2ኛ ቆሮንቶስ 7

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:40 አዳምጥ
አዳምጥ 3:40 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው።

2ልባችሁን አስፉልን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም ወደ ብልሹነት አልመራንም፤ ማንንም አላታለልንም።

3ይህን የምለው ልኰንናችሁ አይደለም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ፣ በልባችን ውስጥ ስፍራ አላችሁ፤ ስለዚህ ብንኖርም ብንሞትም አብረን ነው።

4በእናንተ ላይ ያለኝ እምነት ትልቅ ነው፤ በእናንተም ላይ ያለኝ ትምክሕት ትልቅ ነው፤ እንዲሁም እጅግ ተጽናንቻለሁ፤ በመከራችንም ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።

5ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ ከየአቅጣጫው መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አላገኘም፤ ከውጭ ጠብ፣ ከውስጥ ደግሞ ፍርሀት ነበረብን።

6ይሁን እንጂ ሐዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን።

7የተጽናናነውም በመምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱንም ልታጽናኑት በመቻላችሁ ጭምር ነው። ስለ ናፍቆታችሁ፣ ስለ ሐዘናችሁና ለእኔም ስላላችሁ ቅናት ነግሮናል፤ ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ ብሎኛል።

8በመልእክቴ ባሳዝናችሁም በዚህ አልጸጸትም፤ ብጸጸትም እንኳ መልእክቴ ያሳዘናችሁ ለጥቂት ጊዜ እንደሆነ ተረድቻለሁ።

9አሁን ግን ደስ ብሎኛል፤ ደስታዬም ስላዘናችሁ ሳይሆን፣ ሐዘናችሁ ንስሓ ለመግባት ስላበቃችሁ ነው፤ ምክንያቱም ሐዘናችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከእኛ የተነሣ ምንም አልተጐዳችሁም።

10እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ወደ ድነት ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም። ዓለማዊ ሐዘን ግን ለሞት ያበቃል።

11ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው ሐዘን እንዴት ያለ ትጋት፣ እንዴት ያለ መልስ የመስጠት ችሎታ፣ እንዴት ያለ ቍጣ፣ እንዴት ያለ ፍርሀት፣ እንዴት ያለ ናፍቆት፣ እንዴት ያለ በጎ ቅናት፣ እንዴት ያለ ተግሣጽ እንዳስገኘላችሁ ተመልከቱ። በዚህም ጒዳይ ንጹሓን መሆናችሁን በሁሉ ረገድ አስመስክራችኋል።

12እንግዲህ እኔ የጻፍሁላችሁ ስለ በደለው ወይም ስለ ተበደለው ሰው አይደለም፤ ነገር ግን ለእኛ ምን ያህል ታማኞች እንደሆናችሁ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን እንድታዩ በማለት ነው።

13እኛም የተጽናናነው በዚህ ምክንያት ነው። ከእኛም መጽናናት በተጨማሪ በቲቶ ደስታ እኛም ይበልጥ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ሁላችሁም መንፈሱን አሳርፋችኋል።

14በእናንተ ላይ ያለኝን ትምክሕት ለእርሱ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም። ነገር ግን ስንነግራችሁ የነበረው ሁሉ እውነት እንደሆነ፣ እንደዚሁም ስለ እናንተ ለቲቶ በትምክሕት የነገርነው እውነት መሆኑ ተረጋግጦአል።

15እርሱም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁትና ሁላችሁም እንደ ታዘዛችሁ ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ፍቅር እየበረታ ሄዶአል።

16እኔም በማናቸውም ነገር ልተማመንባችሁ በመቻሌ ደስ ብሎኛል።

ማብራሪያ

፯፡፩-፬ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ቅድስናን እንድንከታተል ጠንካራ ምክንያቶች ናቸው፤ ከሥጋና ከመንፈስ ርኵሰት ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። እግዚአብሔርን አባታችን አድርገን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ፣ እርሱ ቅዱስ እንደሆነ እኛም ቅዱሳን ለመሆን መጣር አለብን፤ በሰማይ እንዳለው አባታችን ደግሞ ፍጹማን መሆን አለብን። የእርሱ ጸጋ በመንፈሱ ተጽዕኖ ብቻውን ሊያነጻ ይችላል፤ ነገር ግን ቅድስና የማያቋርጥ ጸሎታችን ዓላማ መሆን አለበት።

የወንጌል አገልጋዮች የሚናቁ ከሆነ፣ ወንጌሉ ራሱም እንዳይናቅ አደጋ አለ፤ አገልጋዮች ማንንም ማሞኘት ባይገባቸውም፣ ለሁሉም የዋሆች መሆን አለባቸው። አገልጋዮች ክብርንና ሞገስን ሊፈልጉ ይችላሉ፤ ይህም በማንኛውም የሐሰት ትምህርት ወይም በሚያሞኝ ንግግር ማንንም እንዳላበላሹ፣ ማንንም እንዳላታለሉ፣ እንዲሁም ማንንም ሳይጎዱ የራሳቸውን ጥቅም ለማሳደግ እንዳልሞከሩ ለሕዝቡ በድፍረት መናገር ሲችሉ ነው። ሐዋርያው በነጻነት እንዲናገራቸውና በሁሉም ስፍራና በሁሉም አጋጣሚዎች ስለእነርሱ እንዲመካ ያደረገው ለእነርሱ ያለው ፍቅር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። አማርኛ ENGNIV Since we have these promises, dear friends, let us purify ourselves from everything that contaminates body and spirit, … English BCV እምበኣርከስ፥ ኣቱም ፍቑራተይ፥ እዝ ዅሉ ተስፋ እዙይ ካብ ሃለወናስ፥ ካብቲ ዅሉ ስጋን መንፈስን ዘርክስ፥ ርእስና ነንፅህ። ንእግዚኣብሄር ብምፍራሕ፥ ቅድስናና ፍፁም ንግበሮ። ትግርኛ GAZBIB Yaa michoota ko! Abdii kana erga qabaannee, kottaa, waanuma dhagna keenyaa fi hafuura keenya xureessuttii of in qullees… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበእንተ ዘብነ ዝንቱ ተስፋ አኀዊነ ናንጽሕ ርእሰነ ወኢናግምን ነፍስተነ ወንግበር በዘንትቄደስ በፈሪሀ እግዚአብሔር። giz GAZGAZ Yaa michoota ko! Abdii kana erga qabaannee, kottaa, waanuma dhagna keenyaa fi hafuura keenya xureessuttii of in qullees… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣርከስ፥ ኣቱም ፍቑራተይ፥ እዝ ዅሉ ተስፋ እዙይ ካብ ሃለወናስ፥ ካብቲ ዅሉ ስጋን መንፈስን ዘርክስ፥ ርእስና ነንፅህ። ንእግዚኣብሄር ብምፍራሕ፥ ቅድስናና ፍፁም ንግበሮ። ትግርኛ SWAHSUV Basi, wapenzi wangu, kwa kuwa tuna ahadi hizo, na tujitakase nafsi zetu na uchafu wote wa mwili na roho, huku tukitimiz… Kiswahili