ትንቢተ ዘካርያስ 9

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:15 አዳምጥ
አዳምጥ 3:15 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፤ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፤

2ደግሞም በዳርቻዋ ባለችው በሐማት ላይ፥ እጅግ ጠቢበኞች በሆኑ በጢሮስና በሲዶና ላይ ነው።

3ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።

4እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፤ እርስዋም በእሳት ትበላለች።

5አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፤ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፤ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም።

6የተደባለቀ ወገን በአዛጦን ይቀመጣል፥ የፍልስጥኤማውያንንም ትዕቢት አጠፋለሁ።

7ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፤ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።

8እኔም ማንም እንዳይሄድና እንዳይመለስ እንደ ጠባቂ ጦር ሆኖ በቤቴ ዙሪያ ሰፈር አደርጋለሁ፤ አሁንም በዓይኔ አይቻለሁና ከዚህ በኋላ አስጨናቂ አያልፍባቸውም።

9አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

10ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ፤ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።

11ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።

12እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፤ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ።

13ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ፤ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ፤ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።

14እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።

15የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፤ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።

16በዚያም ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፤ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ይብለጨለጫሉ።

17በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።

ማብራሪያ

9:1-8 እዚህ ላይ በበርካታ ሕዝቦች ላይ የተነገሩ ፍርዶች ተዘርዝረዋል። መቄዶናውያንና የአሌክሳንደር ተተኪዎች በእነዚህ አገሮች ጦርነት ውስጥ ሳሉ፣ ጌታ ሕዝቡን እንደሚጠብቅ ቃል ገብቷል። የእግዚአብሔር ቤት በጠላት አገር መካከል ይገኛል፤ ቤተ ክርስቲያኑም በእሾህ መካከል እንዳለች ጽጌረዳ ናት። የእግዚአብሔር ኃይልና ቸርነት በእርሷ ልዩ ጥበቃ ውስጥ ይታያል። ጌታ በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ይሰፍራል፤ የትዕቢተኞች ተቃዋሚዎች ሠራዊት ሲያልፍና ሲመለስም ዓይኖቹ በእርሷ ላይ ይጠብቃሉ፣ ስለዚህም ሊያሸንፏት አይችሉም። ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ምንም ዓይነት አስጨናቂ (ግብር ሰብሳቢ) በእርሷ ዘንድ ዳግመኛ የማያልፍበት ጊዜ ይመጣል።

9:9-17 ነቢዩ ስለ መሲሑ መምጣት በደስታ ይገልጣል፤ እርሱም ጥንቶቹ አይሁድ ይህን ትንቢት ስለ እርሱ እንደሆነ የፈቱት ነው። ኢየሩሳሌም ሲገባም በሕዝቡ ሁለንተናዊ ሆሣዕና መካከለ የንጉሣቸውን ባህርይ ተጎናጸፈ። ነገር ግን መንግሥቱ መንፈሳዊ መንግሥት ነው። በውጫዊ ኃይል ወይም በሥጋዊ የጦር መሣሪያ አይራመድም። ወንጌሉ ለዓለም ይሰበካል፤ በአሕዛብም ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The word of the Lord is against the land of Hadrach and will rest upon Damascus– for the eyes of men and all the tribes… English BCV ፆር ቃል እግዚኣብሄር ኣብ ምድሪ ሴድራክ እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ደማስቆውን ይዓርፍ፤ ዓይኒ እግዚኣብሄር ከዓ፥ ኣብ ልዕሊ ሰባትን ኣብ ልዕሊ ዅሉ ነገድ እስራኤልን እዩ። ትግርኛ GAZBIB Dubbiin Waaqayyo waa'ee biyya Hadraakiif dubbate mandara Damaasqoo irras in ga'e; iji namoota kan biraa, iji gosoota Is… Afaan Oromoo BCV GIZ ተረፈ ቃለ እግዚአብሔር በምድረ ሴድራ ወደማስቆ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር ወኵሉ ሕዝበ እስራኤል። giz GAZGAZ Dubbiin Waaqayyo waa'ee biyya Hadraakiif dubbate mandara Damaasqoo irras in ga'e; iji namoota kan biraa, iji gosoota Is… Afaan Oromoo BCV aksum ፆር ቃል እግዚኣብሄር ኣብ ምድሪ ሴድራክ እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ደማስቆውን ይዓርፍ፤ ዓይኒ እግዚኣብሄር ከዓ፥ ኣብ ልዕሊ ሰባትን ኣብ ልዕሊ ዅሉ ነገድ እስራኤልን እዩ። ትግርኛ AMHNIV የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፎአልና። አማርኛ SWAHSUV Ufunuo wa neno la Bwana, lililosemwa juu ya nchi ya Hadraki, na Dameski itakuwa mahali pake pa kustarehe; kwa maana jic… Kiswahili