የሐዋርያት ሥራ 24

AMHEVGአማርኛ25 ጥቅሶች3:56 አዳምጥ
አዳምጥ 3:56 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት።

2በተጠራም ጊዜ ጠርጠሉስ ይከሰው ዘንድ ጀመረ እንዲህ እያለ፦ “ክቡር ፊልክስ ሆይ፥ በአንተ በኩል ብዙ ሰላም ስለምናገኝ ለዚህም ሕዝብ በአሳብህ በየነገሩ በየስፍራውም መልካም መሻሻል ስለሚሆንለት፥ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን።

4ነገር ግን እጅግ እንዳላቆይህ በቸርነትህ በአጭሩ ትሰማን ዘንድ እለምንሃለሁ።

5ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤

6መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፥ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።

7ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል ከእጃችን ወሰደው፥

8ከሳሾቹንም ወደ አንተ ይመጡ ዘንድ አዘዘ፤ አንተም ራስህ እርሱን መርምረህ እኛ ስለምንከስበት ነገር ሁሉ ልታውቅ ትችላለህ።”

9አይሁድም ደግሞ፦ “ይህ ነገር እንዲሁ ነው፡” እያሉ ተስማሙ።

10ገዡም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ መለሰ እንዲህ ሲል፦ “ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደ ሆንህ አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤

11እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከአሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ።

12ከአንድም ስንኳ ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም ቢሆን አላገኙኝም።

13አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።

14ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤

15እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ።

16ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።

17ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤

18ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።

19ነገር ግን በእኔ ላይ ነገር ያላቸው እንደ ሆነ፥ በፊትህ መጥተው ይከሱኝ ዘንድ የሚገባቸው ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ አሉ።

20ወይም በመካከላቸው ቆሜ፦ ‘ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል’ ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊት ቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዓመፃ ያገኙ እንደ ሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ።”

22ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፡” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።

23የመቶውንም አለቃ ጳውሎስን ሲጠብቅ እንዲያደላለት፥ ከወዳጆቹም ማንም ሲያገለግለው ወይም ወደ እርሱ ሲመጣ እንዳይከለክልበት አዘዘው።

24ከጥቂት ቀንም በኋላ ፊልክስ አይሁዳዊት ከነበረች ድሩሲላ ከሚሉአት ከሚስቱ ጋር መጥቶ ጳውሎስን አስመጣ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም ስለ ማመን የሚናገረውን ሰማው።

25እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኵነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ፦ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ” ብሎ መለሰለት።

26ያን ጊዜም ደግሞ እንዲፈታው ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ አደረገ፤ ስለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ እያስመጣ ያነጋግረው ነበር።

27ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ጶርቅዮስ ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።

ማብራሪያ

ምዕራፍ 24 ከቍጥር 1-9። እነሆ የታላላቅ ሰዎች መከራ፡ አገልግሎታቸው ከመጠን በላይ ሲመሰገን እና ስለ ስህተቶቻቸው በታማኝነት በጭራሽ በማይነገራቸው ጊዜ ታላቅ መከራ ነው። በዚህም እንደ ፌሊክስ በክፋት ይጠነክራሉ እንዲሁም ይበረታታሉ።

የእግዚአብሔር ነቢያት አገሪቱን የሚያውኩ ተብለው ተወንጅለዋል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሕዝቡን አሳሳተ ተብሎ ተወነጀለ፤ ልክ እንደዚሁም ተመሳሳይ ክሶች በጳውሎስ ላይ ቀርበዋል። የሰዎች ራስ ወዳድነትና ክፉ ስሜቶች ወደፊት ይገፋፋቸዋል፤ የንግግር ውበትና ኃይልም ብዙውን ጊዜ ሰዎችን ከእውነት ለማሳትና ለአድሏዊነት ጥቅም ላይ ውለዋል። በጠርጡሎስ ንግግር ከተገለጹበት መንገድ ጋር ሲነጻጸር፣ የጳውሎስና የፌሊክስ ማንነቶች በፍርድ ቀን ምንኛ የተለዩ ሆነው ይታያሉ!

ክርስቲያኖች የሰዎችን ውዳሴ ከፍ አድርገው እንዳይመለከቱ ወይም ዓመፀኞች ሰዎች በሚሰነዝሩት የስድብ ቃል እንዳይታወኩ። እነዚያም እጅግ ክፉ የሆኑትን የሰውን ዘር እንደ አማልክት አድርገው ይገልጻሉ፤ የምድርን ምርጦች ደግሞ እንደ ወረርሽኝና ሁከት ፈጣሪዎች ይወክላሉ።

24:10-21 ጳውሎስ ስለ ራሱ ትክክለኛውን ነገር ተናገረ፣ ይህም ከወንጀል ያነጻው ሲሆን በእርሱ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እውነተኛ ምክንያትም ያሳያል። አንድ መልካም ነገር መጥፎ ስም ስላለው ብቻ ከእርሱ ፈጽሞ አንገፋ። እግዚአብሔርን ስናመልክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አድርገን ወደ እርሱ መመልከት እንዲሁም ከቅዱሳት መጻሕፍት ውጪ ሌላ የእምነት ወይም የአኗኗር መለኪያ አለማድረግ በጣም የሚያጽናና ነው። ይህም ወደ መጨረሻው ፍርድ የሚሆን ትንሣኤ እንደሚኖር ያሳያል። ነቢያትና ትምህርቶቻቸው በፍሬዎቻቸው ሊመረመሩ ይገባል። የጳውሎስ ዓላማ ከበደል ነጻ የሆነ ሕሊና እንዲኖረው ነበር። ትጋቱና ጥረቱ ከብዙ ነገሮች መታቀብና ሁልጊዜም በሃይማኖታዊ ልምምዶች መብዛት ነበር፤ ይኸውም ወደ እግዚአብሔርም ሆነ ወደ ሰው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Five days later the high priest Ananias went down to Caesarea with some of the elders and a lawyer named Tertullus, and… English BCV ድሕሪ ሓሙሽተ መዓልቲ፥ ሓናንያ እቲ ሊቀ ካህናት፥ ምስ ሽማግለታትን ጠርጠሉስ ምስ ዝበሃል ሓደ ወዳኢ ነገርን ወረደ፤ ንሳቶም ድማ፥ ንጳውሎስ ኣብ ቅድሚ እቲ ሹም ከሰስዎ። ትግርኛ GAZBIB Guyyoota shan booddee Ananiiyaas angafni lubootaa, maanguddootaa fi nama seera falmuuf Xerxilos jedhamu tokkoo wajjin g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአመ ኀሙስ ዕለት ወረደ ሐናንያ ሊቀ ካህናት ምስለ ረበናት ወአሐዱ ዐቃቤ ነቢብ ዘስሙ ጠርጠሉስ ወአስተዋደይዎ ለጳውሎስ ኀበ መልአክ። giz GAZGAZ Guyyoota shan booddee Ananiiyaas angafni lubootaa, maanguddootaa fi nama seera falmuuf Xerxilos jedhamu tokkoo wajjin g… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪ ሓሙሽተ መዓልቲ፥ ሓናንያ እቲ ሊቀ ካህናት፥ ምስ ሽማግለታትን ጠርጠሉስ ምስ ዝበሃል ሓደ ወዳኢ ነገርን ወረደ፤ ንሳቶም ድማ፥ ንጳውሎስ ኣብ ቅድሚ እቲ ሹም ከሰስዎ። ትግርኛ AMHNIV ከአምስት ቀን በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በጳውሎስም ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዡ አቀረቡ። አማርኛ SWAHSUV Baada ya siku tano, Anania, Kuhani Mkuu, akatelemka na baadhi ya wazee pamoja naye, na msemi mmoja, Tertulo, nao wakamw… Kiswahili