2ኛ ቆሮንቶስ 7

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:42 አዳምጥ
አዳምጥ 2:42 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።

2በልባችሁ ስፍራ አስፉልን፤ ማንንም አልበደልንም፥ ማንንም አላጠፋንም፥ ማንንም አላታለልንም።

3ለኵነኔ አልልም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።

4ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነው፥ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነው፤ መጽናናት ሞልቶብኛል፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ከመጠን ይልቅ ይበዛል።

5ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሥጋችን ዕረፍት አልነበረውም፤ በውጭ ጠብ ነበረ፥ በውስጥ ፍርሃት ነበረ።

6ነገር ግን ኀዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን፤

7በመምጣቱም ብቻ አይደለም ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም ቅንዓታችሁን ሲናገረን በእናንተ ላይ በተጽናናበት መጽናናት ደግሞ ነው፤ ስለዚህም ከፊት ይልቅ ደስ አለን።

8በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤

9በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና።

10እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።

11እነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል በመካከላችሁ አደረገ። በዚህ ነገር ንጹሐን እንደ ሆናችሁ በሁሉ አስረድታችኋል።

12እንግዲያስ የጻፍሁላችሁ ብሆን እንኳ፥ ስለ እኛ ያላችሁ ትጋታችሁ ከእናንተ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ እንጂ፥ ስለ በዳዩ ወይም ስለ ተበዳዩ አልጻፍሁም። ስለዚህ ተጽናንተናል።

13በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፥ መንፈሱ በሁላችሁ ዐርፎአልና፤

14ለእርሱ በምንም ስለ እናንተ የተመካሁ እንደ ሆነ አላፈርሁምና፥ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚህ ደግሞ ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።

15ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ፍቅሩ በእናንተ ላይ እጅግ በዝቶአል።

16በነገር ሁሉ ተማምኜባችኋለሁና ደስ ይለኛል።

ማብራሪያ

፯፡፩-፬ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ቅድስናን እንድንከታተል ጠንካራ ምክንያቶች ናቸው፤ ከሥጋና ከመንፈስ ርኵሰት ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። እግዚአብሔርን አባታችን አድርገን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ፣ እርሱ ቅዱስ እንደሆነ እኛም ቅዱሳን ለመሆን መጣር አለብን፤ በሰማይ እንዳለው አባታችን ደግሞ ፍጹማን መሆን አለብን። የእርሱ ጸጋ በመንፈሱ ተጽዕኖ ብቻውን ሊያነጻ ይችላል፤ ነገር ግን ቅድስና የማያቋርጥ ጸሎታችን ዓላማ መሆን አለበት።

የወንጌል አገልጋዮች የሚናቁ ከሆነ፣ ወንጌሉ ራሱም እንዳይናቅ አደጋ አለ፤ አገልጋዮች ማንንም ማሞኘት ባይገባቸውም፣ ለሁሉም የዋሆች መሆን አለባቸው። አገልጋዮች ክብርንና ሞገስን ሊፈልጉ ይችላሉ፤ ይህም በማንኛውም የሐሰት ትምህርት ወይም በሚያሞኝ ንግግር ማንንም እንዳላበላሹ፣ ማንንም እንዳላታለሉ፣ እንዲሁም ማንንም ሳይጎዱ የራሳቸውን ጥቅም ለማሳደግ እንዳልሞከሩ ለሕዝቡ በድፍረት መናገር ሲችሉ ነው። ሐዋርያው በነጻነት እንዲናገራቸውና በሁሉም ስፍራና በሁሉም አጋጣሚዎች ስለእነርሱ እንዲመካ ያደረገው ለእነርሱ ያለው ፍቅር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Since we have these promises, dear friends, let us purify ourselves from everything that contaminates body and spirit, … English BCV እምበኣርከስ፥ ኣቱም ፍቑራተይ፥ እዝ ዅሉ ተስፋ እዙይ ካብ ሃለወናስ፥ ካብቲ ዅሉ ስጋን መንፈስን ዘርክስ፥ ርእስና ነንፅህ። ንእግዚኣብሄር ብምፍራሕ፥ ቅድስናና ፍፁም ንግበሮ። ትግርኛ GAZBIB Yaa michoota ko! Abdii kana erga qabaannee, kottaa, waanuma dhagna keenyaa fi hafuura keenya xureessuttii of in qullees… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበእንተ ዘብነ ዝንቱ ተስፋ አኀዊነ ናንጽሕ ርእሰነ ወኢናግምን ነፍስተነ ወንግበር በዘንትቄደስ በፈሪሀ እግዚአብሔር። giz GAZGAZ Yaa michoota ko! Abdii kana erga qabaannee, kottaa, waanuma dhagna keenyaa fi hafuura keenya xureessuttii of in qullees… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣርከስ፥ ኣቱም ፍቑራተይ፥ እዝ ዅሉ ተስፋ እዙይ ካብ ሃለወናስ፥ ካብቲ ዅሉ ስጋን መንፈስን ዘርክስ፥ ርእስና ነንፅህ። ንእግዚኣብሄር ብምፍራሕ፥ ቅድስናና ፍፁም ንግበሮ። ትግርኛ AMHNIV እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው። አማርኛ SWAHSUV Basi, wapenzi wangu, kwa kuwa tuna ahadi hizo, na tujitakase nafsi zetu na uchafu wote wa mwili na roho, huku tukitimiz… Kiswahili