእውነት ሰዎችና ስግብግብነትን የሚጠሉ መሆን አለባቸው። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የተሰማሩ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ጸሎት ለመለኮታዊ ጸጋ ሊሰጡ ይገባል። በጌታ ስም ባረኳቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In those days when the number of disciples was increasing, the Grecian Jews among them complained against the Hebraic J… English BCV በቲ እዋን እቱይ፥ ደቀ መዛሙርት ብቝፅሪ እናበዝሑ ምስ ከዱ፥ እቶም ካብ ግሪክ ዝመፁ ኣይሁድ፥ እተን ናታቶም መበለታት፥ ኣብቲ ዕለታዊ ምዕዳል ምግቢ ሸለል ስለ ዝተብሃላ፥ ኣብ ልዕሊ እቶም … ትግርኛ GAZBIB Bara sana lakkoobsi warra Yesusitti amananii baay'atee, Yihudoonni warri afaan Griikii dubbatan warra afaan Yihudootaa … Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ በዝኁ ሕዝብ ወግዕዝዎሙ እለ እምአረሚ አርድእት ለአይሁድ እስመ ይሬእይዎን ለመበለታቲሆን እንዘ ኢይፀመዳ ኵሎ አሚረ ወያሰትታ ተልእኮቶን። giz GAZGAZ Bara sana lakkoobsi warra Yesusitti amananii baay'atee, Yihudoonni warri afaan Griikii dubbatan warra afaan Yihudootaa … Afaan Oromoo BCV aksum በቲ እዋን እቱይ፥ ደቀ መዛሙርት ብቝፅሪ እናበዝሑ ምስ ከዱ፥ እቶም ካብ ግሪክ ዝመፁ ኣይሁድ፥ እተን ናታቶም መበለታት፥ ኣብቲ ዕለታዊ ምዕዳል ምግቢ ሸለል ስለ ዝተብሃላ፥ ኣብ ልዕሊ እቶም … ትግርኛ AMHNIV የደቀ መዛሙርት ቍጥር እየጨመረ በሄደበት በዚህ ወቅት፣ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በይሁዳ ይኖሩ በነበሩት አይሁድ ላይ አጒረመረሙ፤ ምክንያቱም በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማደል አሠራር … አማርኛ SWAHSUV Hata siku zile wanafunzi walipokuwa wakiongezeka hesabu yao, palikuwa na manung'uniko ya Wayahudi wa Kiyunani juu ya Wa… Kiswahili