2ኛ ነገሥት 20

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:43 አዳምጥ
አዳምጥ 4:43 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል” አለው።

2ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

3“እግዚአብሔር ሆይ፤ በታማኝነትና በፍጹም ልብ በፊትህ እንደሄድሁ፣ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ አስብ፤” ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።

4ኢሳይያስ የመካከለኛውን አደባባይ አልፎ ከመሄዱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤

5“ተመለስና የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፣ እፈውስሃለሁ። ከዛሬ ሦስት ቀን በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤

6በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”

7ከዚያም ኢሳይያስ፣ “ትኵስ የበለስ ጥፍጥፍ አዘጋጁ” አላቸው፤ እነርሱም አዘጋጅተው ዕባጩ ላይ አደረጉለት፤ ተፈወሰም።

8ሕዝቅያስም፣ “እግዚአብሔር እኔን ስለ መፈወሱ፣ ከሦስት ቀን በኋላም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስለ መውጣቴ ምልክቱ ምንድን ነው?” ሲል ኢሳይያስን ጠየቀው።

9ኢሳይያስም፣ “እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም ምልክቱ ይህ ነው፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይቅደምን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ?” ሲል ጠየቀው።

10ሕዝቅያስም መልሶ፣ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት መሄዱ ቀላል ነገር ነው፤ ይልቁን ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ” አለ።

11ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አካዝ በሠራው ደረጃ ላይ የወረደውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው እንዲመለስ አደረገ።

12በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመም ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ገጸ በረከት ለሕዝቅያስ ላከለት።

13ሕዝቅያስም መልክተኞቹን ተቀብሎ በዕቃ ቤቱ ያለውን ሁሉ ብሩን፣ ወርቁን ቅመማ ቅመሙንና ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን ዘይት የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤቱንና በቀረውም ግምጃ ቤት ያለውን በሙሉ አሳያቸው። በቤተ መንግሥቱም ሆነ በመላው ግዛቱ ሕዝቅያስ ሳያሳያቸው የቀረ ምንም ነገር አልነበረም።

14ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ ሄዶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? የመጡትስ ከወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም መልሶ፣ “የመጡት ከሩቅ አገር ከባቢሎን ነው” አለው።

15ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ምን ምን አዩ?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በግምጃ ቤቶቼ ሳላሳያቸው የቀረ ምንም ነገር የለም” አለ።

16ከዚያም ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤

17በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት በሙሉ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ በርግጥ ይመጣል፤ አንዳች የሚቀር ነገር የለም ይላል እግዚአብሔር።

18የሥጋህ ቁራጭ የዐጥንትህ ፍላጭ ከሚሆኑት፣ ከምትወልዳቸው ልጆችህ አንዳንዶቹ በምርኮ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎንም ቤተ መንግሥት ጃንደረቦች ይሆናሉ።”

19ሕዝቅያስም፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ፤ “እኔ እስካለሁ ድረስ ሰላምና ጸጥታ ከተገኘ የሆነው ይሁን” ብሎ አስቦአልና።

20በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ ኵሬውንና ውሃውን ወደ ከተማዪቱ ያመጣበትን የመሬት ለመሬት ቦይ እንዴት አድርጎ እንደ ሠራው በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

21ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ምናሴም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

ማብራሪያ

20:1-11 ሕዝቅያስ የአሦር ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በከበበበት በዚያው ዓመት ሞት የሚያደርስ ሕመም ታመመ። ሕዝቅያስ ለሞት እንዲዘጋጅ የሚያስጠነቅቅ መልእክት በኢሳይያስ አማካኝነት ተላከለት። ጸሎት ለሞት ከሚደረጉ ምርጥ ዝግጅቶች አንዱ ነው፤ ምክንያቱም በእርሱ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ኃይልንና ጸጋን እናገኛለን፤ ይህም በጎ ፍጻሜ እንድናገኝ ያስችለናል። እጅግ አለቀሰ፤ አንዳንዶች ከዚህ በመነሳት መሞት አልፈለገም ብለው ይገምታሉ፤ ነፍስና ሥጋ ሲለያዩ መፍራት የሰው ተፈጥሮ ነው። በሕዝቅያስ ሁኔታም ውስጥ ለየት ያለ ነገር ነበር፤ በአገልግሎቱ ከፍተኛ ፍሬ በሚያፈራበት ጊዜ ላይ ነበር። የሕዝቅያስ ጸሎት (ኢሳ. 38 ይመልከቱ) እንባዎቹን ይተርጉምልን፤ በዚያ ጸሎት ውስጥ እስራት ወይም ሥቃይ ካለው ከሞት ፍርሃት ጋር የሚመሳሰል ምንም ነገር የለም። የሕዝቅያስ አምልኮተ እግዚአብሔር የሕመሙን አልጋ ቀለል አደረገለት። አቤቱ፥ አሁን አስበኝ፤ እግዚአብሔር በማንኛውም ነገር በእኛ ሊታወስ እንደሚገባው አድርጎ አይናገርም፤ ወይም ደግሞ ዋጋ እንደ ተገባው ሊጠየቅ እንደሚችል አድርጎ አይደለም፤ የምሕረትና የጸጋ መግዣ የክርስቶስ ጽድቅ ብቻ ነው። ሕዝቅያስ፥ ጌታ ሆይ፥ ሕይወቴን አትርፍልኝ ብሎ አይጸልይም፤ ይልቁንም፥ ጌታ ሆይ፥ አስበኝ ይላል፤ ብኖርም ባልኖርም የአንተ ልሁን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያም ወራት ሕዝቅያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል፡ አለው። አማርኛ ENGNIV In those days Hezekiah became ill and was at the point of death. The prophet Isaiah son of Amoz went to him and said, “… English BCV በቲ ጊዜ እቱይ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኽመውት ቀረበ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ድማ ናብኡ መፂኡ “ንስኻ ኽትመውት ኢኻ እምበር፥ ኣይትሓውን ኢኻ እሞ ቤትካ ኣመዓራሪ ይብል ኣሎ እግዚኣብሄር” ኢሉ… ትግርኛ GAZBIB Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas raajichi ilmi Amos gara isaa dhaqee,“Waaqayyo,“Ati in duuta mal… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ደወየ ሕዝቅያስ ወበጽሐ ለመዊት፤ ወቦአ ኢሳይያስ ነቢይ ወልደ አሞጽ ኀቤሁ፤ ወይቤሎ፦ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሥራዕ ቤተከ እስመ ትመውት ወኢተሐዩ። giz GAZGAZ Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas raajichi ilmi Amos gara isaa dhaqee,“Waaqayyo,“Ati in duuta mal… Afaan Oromoo BCV aksum በቲ ጊዜ እቱይ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኽመውት ቀረበ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ድማ ናብኡ መፂኡ “ንስኻ ኽትመውት ኢኻ እምበር፥ ኣይትሓውን ኢኻ እሞ ቤትካ ኣመዓራሪ ይብል ኣሎ እግዚኣብሄር” ኢሉ… ትግርኛ SWAHSUV Siku hizo Hezekia akaugua, akawa katika hatari ya kufa. Isaya, nabii, mwana wa Amozi, akamjia akamwambia, Bwana asema h… Kiswahili