1ኛ ቆሮንቶስ 15

AMHNIVአማርኛ58 ጥቅሶች9:04 አዳምጥ
አዳምጥ 9:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አሁንም፣ ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ እወዳለሁ፤

2የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው።

3እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤

4ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤

5ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤

6ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን አንቀላፍተዋል።

7ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ በኋላም ለሐዋርያት በሙሉ ታየ፤

8ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምቈጠር ለእኔ ደግሞ ታየ።

9እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ፣ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ እንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን አሳድጃለሁ፤

10ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ እንዲያውም ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ዳሩ ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።

11እንግዲህ እኔም ሆንሁ እነርሱ የምንሰብከው ይህንኑ ነው፤ እናንተም ያመናችሁት ይህንኑ ነው።

12ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ፣ ከእናንተ አንዳንዶቹ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ?

13የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሣም ማለት ነዋ!

14ክርስቶስም ካልተነሣ ስብከታችን ዋጋ ቢስ ነው፤ እምነታችሁም ከንቱ ነው።

15ከዚህም በላይ፣ እግዚአብሔር ክርስቶስን ከሞት አስነሥቶታል ብለን በመመስከራችን፣ ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን የማይነሡ ከሆነ፣ ክርስቶስንም አላስነሣውም ማለት ነው፤

16ምክንያቱም ሙታን ካልተነሡ፣ ክርስቶስም አልተነሣም።

17ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው።

18እንዲህም ከሆነ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው።

19ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን።

20ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቶአል።

21ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና።

22ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤

23ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፣ ከዚያም በኋላ እርሱ ሲመጣ የክርስቶስ የሆኑት።

24ከዚያም ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ መንግሥትን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ፣ ያን ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል።

25ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።

26የሚደመሰሰውም የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው፤

27“ሁሉን ነገር ከእግሩ ሥር አስገዝቶለታል” ተብሎአልና፤ ነገር ግን፣ ሁሉን ነገር አስገዛለት ሲል፣ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ሥር እንዲገዛ ያደረገውን እግዚአብሔርን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።

28ሁሉ ከተገዛለት በኋላ እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ወልድ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል።

29ትንሣኤ ከሌለማ ለሞቱ ሰዎች ብለው የሚጠመቁት ምን እያደረጉ ነው? ሙታን ከቶ የማይነሡ ከሆነ፣ ሰዎች ለእነርሱ ብለው ለምን ይጠመቃሉ?

30እኛስ ብንሆን ዘወትር ለአደጋ የምንጋለጠው ለምንድን ነው?

31ወንድሞች ሆይ፤ እኔ በየቀኑ እሞታለሁ፤ ይህንንም በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክሕት አረጋግጣለሁ።

32በኤፌሶን ከአራዊት ጋር የታገልሁት ለሰው አስተያየት ብቻ ከሆነ ትርፌ ምንድን ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፤ “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፣ እንጠጣ፤” እንደሚሉት መሆናችን ነው።

33አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”

34ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።

35ነገር ግን፣ “ሙታን እንዴት ይነሣሉ? የሚመጡትስ በምን ዐይነት አካል ነው?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል።

36አንተ ሞኝ! የምትዘራው ካልሞተ ሕይወት አያገኝም።

37የምትዘራውም የስንዴ ወይም የሌላ ዐይነት ዘር ቅንጣት ብቻ እንጂ ወደ ፊት የምታገኘውን አካል አይደለም።

38እግዚአብሔር ግን እንደ ፈቀደ አካልን ይሰጠዋል፤ ለእያንዳንዱም የዘር ዐይነት የራሱን አካል ይሰጠዋል።

39ሥጋ ሁሉ አንድ አይደለም፤ የሰው ሥጋ አንድ ነው፤ የእንስሳት ሥጋ ሌላ ነው፤ የዓሣ ሥጋ ሌላ ዐይነት ነው።

40እንዲሁም ሰማያውያን አካላት አሉ፤ ምድራውያን አካላት አሉ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካላት ክብር አንድ ነው፤ የምድራዊም አካላት ክብር ሌላ ነው።

41የፀሓይ ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ነው፤ የከዋክብት ደግሞ ሌላ ነው፤ የአንዱም ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል።

42የሙታን ትንሣኤም እንደዚሁ ነው፤ የሚበሰብስ አካል ይዘራል፤ የማይበሰብስ አካል ሆኖ ይነሣል፤

43በውርደት ይዘራል፤ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል በኀይል ይነሣል፤

44ፍጥረታዊ አካል ይዘራል መንፈሳዊ አካል ይነሣል። ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ።

45ስለዚህ፣ “የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ” ተብሎ ተጽፎአል፤ የኋለኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።

46ነገር ግን በመጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፤ ከዚያም በኋላ መንፈሳዊው መጣ።

47የመጀመሪያው ሰው ከምድር የተገኘ ምድራዊ ነው፤ የኋለኛው ግን ከሰማይ ነው።

48ከምድር የሆኑት እንደ ምድራዊው ናቸው፤ ከሰማይ የሆኑትም እንደ ሰማያዊው ናቸው።

49የምድራዊውን ሰው መልክ እንደ ለበስን፣ የሰማያዊውን ሰው መልክ ደግሞ እንለብሳለን።

50ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም።

51እነሆ፤ አንድ ምስጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤

52ይህም የሚሆነው የመጨረሻው መለከት ሲነፋ ድንገት በቅጽበተ ዐይን ነው። መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።

53የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።

54የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተውም የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ፣ “ሞት በድል ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

55እንዲሁም፣ “ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? ሞት ሆይ፤ መንደፊያህስ የት አለ?”።

56የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው።

57ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

58ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።

ማብራሪያ

፩፭፥፩-፲፩ ትንሣኤ የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ከመቃብር ባሻገር ያለውን ሕልውናችንን ያመለክታል። የሐዋርያው ትምህርት ፈለግ በፈላስፋዎች ትምህርት ሁሉ ውስጥ ሊገኝ አይችልም። የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ትምህርት የክርስትና መሠረት ነው። ይህን ካስወገድነው፣ የዘላለም ተስፋዎቻችን ሁሉ በአንዴ ይወድቃሉ። ክርስቲያኖች በፈተና ቀን የሚቆሙትና ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው የሚጠበቁት ይህን እውነት አጥብቀው በመያዝ ነው። በወንጌል እምነት ውስጥ ካልጸናን በቀር፣ በከንቱ እናምናለን። ይህ እውነት በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች የተረጋገጠ ሲሆን፣ ብዙዎችም እርሱ ከሞት ከተነሳ በኋላ ክርስቶስን አዩ። ይህ ሐዋርያ እጅግ ጸጋ የሞላበት ነበር፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ስለ ራሱ ትሑት አስተሳሰብ ነበረው፣ እርሱም ይገልጸው ነበር። ኃጢአተኞች በመለኮታዊ ጸጋ ወደ ቅዱሳን ሲለወጡ፣ እግዚአብሔር የቀድሞ ኃጢአቶቻቸውን ትዝታ ትሑት፣ ታታሪና ታማኝ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በእርሱ የነበረውን ውድ ነገር ሁሉ ለመለኮታዊ ጸጋ ያደርጋል። እውነተኛ አማኞች፣ ጌታ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ውስጥና በእነርሱ አማካይነት ያደረገውን ቢያውቁም፣ ጠቅላላ ምግባራቸውንና ግዴታዎቻቸውን ሲመለከቱ፣ እንደ እነርሱ ምንም የማይረባ እንደሌለ እንዲሰማቸው ይደረጋሉ። ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እርሱም የተሰቀለው፣ ከዚያም ከሙታን የተነሳው፣ የክርስትና ሁሉ እምብርትና ይዘት እንደሆነ ያምናሉ። ሁሉም ሐዋርያት በዚህ ምስክርነት ተስማምተዋል፤ በዚህ እምነት ኖረዋል፣ በዚህም እምነት ሞተዋል።

፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፥፲፪-፲፱ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ካሳየ በኋላ፣ ሐዋርያው ትንሣኤ የለም ለሚሉ ሰዎች መልስ ይሰጣል። ክርስቶስ ባልተነሳ ኖሮ፣ ጽድቅ ወይም መዳን አይኖርም ነበር። እርሱ አሁንም በሙታን ዘንድ ቢገኝስ፣ በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት ከንቱና ዋጋ ቢስ መሆኑ አይቀርም ነበርን? የሥጋ ትንሣኤ ማስረጃ የጌታችን ትንሣኤ ነው። ክርስቶስ ባልተነሳ ኖሮ፣ በእምነት የሞቱትም እንኳ በኃጢአታቸው የጠፉ ይሆኑ ነበር።

በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ እንደ ቤዛ በእርሱ ተስፋ ያደርጋሉ፤ በእርሱም በኩል ለቤዛነትና ለመዳን ተስፋ አላቸው። ነገር ግን ትንሣኤ ወይም የወደፊት ምንዳ ከሌለ፣ በእርሱ ያላቸው ተስፋ ለዚህ ሕይወት ብቻ የተወሰነ ይሆናል። በተለይም ሐዋርያት በጻፉበት ጊዜና ሁኔታ፣ ክርስቲያኖች በሁሉም ዘንድ የተጠሉና የተሳደዱ ስለነበሩ፣ ከሌሎቹ ሰዎች ሁሉ የባሰ ሁኔታ ውስጥ ይሆኑ ነበር። ነገር ግን እንዲህ አይደለም፤ እነርሱ በሁሉም ችግሮቻቸውና ፈተናዎቻቸው መካከል፣ እጅግ በከፋ ስደት ጊዜም ቢሆን፣ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ የጸና መጽናናትን ያገኛሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ አማርኛ ENGNIV Now, brothers, I want to remind you of the gospel I preached to you, which you received and on which you have taken you… English BCV ሕዚ ኸዓ ኣሕዋተይ፥ ነቲ ኣነ ዝሰበኽኩልኩም ወንጌል፥ ከዘክረኩም እደሊ ኣለኹ። ንሱ ድማ እቲ ዝተቐበልኩምዎን፥ ብእኡ ድማ ፀኒዕኹም እትነብሩ ዘለኹምን እዩ። ትግርኛ GAZBIB Ammas yaa obboloota ko! Wangeela isa ani isinitti lallabe, isa isin fudhattan, isa isin itti cimtanii dhaabattanii jirt… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአጤይቀክሙ አኀዊነ ትምህርተ ዘመሀርኩክሙ፤ ዘአመ ተዐሎክሙ ዘቦቱ ሀለውክሙ ወዘቦቱ ተሐይዉ። giz GAZGAZ Ammas yaa obboloota ko! Wangeela isa ani isinitti lallabe, isa isin fudhattan, isa isin itti cimtanii dhaabattanii jirt… Afaan Oromoo BCV aksum ሕዚ ኸዓ ኣሕዋተይ፥ ነቲ ኣነ ዝሰበኽኩልኩም ወንጌል፥ ከዘክረኩም እደሊ ኣለኹ። ንሱ ድማ እቲ ዝተቐበልኩምዎን፥ ብእኡ ድማ ፀኒዕኹም እትነብሩ ዘለኹምን እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Basi, ndugu zangu, nawaarifu ile injili niliyowahubiri; ambayo ndiyo mliyoipokea, na katika hiyo mnasimama, Kiswahili