የሐዋርያት ሥራ 6

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:14 አዳምጥ
አዳምጥ 3:14 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የደቀ መዛሙርት ቍጥር እየጨመረ በሄደበት በዚህ ወቅት፣ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በይሁዳ ይኖሩ በነበሩት አይሁድ ላይ አጒረመረሙ፤ ምክንያቱም በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማደል አሠራር ላይ ከእነርሱ ወገን የሆኑት መበለቶች ችላ ተብለው ነበር።

2ስለዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሌሎችን ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እኛ የማእዱን አገልግሎት ለማስተናገድ ስንል የእግዚአብሔርን ቃል አገልግሎት መተው አይገባንም።

3ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ መካከል በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ለመሆናቸው የተመሰከረላቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ፤ ይህን ኀላፊነት ለእነርሱ እንሰጣለን፤

4እኛ ግን በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንተጋለን።”

5አባባሉ ሁላቸውን ደስ አሰኘ፤ በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን፣ እንዲሁም ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጰርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ።

6እነዚህንም አምጥተው ሐዋርያት ፊት አቀረቡአቸው፤ እነርሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።

7የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ የደቀ መዛሙርቱም ቍጥር በኢየሩሳሌም እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት የታዘዙ ሆኑ።

8በዚህ ጊዜ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን ያደርግ ነበር።

9“የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ተብሎ የሚጠራው ምኵራብ አባላት የሆኑ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ እንዲሁም ከኪልቅያና ከእስያ አውራጃዎች የመጡ ሰዎችም ተቃውሞ አስነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ጀመር፤

10ይሁን እንጂ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።

11ስለዚህ፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አዘጋጁ።

12በዚህ ሁኔታ ሕዝቡን፣ የአገር ሽማግሌዎቹንና የሕግ መምህራኑን በማነሣሣት፣ እስጢፋኖስን አስይዘው በአይሁድ ሸንጎ ፊት አቀረቡት፤

13እንዲህ ብለው የሚመሰክሩ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ “ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራና በሕጉ ላይ የስድብ ቃል መናገሩን በፍጹም አልተወም፤

14ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።”

15በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኵር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው።

ማብራሪያ

6:1-7 እስከዚያው ድረስ ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ልብ ነበሩ፤ ይህ ደግሞ ለክብራቸው በተደጋጋሚ ተመስክሮላቸዋል፤ አሁን ግን ቁጥራቸው በበዛ ጊዜ ማጉረምረም ጀመሩ። የእግዚአብሔር ቃል የሐዋርያትን ሙሉ ሀሳብ፣ እንክብካቤና ጊዜ የሚወስድ በቂ ነገር ነበር። ማዕድ ለማገልገል የተመረጡት ሰዎች በብቃት የተሟሉ መሆን አለባቸው። እነርሱም ይህን አደራ በትክክል ለማስተዳደር አስፈላጊ በሆኑ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ጸጋዎች የተሞሉ፣ የእውነት ሰዎችና ስግብግብነትን የሚጠሉ መሆን አለባቸው። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የተሰማሩ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ጸሎት ለመለኮታዊ ጸጋ ሊሰጡ ይገባል። በጌታ ስም ባረኳቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚህም ወራት ደቀ መዛሙርት እየበዙ ሲሄዱ ከግሪክ አገር መጥተው የነበሩት አይሁድ በይሁዳ ኖረው በነበሩት አይሁድ አንጐራጐሩባቸው፥ በየቀኑ በተሠራው አገልግሎት መበለቶቻቸውን ችላ ይሉባቸው … አማርኛ ENGNIV In those days when the number of disciples was increasing, the Grecian Jews among them complained against the Hebraic J… English BCV በቲ እዋን እቱይ፥ ደቀ መዛሙርት ብቝፅሪ እናበዝሑ ምስ ከዱ፥ እቶም ካብ ግሪክ ዝመፁ ኣይሁድ፥ እተን ናታቶም መበለታት፥ ኣብቲ ዕለታዊ ምዕዳል ምግቢ ሸለል ስለ ዝተብሃላ፥ ኣብ ልዕሊ እቶም … ትግርኛ GAZBIB Bara sana lakkoobsi warra Yesusitti amananii baay'atee, Yihudoonni warri afaan Griikii dubbatan warra afaan Yihudootaa … Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ በዝኁ ሕዝብ ወግዕዝዎሙ እለ እምአረሚ አርድእት ለአይሁድ እስመ ይሬእይዎን ለመበለታቲሆን እንዘ ኢይፀመዳ ኵሎ አሚረ ወያሰትታ ተልእኮቶን። giz GAZGAZ Bara sana lakkoobsi warra Yesusitti amananii baay'atee, Yihudoonni warri afaan Griikii dubbatan warra afaan Yihudootaa … Afaan Oromoo BCV aksum በቲ እዋን እቱይ፥ ደቀ መዛሙርት ብቝፅሪ እናበዝሑ ምስ ከዱ፥ እቶም ካብ ግሪክ ዝመፁ ኣይሁድ፥ እተን ናታቶም መበለታት፥ ኣብቲ ዕለታዊ ምዕዳል ምግቢ ሸለል ስለ ዝተብሃላ፥ ኣብ ልዕሊ እቶም … ትግርኛ SWAHSUV Hata siku zile wanafunzi walipokuwa wakiongezeka hesabu yao, palikuwa na manung'uniko ya Wayahudi wa Kiyunani juu ya Wa… Kiswahili