2ኛ ነገሥት 20

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች3:47 አዳምጥ
አዳምጥ 3:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያም ወራት ሕዝቅያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል፡ አለው።

2ፊቱንም ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦

3አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ።

4ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ከተማ አደባባይ ሳይደርስ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦

5ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።

6በዕድሜህም ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔም ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ።

7ኢሳይስም፦ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡልኝ፡ አለ፤ አምጥተውም በእባጩ ላይ አደርጉለት፥ እርሱም ተፈወሰ።

8ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ፥ እኔስ በሦስተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት እንድወጣ ምልክቱ ምንድር ነው? አለው።

9ኢሳይያስም፦ እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፤ ጥላው አሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሄድ ዘንድ ወይም አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ ዘንድ ትወድዳለህን? አለ።

10ሕዝቅያስም፦ ጥላው አሥር ደረጃ ቢጨምር ቀላል ነገር ነው፤ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ጥላው አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ፡ አለው።

11ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ጥላውንም በአካዝ የጥላ ስፍራ ሰዓት ላይ በወረደበት መንገድ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ መለሰው።

12በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ እንደ ታመመ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ወደ ሕዝቅያስ ላከ።

13ሕዝቅያስም ደስ አለው፥ ግምጃ ቤቱንም ሁሉ፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።

14ነቢዩም ኢሳያሳ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ? አለው። ሕዝቅያስም፦ ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡ፡ አለው።

15እርሱም፦ በቤትህ ያዩት ምንድር ነው? አለው፤ ሕዝቅያስም፦ በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም፡ አለው።

16ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።

17እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።

18ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ፡ አለው።

19ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፦ የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው፡ አለው። ደግሞም፦ በዘመኔ ሰላምና እውነት የሆነ እንደ ሆነ መልካም አይደለምን? አለ።

20የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ጭከናውም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውንም እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማይቱ እንዳመጣ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

21ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማብራሪያ

20:1-11 ሕዝቅያስ የአሦር ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በከበበበት በዚያው ዓመት ሞት የሚያደርስ ሕመም ታመመ። ሕዝቅያስ ለሞት እንዲዘጋጅ የሚያስጠነቅቅ መልእክት በኢሳይያስ አማካኝነት ተላከለት። ጸሎት ለሞት ከሚደረጉ ምርጥ ዝግጅቶች አንዱ ነው፤ ምክንያቱም በእርሱ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ኃይልንና ጸጋን እናገኛለን፤ ይህም በጎ ፍጻሜ እንድናገኝ ያስችለናል። እጅግ አለቀሰ፤ አንዳንዶች ከዚህ በመነሳት መሞት አልፈለገም ብለው ይገምታሉ፤ ነፍስና ሥጋ ሲለያዩ መፍራት የሰው ተፈጥሮ ነው። በሕዝቅያስ ሁኔታም ውስጥ ለየት ያለ ነገር ነበር፤ በአገልግሎቱ ከፍተኛ ፍሬ በሚያፈራበት ጊዜ ላይ ነበር። የሕዝቅያስ ጸሎት (ኢሳ. 38 ይመልከቱ) እንባዎቹን ይተርጉምልን፤ በዚያ ጸሎት ውስጥ እስራት ወይም ሥቃይ ካለው ከሞት ፍርሃት ጋር የሚመሳሰል ምንም ነገር የለም። የሕዝቅያስ አምልኮተ እግዚአብሔር የሕመሙን አልጋ ቀለል አደረገለት። አቤቱ፥ አሁን አስበኝ፤ እግዚአብሔር በማንኛውም ነገር በእኛ ሊታወስ እንደሚገባው አድርጎ አይናገርም፤ ወይም ደግሞ ዋጋ እንደ ተገባው ሊጠየቅ እንደሚችል አድርጎ አይደለም፤ የምሕረትና የጸጋ መግዣ የክርስቶስ ጽድቅ ብቻ ነው። ሕዝቅያስ፥ ጌታ ሆይ፥ ሕይወቴን አትርፍልኝ ብሎ አይጸልይም፤ ይልቁንም፥ ጌታ ሆይ፥ አስበኝ ይላል፤ ብኖርም ባልኖርም የአንተ ልሁን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In those days Hezekiah became ill and was at the point of death. The prophet Isaiah son of Amoz went to him and said, “… English BCV በቲ ጊዜ እቱይ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኽመውት ቀረበ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ድማ ናብኡ መፂኡ “ንስኻ ኽትመውት ኢኻ እምበር፥ ኣይትሓውን ኢኻ እሞ ቤትካ ኣመዓራሪ ይብል ኣሎ እግዚኣብሄር” ኢሉ… ትግርኛ GAZBIB Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas raajichi ilmi Amos gara isaa dhaqee,“Waaqayyo,“Ati in duuta mal… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ደወየ ሕዝቅያስ ወበጽሐ ለመዊት፤ ወቦአ ኢሳይያስ ነቢይ ወልደ አሞጽ ኀቤሁ፤ ወይቤሎ፦ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሥራዕ ቤተከ እስመ ትመውት ወኢተሐዩ። giz GAZGAZ Baras Hisqiyaas dhukkubsatee du'uu ga'ee ture; Isaayaas raajichi ilmi Amos gara isaa dhaqee,“Waaqayyo,“Ati in duuta mal… Afaan Oromoo BCV aksum በቲ ጊዜ እቱይ ሕዝቅያስ ሓሚሙ ኽመውት ቀረበ። ነቢይ ኢሳይያስ ወዲ ኣሞፅ ድማ ናብኡ መፂኡ “ንስኻ ኽትመውት ኢኻ እምበር፥ ኣይትሓውን ኢኻ እሞ ቤትካ ኣመዓራሪ ይብል ኣሎ እግዚኣብሄር” ኢሉ… ትግርኛ AMHNIV በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል”… አማርኛ SWAHSUV Siku hizo Hezekia akaugua, akawa katika hatari ya kufa. Isaya, nabii, mwana wa Amozi, akamjia akamwambia, Bwana asema h… Kiswahili