የሐዋርያት ሥራ 24

AMHNIVአማርኛ27 ጥቅሶች4:28 አዳምጥ
አዳምጥ 4:28 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከአምስት ቀን በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በጳውሎስም ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዡ አቀረቡ።

2ጳውሎስ ተጠርቶ በቀረበ ጊዜ፣ ጠርጠሉስ እንዲህ ሲል ክሱን አቀረበ፤ “ክቡር ፊልክስ ሆይ፤ በአንተ ዘመን ሰላም ለብዙ ጊዜ ሰፍኖልናል፤ አርቆ አስተዋይነትህም ለዚህ ሕዝብ መሻሻልን አስገኝቶለታል፤

3በየቦታውና በየጊዜው ይህን ውለታ በታላቅ ምስጋና እንቀበላለን።

4ነገር ግን ይበልጥ እንዳላደክምህ፣ በአጭሩ እንድትሰማን መልካም ፈቃድህን እለምንሃለሁ።

5“ይህ ሰው፣ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ መካከል በሽታ ሆኖ ሁከት የሚያስነሣ፣ ደግሞም የናዝራውያን ወገን ቀንደኛ መሪ ሆኖ አግኝተነዋል።

6ከዚህም በላይ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር አግኝተን ያዝነው። በሕጋችንም መሠረት ልንፈርድበት አስበን ነበር፤

7ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው፤ ከሳሾቹም ወደ አንተ እንዲመጡ አዘዘ።

8እንግዲህ አንተ ራስህ መርምረኸው እርሱን የከሰስንበትን ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን ልታረጋግጥ ትችላለህ።”

9አይሁድም ነገሩን እንደ ተባለው መሆኑን በመደገፍ በክሱ ተባበሩ።

10አገረ ገዡም እንዲናገር በእጁ ምልክት በሰጠው ጊዜ፣ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ የመከላከያ መልሴን የማቀርበው በደስታ ነው።

11ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣሁት ከዐሥራ ሁለት ቀን በፊት መሆኑን አንተው ራስህ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላለህ።

12ከሳሾቼም በቤተ መቅደስ ከማንም ጋር ስከራከር ወይም በምኵራብ ወይም በከተማ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ሕዝብን ሳነሣሣ አላገኙኝም።

13አሁንም ለተከሰስሁበት ነገር ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም።

14ይሁን እንጂ፣ እነርሱ ኑፋቄ በሚሉት በጌታ መንገድ የአባቶቻችንን አምላክ አመልካለሁ፤ በሕጉ የታዘዘውንና በነቢያት የተጻፈውን ሁሉ አምናለሁ፤

15ደግሞም እንደነዚህ ሰዎች ሁሉ፣ ጻድቃንና ኀጥአን ከሙታን እንደሚነሡ በእግዚአብሔር ተስፋ አለኝ።

16ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ንጹሕ ኅሊና እንዲኖረኝ ሁልጊዜ እጥራለሁ።

17“ከብዙ ዓመት በኋላም፣ ለድኻው ወገኔ ምጽዋትና መባ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም መጣሁ።

18እነርሱም በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዐት ፈጽሜ ይህንኑ ሳደርግ አገኙኝ፤ የሕዝብ ሁካታ ወይም ረብሻ አልነበረም።

19ነገር ግን ክስ ካላቸው አንተ ፊት ቀርበው ሊከሱ የሚገባቸው ከእስያ አውራጃ የመጡ አንዳንድ አይሁድ አሉ፤

20ወይም በዚህ ያሉት እነዚህ በሸንጎው ፊት ቀርቤ በነበረበት ጊዜ ያገኙብኝ ወንጀል ካለ ይናገሩ፤

21በመካከላቸው በቆምሁበት ጊዜ ስለ ሙታን ትንሣኤ ከተናገርሁት አንድ ነገር በስተቀር ዛሬ ተከስሼ የቀረብሁበት ሌላ ነገር የለም።”

22ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስዮስ ሲመጣ ለጒዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው።

23ከዚያም ለጳውሎስ መጠነኛ ነጻነት እየሰጠ እንዲጠብቀውና ወዳጆቹም ገብተው እንዲጠይቁት ፈቃድ እንዲሰጣቸው የመቶ አለቃውን አዘዘው።

24ከጥቂት ቀን በኋላ፣ ፊልክስ ከአይሁዳዊት ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ማመን ሲናገር አዳመጠው።

25ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በሚናገርበት ጊዜ ግን ፊልክስ ፈርቶ፣ “ለጊዜው ይህ ይበቃል፤ ወደ ፊት ሲመቸኝ አስጠራሃለሁ፤ አሁን ልትሄድ ትችላለህ” አለው።

26ደግሞም ከጳውሎስ ጉቦ ለመቀበል ተስፋ ያደርግ ስለ ነበር፣ በየጊዜው እያስጠራ ያነጋግረው ነበር።

27ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላም፣ ፊልክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ ፊልክስም አይሁድን ለማስደሰት ሲል፣ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

ማብራሪያ

ምዕራፍ 24 ከቍጥር 1-9። እነሆ የታላላቅ ሰዎች መከራ፡ አገልግሎታቸው ከመጠን በላይ ሲመሰገን እና ስለ ስህተቶቻቸው በታማኝነት በጭራሽ በማይነገራቸው ጊዜ ታላቅ መከራ ነው። በዚህም እንደ ፌሊክስ በክፋት ይጠነክራሉ እንዲሁም ይበረታታሉ።

የእግዚአብሔር ነቢያት አገሪቱን የሚያውኩ ተብለው ተወንጅለዋል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሕዝቡን አሳሳተ ተብሎ ተወነጀለ፤ ልክ እንደዚሁም ተመሳሳይ ክሶች በጳውሎስ ላይ ቀርበዋል። የሰዎች ራስ ወዳድነትና ክፉ ስሜቶች ወደፊት ይገፋፋቸዋል፤ የንግግር ውበትና ኃይልም ብዙውን ጊዜ ሰዎችን ከእውነት ለማሳትና ለአድሏዊነት ጥቅም ላይ ውለዋል። በጠርጡሎስ ንግግር ከተገለጹበት መንገድ ጋር ሲነጻጸር፣ የጳውሎስና የፌሊክስ ማንነቶች በፍርድ ቀን ምንኛ የተለዩ ሆነው ይታያሉ!

ክርስቲያኖች የሰዎችን ውዳሴ ከፍ አድርገው እንዳይመለከቱ ወይም ዓመፀኞች ሰዎች በሚሰነዝሩት የስድብ ቃል እንዳይታወኩ። እነዚያም እጅግ ክፉ የሆኑትን የሰውን ዘር እንደ አማልክት አድርገው ይገልጻሉ፤ የምድርን ምርጦች ደግሞ እንደ ወረርሽኝና ሁከት ፈጣሪዎች ይወክላሉ።

24:10-21 ጳውሎስ ስለ ራሱ ትክክለኛውን ነገር ተናገረ፣ ይህም ከወንጀል ያነጻው ሲሆን በእርሱ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እውነተኛ ምክንያትም ያሳያል። አንድ መልካም ነገር መጥፎ ስም ስላለው ብቻ ከእርሱ ፈጽሞ አንገፋ። እግዚአብሔርን ስናመልክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አድርገን ወደ እርሱ መመልከት እንዲሁም ከቅዱሳት መጻሕፍት ውጪ ሌላ የእምነት ወይም የአኗኗር መለኪያ አለማድረግ በጣም የሚያጽናና ነው። ይህም ወደ መጨረሻው ፍርድ የሚሆን ትንሣኤ እንደሚኖር ያሳያል። ነቢያትና ትምህርቶቻቸው በፍሬዎቻቸው ሊመረመሩ ይገባል። የጳውሎስ ዓላማ ከበደል ነጻ የሆነ ሕሊና እንዲኖረው ነበር። ትጋቱና ጥረቱ ከብዙ ነገሮች መታቀብና ሁልጊዜም በሃይማኖታዊ ልምምዶች መብዛት ነበር፤ ይኸውም ወደ እግዚአብሔርም ሆነ ወደ ሰው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት። አማርኛ ENGNIV Five days later the high priest Ananias went down to Caesarea with some of the elders and a lawyer named Tertullus, and… English BCV ድሕሪ ሓሙሽተ መዓልቲ፥ ሓናንያ እቲ ሊቀ ካህናት፥ ምስ ሽማግለታትን ጠርጠሉስ ምስ ዝበሃል ሓደ ወዳኢ ነገርን ወረደ፤ ንሳቶም ድማ፥ ንጳውሎስ ኣብ ቅድሚ እቲ ሹም ከሰስዎ። ትግርኛ GAZBIB Guyyoota shan booddee Ananiiyaas angafni lubootaa, maanguddootaa fi nama seera falmuuf Xerxilos jedhamu tokkoo wajjin g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአመ ኀሙስ ዕለት ወረደ ሐናንያ ሊቀ ካህናት ምስለ ረበናት ወአሐዱ ዐቃቤ ነቢብ ዘስሙ ጠርጠሉስ ወአስተዋደይዎ ለጳውሎስ ኀበ መልአክ። giz GAZGAZ Guyyoota shan booddee Ananiiyaas angafni lubootaa, maanguddootaa fi nama seera falmuuf Xerxilos jedhamu tokkoo wajjin g… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪ ሓሙሽተ መዓልቲ፥ ሓናንያ እቲ ሊቀ ካህናት፥ ምስ ሽማግለታትን ጠርጠሉስ ምስ ዝበሃል ሓደ ወዳኢ ነገርን ወረደ፤ ንሳቶም ድማ፥ ንጳውሎስ ኣብ ቅድሚ እቲ ሹም ከሰስዎ። ትግርኛ SWAHSUV Baada ya siku tano, Anania, Kuhani Mkuu, akatelemka na baadhi ya wazee pamoja naye, na msemi mmoja, Tertulo, nao wakamw… Kiswahili